ሮቤል ተክለማርያም
ሮቤል ተክለማርያም (1966 ዓ.ም. የተወለደ) በ1998 (2006) በዊንተር ኦሊምፒክስ በስካይ ኢትዮጵያን የወከለ ብቸኛና የመጀመሪያ ሰው ከመሆኑም በላይ በዊንተር ኦሊምፒክስ ጨዋታዎች አፍሪካን የወከለ መጀመርያው ስፖርተኛ ነው።
ሮቤል በ9 አመቱ ወደ አሜሪካ ቢመጣም አገሩን በጣም ይወዳል። እስከዛሬ ድረስም አማርኛን አቀላጥፎ ይናገራል፡ ሮቤል በጣሊያኑ ኦሊምፒክ በውጭ አገር የሚኖሩት ኢትዮጵያውያን ባደረጉለት ከፍተኛ ማበረታት የአግሩ ባንዲራ ከሌሎች አገሮች ጎን እንዲውለበለብ እንዳስቻለው ተናግሮአል። ምንም እንክዋ ሮቤል ባደረጋቸው ውድድሮች(ተራራማና እና ሀገር አቋራጭ ስኪቲንግ) ውጤት ባያመስመዘግብም እንክዋ የኦሊምፒክ መግቢያ ሰዓት አስመዝግቦ የኢትዮጵያን ስም ማስጠራት በመቻሉ እስከ ዕድሜው መጨረሻ ኩራት እንደሚሰማው ተናግሮአል። በወቅቱ ፦ ሮቤል ለጋዜጤኞች ሲናገር «እኔ የተጨባጭ ሰው ነኝ። ዓላማዬ ይህ ኦሊምፒክ የሌሎችንም ኢትዮጵያውያን ዐይኖች እንዲከፍት ነው» ብሎአል። ሮቤል ተ/ማሪያም ባሁኑ ጊዜ በእሱና በታላቅ ወንድሙ በውስካንሰን የተቋቋመው ኢትዮጵያ ብሔራዊ ስካይ ፌዴሬሽንእስከ አገር ቤት ድረስ እውቅና እንዲያገኝ የበኩሉን ጥረት እያደረገ ነው።