ቀርጨጬ
ቀርጨጬ ከተማ በድጉና ፋንጎ ወረዳ ውስጥ የሚትገኝ ከተማ ናት። በደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል በወላይታ ዞን ይገኛል። ቀርጨጬ ከቤዴሳ በስተሰሜን 10 ኪ.ሜ. እንዲሁም ከቢቴና ደቡብ ምዕራብ በሶዶ-ዲምቱ ሀዋሳ መንገድ ላይ 8 ኪ.ሜ. ገደማ ትገኛለች።[1] ከአዲስ አበባ ከተማ እስከ ቀርጨጬ ከተማ ያለው ርቀት በግምት 362 ኪ.ሜ. በአዲስ-ሐዋሳ-ዲምቱ-ሶዶ መንገድ ላይ ይገኛል። ከወላይታ ዞን ዋና ከተማ ከሶዶ 38 ኪ.ሜ. ርቀት ላይ ይገኛል። በከተማዋ ያሉት አገልግሎቶች የ24 ሰአታት የኤሌክትሪክ መብራት፣ የንፁህ ውሃ አገልግሎት፣ አፀደ ህጻናት፣ አንደኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤት፣ የሁል ጊዜ ገበያ፣ ጤና ጣቢያ እና ሌሎችም ናቸው።
ቀርጨጬ Qarccacce Ambbaa | |
ከተማ | |
አገር | ኢትዮጵያ |
ክልል | ደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል |
ዞን | ወላይታ |
ወረዳ | ድጉና ፋንጎ |
ዋቢ
ለማስተካከል- ^ "Archive copy". Archived from the original on 2021-12-23. በ2021-12-23 የተወሰደ.