ተዘራ ኃይለ ሚካኤል ዝነኛ ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ ነው።

ተዘራ ኃይለ ሚካኤል በ፲፱፻፴ ዓ.ም. በሸዋ ክፍለ ሀገር በየረርና ከረዮ አውራጃ ደብረ ዘይት ከተማ ልዩ ስሙ ሆራ በተባለው ሥፍራ ተወለደ። ተዘራ በወላጅ አባቱ የሥራ ፀባይ የተነሳ ባሌንና ወለጋን ገና ሕፃን ሳለ ረግጧቸዋል። በ፲፱፻፴፰ ዓ.ም. ወደ አዲስ አበባ መጥቶ በዳግማዊ ምኒልክ ትምህርት ቤት እስከ 9ኛ ክፍል ድረስ ተማረ።

ከድምፃዊነቱ ባሻገር በጊታር ጨዋታ የተካነ ነው። በተጨማሪም የዜማና የግጥም ድርሰት ዕጣ ክፍሉ ናቸው። ተዘራ በአብዛኛው የሚታወቀው በቁመቱ ነው። ከሚጫወትበት የጊታር መሣሪያ ከፍ የሚለው በጥቂቱ ነው።

ተዘራ በረጅም ዘመን ቆይታው ከተጫወታቸው አያሌ ዘፈኖች ውስጥ «እኔ ነኝ ተዘራ» እና «ማን ይሆን ተርጓሚ» የተሰኙት ዜማዎቹ በሕዝቡ ዘንድ እንዲታወቅ አድርገውታል።