ቀቿ
(ከቀችዋ የተዛወረ)
ቀቿ (Qhichwa Simi / Runa Shimi / Runa Simi) በደቡብ አሜሪካ በ10 ሚሊዮን ሰዎች የሚናገር ቋንቋ ነው። በጥንታዊ ኢንካ መንግሥት መደበኛ ቋንቋ ነበረ። ዛሬም በቦሊቪያ ፔሩና አንዳንድ አውራጃ በኤክዋዶር መደበኛ ሁኔታ አለው። አይማራ የሚባለው ሌላ ደቡብ-አሜሪካዊ ቋንቋ ዘመድ ነው።
እስፓንያውያን ከወረሩ አስቀድሞ በሰፊ ይሰማ ሲሆን በዚያን ጊዜ ምንም ጽሕፈት አልነበረውም። ይሁንና መቆጣጠር ሲባጎዎች በማሰር ዘዴ ነበር የተፈጸመ። ዛሬ የሚጻፈው በላቲን ፊደል ነው።
ስዋሰው
ለማስተካከልበቀችዋ ሦስት አናባቢዎች ብቻ አሉ እነሱም አ ኢ ኡ ናቸው።
ቁጥር | |||
ነጠላ | ብዙ | ||
ተውላጠ ስም | 1ኛ | Ñuqa ኑቃ | Ñuqanchik ኑቃንቺክ (ከነናንተ)
Ñuqayku ኑቃይኩ (ያለ እናንተ) |
2ኛ | Qam ቃም | Qamkuna ቃምኩና | |
3ኛ | Pay ፓይ | Paykuna ፓይኩና |
ቁጥሮች:- huk (1), iskay (2), kimsa (3), tawa (4), pichqa (5), suqta (6), qanchis (7), pusaq (8), isqun (9), chunka (10)
ግሦች
ለማስተካከል- ሙጫይ - መሳም
- ሙጫኒ - እስማለሁ
- ሙጫንኪ - ትስማለሽ / ትስሚያለሽ
- ሙጫን - ይስማል / ትስማለች
- ሙጫንቺክ - እንስማለን (እኔና እርስዎ)
- ሙጫይኩ - እንስማለን (ያለእርስዎ)
- ሙጫንኪቺክ - ትስማላችሁ
- ሙጫንኩ - ይስማሉ
- ሙጫርቃኒ - ሳምሁ (ሙጫርቃንኪ - ሳምክ ሳምሽ ወዘተ...)
- ሙጫሳቅ - ወደፊት እስማለሁ
- ሙጫስቃኒ - ስሜ ነበር
አብዛኛው አረፍተ ነገር የ'እርግጠኛነት ምልክት' ባዕድ መድረሻ አለው።
- -ሚ እርግጠኛነት ወይም ዕውቀት ያመለክታል: Tayta Wayllaqawaqa chufirmi ታይታ ዋይላቃዋቃ ቹፊርሚ - አቶ ዋይላቃዋቃ ነጂ ነው (እኔ ራሴ አውቀዋለሁ)።
- -ሲ የሚሰማ ወሬ ያመለክታል: Tayta Wayllaqawaqa chufirsi ታይታ ዋይላቃዋቃ ቹፊርሲ - አቶ ዋይላቃዋቃ ነጂ ነው (ስምቼ ነው)።
- -ቻ ሊሆን የሚችል ወይም የሚሆን ምናልባትነት ያመለክታል: Tayta Wayllaqawaqa chufircha ታይታ ዋይላቃዋቃ ቹፊርቻ - አቶ ዋይላቃዋቃ ነጂ ይሆናል።