ብራና መቅደስሙት ባሕር ብራናዎች መኃል አንድ ነው። ይህ ብራና ጥቅል በ1948 ዓ.ም. በዋሻ ቢገኝም እስከ 1959 ዓ.ም. ድረስ በሊቃውንት አልተተረጎመም ነበር። የተጻፈው በዕብራይስጥ ሲሆን ስለቤተ መቅደስ የሚነኩ የእግዚአብሔር ትዕዛዛት ለሙሴ ይከትታል።

በነዚህ ትእዛዛት የዘላለማዊ ቤተ መቅደስ ዝርዝሮች፣ ሥርዓቶችና ደንቦች ለሙሴ ይገለጻሉ። ሆኖም በታሪክ የእስራኤል ንጉስ ሰሎሞን ቤተ መቅደስ በኢየሩሳሌም በሠሩ ጊዜ፣ አሠራሩ በዚህ አይነት እቅድ አልነበረም። በዚህ ብራና የተገለጸው ቤተ መቅደስ ገና መቸም አልተሠራም። ቤተ መቅደሱ በዚህ የተሰጠው መጠን በነቢዩ ሕዝቅኤል ራዕይ ከታየው ቤተ መቅደስ መጠን ይልቅ ይበልጣል (ትንቢተ ሕዝቅኤል ምዕ. 40-47)። በምዕራብ ሊቃውንት አስተያየት ዘንድ፣ ያልታወቀ ደራሲ፦ «የኢየሩሳሌም መቅደስ እንደ ሰሎሞን መቅደስ ሳይሆን እንዲህ መሆን ነበረበት» የሚል ሀሣብ ለማቅረብ ፈልጎ ነበር።

ብራናው በየዓመቱ ስለሚከበሩ በዓላት ስርዓቶች ይዘረዝራሉ።

  • የቂጣ በዓልና ነዶውን መወዘወዙ
  • የሰንበታትና የበኲር መከር በዓላት
  • የወይን በዓል
  • የዘይት በዓል
  • የእንጨት በዓል

መሠረቱ ቅዱስ ስለሚሆን፣ ፈሻሽ ነገር ያለበት ሰው ወደ መቅደሱ ግቢ ሳይገባ ለ7 ቀን በርኩስና መቆየት አለበት። እንዲሁም መቅደሱ ያለበት ከተማ (ዘላለማዊው ኢየሩሳሌም) በሙሉ ቅዱስ ስለሆነ ግብረ ስጋ ግንኙነት በከተማው ውስጥ ይከለክላል። ማንም ባለትዳር ወደ ከተማው ሳይገባ ከሩካቤ ሁሉ 3 ቀን መቆየት አለበት። ነገር ግን በዚህ ብራና የተጻፉት እነዚህና ብዙ ሌሎች ደንቦች በታሪክ ውስጥ መቸም በተግባር አልታወቁም ነበር።

የውጭ መያያዣ

ለማስተካከል