ሴይር
(ከሴይር ተራራ የተዛወረ)
ሴይር ተራራ (ዕብራይስጥ፦ הַר-שֵׂעִיר /ሀር-ሠዒር/) ከሞት ባሕርና አቃባህ ወሽመጥ መካከል ያለው ተራራማ አገር ነው። ይህ የኤዶምያስ ደቡብ-ምሥራቅ ጠረፍ ከይሁዳህ ጋር ነበረ። ምናልባትም ከዚያ በፊት የግብጽ ጠረፍ በከነዓን ይሆናል።
ሴይር ተራራ ስሙን ከ«ሖሪው ሴይር» አገኘ። የሖራውያን ጎሣ መታወቂያ ወይም ተወላጅነት በመጽሐፍ ቅዱስ ባይሰጥም፣ የዚህ ሴይር ልጅ ፅብዖን ደግሞ ኤዊያዊ በመባሉ (ዘፍጥ. ፴፮) የከነዓን ዘር ይመስላል።
በዘፍጥረት ፲፬፡፮ የኮሎዶጎምርና አምራፌል ሠራዊት አገራቸውን መቱ። በኋላ ግን የዔሳው ልጆች (ኤዶማውያን) በሖራውያን ላይ ድል አድርገው ከሴይር ምድር አባረሯቸው (ዘዳግም ፪)። ከዚህ በኋላ «ሴይር ተራራ» በመጽሐፍ ቅዱስ የእዶምያስ ምድር መጠሪያ ሆነ። (ዘፍጥ ፴፪፣ ፴፫፤ ኢያሱ ፳፬፤ ፩ ዜና መዋዕል ፬፤ ፪ ዜና መዋዕል ፳፤ ኢሳይያስ ፳፩፤ ሕዝቅኤል ፳፭፣ ፴፭።)
ሴይር ደግሞ በግብፅ መዝገቦች ከ3 አመንሆተፕ ዘመን (1388 ዓክልበ. ግ.) ታውቋል። በሶለብ ቤተ መቅደስ #፺፩ «ሴይር በሻሱ ምድር» (ታ-ሻሱ ሰዐር) ይዘርዝራል። «ሻሱ» በግብጽኛ የደቡብ ከነዓን አካባቢ መጠሪያ ነበር።