አትክልት
ዕፅዋት ከሕያዋን ነገሮች አምስቱ ዋና ዘርፎች አንዱ ናቸው። ምግበለፊ ውኑክለስ ናቸው፣ ይህም ማለት የራሳቸውን ምግብ ይሰራሉ እና ውስብስብ ወይም ባለኑክለስ ህዋስ (ሴሎች) ያላቸው ናቸው። አብዛኞቹ ዕፅዋት ከስፍራ ወደ ስፍራ መዛወር እንደ እንስሶች አይችሉም። ሲበቅሉ ግን እጅግ ቀስ ብለው ይዞራሉ።
በዕፅዋት ዘርፍ ውስጥ ታዋቂ አይነቶች ዛፍ፣ ዕፅ፣ ቊጥቋጥ፣ ሣር፣ ሐረግ፣ ፈርን፣ ሽበትና አረንጓዴ ዋቅላሚ ይገኛሉ። በዕፅዋት ጥናት ዘንድ፣ አሁን 350,000 ያሕል የዕፅዋት ዝርያዎች ይኖራሉ። ፈንገስ እና አረንጓዴ ያልሆነ ዋቅላሚ ግን እንደ ዕፅዋት አይቆጠሩም።
አብዛኛዎቹ ዕፅዋት በመሬት ውስጥ ይበቅላሉ፣ አገዳቸው ከላይና ሥራቸው በታች አላቸው። አንዳንድ በውኃ ላይ ሰፋፊዎች ናቸው። ውኃና ምግብ የሚያገኙ በሥሮቻቸው በኩል ነው፤ ከዚያ በአገዳ ወጥተው እስከ ቅጠሎች ድረስ ሲጓዙ ነው። በቅጠሎች ውስጥ በሚገኙት ትንንሽ ቀዳዳዎች ውኃ በፀሐይ ዋዕይ በመትነን፣ ውኃው በአገዳው መንገድ ምግብን ከታቹ ወደ ላይ ይስባል። ይህም ስበተ ቅጠላበት ይባላል።
ዕፅዋት ምግብን እንዲሠሩ፣ የሚያስፈልጉዋቸው የፀሐይ ብርሃን፣ ካርቦን ክልቶኦክሳይድ፣ የመሬት ማዕድንና ውኃ ነው። አረንጓዴው ሃመልሚል (ክሎሮፊል) የፀሐይቱን አቅም ይወስዳል።
እንደ እንሥሣት፣ ዕፅዋትም የእንስትና የተባእት የዘር ህዋስ (gamete) ያመነጫሉ። በተጨማሪ፣ ብዙ የዕፅዋት አይነቶች ወሲባዊ በማይሆን ዘዴ መስፋፋትና መባዛት ይችላሉ። ይህ እፃዊ ተዋልዶ ይባላል።
ሥነ ሕይወታዊ ክፍፍሎች
ለማስተካከልበሥነ ሕይወት ጥናት ዘንድ፣ ዕፅዋት አንድ የሕይወት ስፍን ሲሆን የሚከተሉ ክፍለስፍኖች ብውስጡ ይመደባሉ፦
የመሬት ሃመልማል Embryophyte | ሃመልማል Viridiplantae | |
አረንጓዴ ዋቅላሚ | ||
ሌላ ዋቅላሚ Biliphyta (ባብዛኛው እንደ አትክልት አይመደቡም) |
ክፍለስፍን | ሮማይስጥ | መኖሪያ | የባሕርይ ልዩነት | ዝርያ ቁጥር |
---|---|---|---|---|
ዱኬ ቀንድ | Anthocerotophyta[1] | ዓለም አቀፍ | ቀንድ ያለ ዱኬ ወለድ፣ ሸንዳ የለሽ | 100-300+ |
ሳረንስት | Bryophyta | አለም አቀፍ | ዘለቄታዊ ቅርንጫፍ የለሽ ዱኬ ወለድ፣ ሸንዳ የለሽ | 12000 ያህል |
የባሕር ድንጋይ አረንጌዴ ዋቅላሚ | Charophyta | ጨው አልባ ውሆች | 1000 ያህል | |
የባሕር አረንጓዴ ዋቅላሚ | Chlorophyta | አለም አቀፍ | 7000 ያህል | |
የንጉሥ አሚዶ ዘምባባ ክፍለስፍን | Cycadophyta | ገሞጂዎች | ባዶ ዘር፣ የድርብርብ ቅጠል አናት | 100-200 |
የብር ባሕርኮክ (ጊንኮ) | Ginkgophyta | ቻይና | ባዶ ዘር ዛፍ | 1 ብቻ |
ሰማያዊ ዋቅላሚ | Glaucophyta | ጨው አልባ ውሆች | 13 | |
የመሊንጆ ክፍለስፍን | Gnetophyta | አንዳንድ አገሮች | ባለዘር፣ ሸንዳማ እንጨት | 70 |
የበትረሳረንሰት ክፍለስፍን | Lycopodiophyta Lycophyta |
አለም አቀፍ | ነጠላ ሸንዳ ዕጽ | 1290 |
ክንንብ ዘር፣ አባቢ አትክልት | Magnoliophyta | አለም አቀፍ | አበባ፣ ፍሬ፣ ሸንዳማ እፅ | 300,000 |
ጉብ ዕጽ | Marchantiophyta,[2] Hepatophyta |
አለም አቀፍ | ኢዘለቄታዊ፣ ቅርንጫፍ የለሽ ዱኬ ወለድ፤ ሸንዳ የለሽ | 9000 ያህል |
ዘረ ቅምብብ | Pinophyta Coniferophyta |
አለም አቀፍ | ባለዘር ቅምብብ፣ ሸንዳማ እንጨት | 629 |
ፈርን | Monilophyta | አለም አቀፍ | ቀዳማይ ብቃይ ህዋስ ወለድ እፅ፣ ሸንዳማ | 9000 ያህል |
ቀይ ዋቅላሚ | Rhodophyta | ዓለም አቀፍ | 7000 ያህል | |
ድምሩ፦ 14 |
- ^ Mauseth, James D. (2012). Botany : An Introduction to Plant Biology (5th ed.). Sudbury, MA: Jones and Bartlett Learning. ISBN 978-1-4496-6580-7. p. 489
- ^ Crandall-Stotler, Barbara; Stotler, Raymond E. (2000). "Morphology and classification of the Marchantiophyta". in A. Jonathan Shaw & Bernard Goffinet (Eds.). Bryophyte Biology. Cambridge: Cambridge University Press. p. 21. ISBN 0-521-66097-1.