ተስፋ ጎህ ኢትዮጵያ (Dawn of Hope Ethiopia association) የኤች·አይ·ቪ በሽታን ለመከላከል እና ባለበት ደረጃ ለመግታት «ትዉልድ ይዳን በእኛ ይብቃ» በሚል ክቡር አላማ ተነሳስተው ዘውዱ ጌታቸው እና አሥር ከኤችአይቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ወገኖቻችን ሰኔ 1990 ዓ.ም የመሰረቱት ማህበር ነው። ይህ ማህበር ለትርፍ ያልቆመ፣ ከማንኛውም የፖለቲካና የሀይማኖት ወገንተኝነት ነፃ የሆነ ማህበር ነው። ተስፋ ጎህ ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከ10 ሺህ በላይ ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ አባላት ሲኖሩት በመላው ኢትዮጵያም 12 ቅርንጫፎች አሉት፦ ሐረርሁመራሻሸመኔባህርዳርናዝሬትአዲስ አበባአዋሳደብረዘይትደብረብርሃን እና ዲላ ናቸው።

ራዕይ

የተስፋ ጎሀ ማህበር ራዕይ ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ነፃ የሆነ ትውልድን ማየት ነው።

ዓላማዎች

  • ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ወገኖችና ወላጅ አልባ ሕፃናት እንክብካቤ እንዲያገኙ መርዳት፣
  • ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ወገኖችና ወላጅ አልባ ሕፃናት መብት እንዲከበር መታገል፣ ኤች·አይ·ቪ/ኤድስን ለመከላከልና ለመቆጣጠር በሚደረገው ትግል በግንባር ቀደምትነት መሰለፍ።
  • በትምሕርት፣ በድጋፍና ክብካቤ ፕሮግራሞች አማካኝነት የአባላቱ ጥያቄዎች የሚሟሉበትን መንገድ ለማፈላለግና የአባላቱን መብት ለማስጠበቅ የተቋቋመ ነው።

እንቅስቃሴዎች

  • ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ወገኖቻችን ላይ በማንኛውም መልክ የሚከሰተውን መድሎና መገለልን መታገል፣
  • ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር የሚኖሩ ወገኖቻችን የኤች·አይ·ቪ/ኤድስን በተመለከተ በሚቋቋሙ ምክር ቤቶችና መድረኮች ሁሉ በውሳኔ ሰጪነት ደረጃ ተሳትፎና ውክልና እንዲኖራቸው ማድረግ፣
  • የአባላትን አቅም በመገንባት በማህበሩ እንቅስቃሴዎች ሁሉ እንዲሳተፍ ማድረግ፣
  • መገናኛ ብዙሀንን በመጠቀም ኤች·አይ·ቪ/ኤድስን ለመከላከሉ ዘመቻ ሕብረተሰቡን ስለበሽታው በስፋት ማስተማር፣
  • ማህበሩ ለወደፊቱ በራሱ ገቢ የሚተዳደርበትን ሁኔታ ማመቻቸትና አባላቱም አምራች ዜጋ የሚሆኑባቸውን ስልቶች መቀየስ፣
  • አባላቱ በማናቸውም ብሔራዊና አለም አቀፋዊ እንቅስቃሴዎች ውስጥ የጎላ ተሳትፎ እንዲኖራቸው ማድረግ ናቸው።

ማስተማር እና መቀስቀስ

  • የምክር አገልግሎት መስጠት፦ የቅድመ ምርመራ፣ ድህረ ምርመራና ቀጣይ የምክር አገልግሎት መስጠት
  • ከኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ጋር ተስማምቶ ለመኖር መከተል ስላለባቸው መመሪያዎች ማስተማር
  • ህብረተሰቡ ስለ ኤች·አይ·ቪ/ኤድስ ያለውን ግንዛቤ አሳድጎ ራሱን እንዲጠብቅና በዚህም የወረርሽኙን ተዛማጅነት ለመቀነስ በአባላት አማካኝነት በተለያዩ መድረኮች ትምህርት መስጠት።

ክብካቤና ድጋፍ

  • በኤች·አይ·ቪ ቫይረስ ምክንያት ለሚከሰቱ በሽታዎች ማስታገሻ የመድሃኒት ግዢ ድጋፍ መስጠት፣
  • በኤድስ ሳቢያ ወላጆቻቸውን ላጡ ሕፃናት የሚገባውን ድጋፍ መስጠት፣
  • በኤድስ ሳቢያ ታመው አልጋ ላይ ለዋሉ አባላት ሁለገብ ድጋፍ መስጠት

ሰብአዊ መብት ማስጠበቅ

  • ከኤች·አይ·ቪ/ኤድስ ጋር የሚኖሩ ወገኖች መገለልና መድልዎ እንዳይደርስባቸው መከላከልና በዚህ ረገድ የሚከሰቱ አጋጣሚዎችን ለሕግ አካላት ማቅረብነ የመብት ማስጠበቅ ስራ መስራት

የማሀበሩ የገንዘብ ድጋፍ ምንጮች

  • አገር አቀፍ የኤች·አይ·ቪ/ኤድስ መከላከያና መቆጣጠሪያ ጵ/ቤት (HAPCO)
  • ከተለያዩ በጎ አድራጊ ግለሰቦች
  • Médecins Sans Frontières the Netherlands
  • Netherlands and British Embassies
  • Norwegian Church Aid
  • Action Aid
  • Voluntary services overseas
  • ACCORD Canada
  • Care international & Care Ethiopia
  • CRDA
  • CIDA
  • Pact US
  1. [1] Archived ሜይ 1, 2008 at the Wayback Machine