ሲርላምአይርላንድ አፈ ታሪክ ከ612 እስከ 605 ዓክልበ. ግድም ድረስ የአየርላንድ ከፍተኛ ነጉሥ ነበር።

አብዛኛው የአይርላንድ ታሪኮች እንዳሉት የሲርላም ዘመን ለ16 ዓመታት ቆየ። የላውድ አቆጣጠሮች (1014 ዓም ተቀነባብሮ) 7 ዓመት ብቻ ይላል፤ ይህን የድሮ አቆጣጠር በመከተል፣ ከ612 እስከ 605 ዓክልበ. ድረስ ይሆናል። (በኋላ የታዩት ታሪኮች ግን ከዚያ በፊት ያደርጉታል።)