ባሌ ሀዋሳ
(ከበሌ የተዛወረ)
ባሌ ሀዋሳ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል በወላይታ ዞን የሚገኝ ከተማ ነው። ከተማውም በወላይታ ዞን የኪንዶ ኮይሻ ወረዳ የአስተዳደር ዋና ከተማ ሆኖ ያገለግላል። ባሌ ሀዋሳ በዎላይታ ዞን ውስጥ ካሉት ሰባት ከተማ አስተዳደሮች አንዱ ነው። ከአዲስ አበባ ወደ ደቡብ በአዲስ ቡታጅራ-ሶዶ መንገድ ስከሄድ እስከ 400 ኪሎ ሜትር ርቀት ይደርሳል። ከወላይታ ዞን ዋና ከተማ ከሶዶ በ38 ኪሎ ሜትር ርቀት ላይ ይገኛል። ከተማው በአማካይ ከባህር ጠለል በላይ 1500 ሜትር ከፍታ አላው። በሌ በካርታ ስታይ በ6°55'05" ሰሜን እና በ37°31'55" ምስራቅ መካከል ይገኛል።
ባሌ ሀዋሳ Bale Hawaasa | |
ከተማ | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክልል | ደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት |
ዞን | ወላይታ |
ወረዳ | ኪንዶ ኮይሻ |
ከፍታ | 1,500 ሜ. |
የህዝብ ቁጥር
ለማስተካከልባሌ ሀዋሳ በደቡብ ኢትዮጵያ ክልላዊ መንግስት ውስጥ ሕዝብ ተጠጋግተው ከሚኖርባቸው ቦታዎች አንዱ ነው። እ.ኤ.አ. በ 2020 የህዝብ ብዛት ትንበያ በማዕከላዊ ስታቲስቲክስ ኤጀንሲ በተካሄደው የከተማው አጠቃላይ የህዝብ ብዛት 16,926 ይይዛል። ከኢነዚህም ወንዶች 8,217 ሲሆኑ ሴቶች ደግሞ 8,709 ይቆጥራሉ።[1]
ምንጮች
ለማስተካከል- ^ "የበሌ ከተማ የህዝብ ብዛት". Archived from the original on 2022-07-07. በ2022-02-04 የተወሰደ.