ቦሎሶ ቦምቤ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ በዎላይታ ከሚገኙ ወረዳዎች አንዱ ነው። ቦሎሶ ቦምቤ በደቡብ በኪንዶ ኮይሻ ፣ በምዕራብ በዳውሮ ዞን ፣ በሰሜን ከከምባታ ዞን ፣ በምስራቅ በቦሎሶ ሶሬ ፣ በሰሜን ምዕራብ የጠምባሮ ልዩ ወረዳ እና በደቡብ ምስራቅ በዳሞት ሶሬ ይዋሰናል። የዚህ ወረዳ አስተዳደር ማዕከል ቦምቤ ከተማ ነው። የወረዳው ኬክሮስ እና ኬንትሮስ አቀማመጥ 7°08'15.1"ሰሜን 37° 34'54.1"ምስራቅ ነው።

ቦሎሶ ቦምቤ
Bolooso Bombbe
ወረዳ
ቦሎሶ ቦምቤ መልካዓ ምድር
ሀገር ኢትዮጵያ
ክልል ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት
ዞን ዎላይታ
ርዕሰ ከተማ ቦምቤ
የሕዝብ ብዛት
   • አጠቃላይ 109,789

የስነ ሕዝብ አወቃቀር

ለማስተካከል

በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በተካሄደው የ2019 የህዝብ ብዛት ትንበያ መሰረት [1] ይህ ወረዳ በድምሩ 109,789 ህዝብ ያለው ሲሆን ከነዚህም 53,460 ወንዶች እና 56,329 ሴቶች ናቸው። 1,057 ወይም 1.2% የወረዳው ህዝብ የከተማ ነዋሪዎች ናቸው። አብዛኛው ነዋሪ ፕሮቴስታንቶች ናቸው፣ 69.27% የሚሆነው ህዝብ ነው ይህንን እምነት ተከታዮች፣ 26.86% የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና እምነት ተከታዮች፣ እና 1.26% የካቶሊክ እምነት ተከታዮች ናቸው።