ቦድብካድ
ቦድብካድ በአይርላንድ አፈ ታሪክ ምናልባት በ366 ግድም የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።
በ17ኛው ክፍለ ዘመን የታተሙት የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት የቦድብካድ ዘመን ፩ ቀን ከግማሽ ብቻ ነበር። ቅድመኞችሁ ታሪኮች ግን ቦድብካድ ንጉሡን ኡጋይነ ሞር ከገደለ በኋላ፣ የኡጋይነ ልጅ ሎጋይረ ሎርክ ቦድብካድን ገድሎ በቀጥታ ከፍተኛ ንጉሥ ሆነ።
በተለይ የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብሮ) እና የድሮ አቆጣጠር በመከተል፣ ይህ ዘመን በ366 ዓክልበ. ይሆናል። በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።