ሰይፉ ፋንታሁን
ሰይፉ ፋንታሁን ከ2006 ዓም ጀምሮ ለዘጠና ደቂቃ ሰይፉ በኢቢኤስ አስተናጋጁ ሆኖ ይቀርባል። በኢቢኤስ ቴሌቪዥን ላይ በየእሑድ ሌሊት ከኢትዮጵያ አዲስ አበባ እስቱዲዮ የሚሠራጭ የሌሊት ውይይት ትርዒት ነው። እንደ አሜሪካ አገር የሌሊት-ውይይት ልማድ በመምሰል፣ አስቂኝ ክፍሎች፣ የቀልድ ንግግሮች፣ ሙዚቃዊ ትርዕይቶችና የዝነኛ ቆይታዎችም ያቀርባል። እንደ በርካታ አሜሪካዊ ትዕይንቶች ስልት፣ የተመሠረተውን ስድስት ክፍል ፎርማት ይከተላል።