ቋንቋ
የመግባቢያ መንገድ በፅሁፍ በድመጽ ውይም በተግባር
ቋንቋ የድምጽ፣ የምልክት ወይም የምስል ቅንብር ሆኖ ለማሰብ ወይም የታሰበን ሃሳብ ለሌላ ለማስተላለፍ የሚረዳ መሳሪያ ነው። በአጭሩ ቋንቋ የምልክቶች ስርዓትና እኒህን ምልክቶች ለማቀናበር የሚያስፈልጉ ህጎች ጥንቅር ነው። ቋንቋዎችን ለመፈረጅ እንዲሁም ለመክፈል የሚያስችሉ መስፈርቶችን ለማስቀመጥ ባለው ችግር ምክንያት በአሁኑ ሰዓት በርግጠኝነት ስንት ቋንቋ በዓለም ላይ እንዳለ ማወቅ አስቸጋሪ ነው። እንደ ተለያየ መስፈርት ግምት ከ3000 እስክ 7000 ቋንቋዎች በአለም ላይ እንዳሉ ስምምነት አለ።
የሰው ልጅ ቋንቋ በተፈጥሮ የሚገኝ ሲሆን ህጻናት ቋንቋን በደመ ነፍስ ይማራሉ። በተፈጥሮ የሚገኙ የሰው ልጅ ቋንቋዎች ከድምጽና ከየሰውነት ክፍሎች ምልክት ይፈጠራሉ። በሺሆች የሚቆጠሩ የሰው ልጆች ቋንቋዎች ቢኖሩም የሁሉም የጋራ የሆኑ ቋሚ ጸባዮች አሏቸው። እኒህ ቋሚ ጸባዮች በሁሉም የተፈጥሮ ቋንቋውች ሠርጸው የሚገኙ እንጂ ላንዱ ሰርተው ላንዱ የማይሰሩ አይደሉም።