ሳይሌሲያን
የሳይሌሲያን ቋንቋ (ሳይሌሲያን፦ ślōnskŏ gŏdka, ślōnski, አንዳንዴ ደግሞ po naszymu) በፖላንድ የላይኛው ሳይሌሲያ ክፍለ ሀገር፣ በቼክ ሪፑብሊክ እና በጀርመን ሀገር የሚነገር ቋንቋ ነው። በ2011 እ.ኤ.አ. በፖላንድ በተካሄደው ብሔራዊ የሕዝብ ቆጠራ 509 000[1] ሺ ሰዎች ሳይሌሲያን የመጀመሪያ ቋንቋቸው እንደሆነ አስመዝግበዋል። አንዳንድ የቋንቋ ሊቃውንት የሳይሌሲያን ቋንቋ ከፖልኛ ቋንቋ ጋር በቅርብ የተዛመደ በመሆኑ፣ እንደ ቀበሌኛ አነጋገር ይቆጥሩታል
የሳይሌሲያ ቋንቋ ተናጋሪዎች የራሳቸው ፊደላት ስላልነበራቸው ለጽሑፍ የፖልኛን ፊደላት ይጠቀሙ ነበር። በ1998 በ10 የሳይሌሲያን ፊደላት እና ዲግራፎች (digraphs) የተመሠረተ የአጻጻፍ ደንብ ተፈጥሮ፣ በኢንተርኔትና በሳይሌሲያን ዊኪፔድያ የተስፋፋ ጥቅም ላይ ውሏል።
ማመዛገቢያ
ለማስተካከል- ^ Narodowy Spis Powszechny Ludności i Mieszkań 2011. Raport z wyników - Central Statistical Office of Poland
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |