ሦስቱ እኅትማማች
«ሦስቱ እኅትማማች» በእርሻ ተግባር በስሜን አሜሪካ ኗሪዎች (ቀይ ኢንዲያን የተባሉት) የተለማና የሚጠቀም የግብርና ዘዴ ነው። ሦስቱ ዋና ዋናዎች አዝመራዎቻቸው እነሱም በቆሎ፣ ባቄላ (ወይም ቦሎቄ)፣ እና ዱባ (ማናቸውም አይነት) አንድላይ ሲተከሉ ማለት ነው።
በአዚሁ ዘዴ አስቀድሞ ብዙ ትንንሽ የአፈር ቁልል ይደረጋል። የእያንዳንዱ ቁልል ከፍታ 30 ሴንቲ ሜትር ሲሆን ስፋቱ 50 ሴንቲ ሜትር ይሆናል። በመሃሉ አያሌ የበቆሎ ዘር አንድላይ ይጨመራል። በአንዳንድ ጎሣ ልማድ ደግሞ፣ ማዳበሪያ እንዲሆን የበሰበሰ ዓሣ ከዘሩ ጋር ይቀበራል።
የበቆሎው ቁመት እስከ 15 ሴንቲ ሜትር ድረስ ሲወጣ፣ ባቄላውና ዱባው በመፈራረቅ እንዲከብቡት ይዘራሉ።
እነዚህ ሦስት ሰብሎች በመጠቃቀም ይተባበራሉ። በቆሎው ለባቄላው መንጠላጠል የሚችል መዋቅር ስለሚሰጥ፣ ምሰሶ ማቆም አያስፈልግም። ባቄላውም ለሌሎቹ አትክልት በጣም አስፈላጊ የሆነውን ናይትሮጀን ወደ መሬት ለመጨመር ልዩ ችሎታ አለው። ዱባውም በመሬት ገጽ ላይ እጅግ ሲስፋፋ፣ መዓልቱን በመሸፈኑ አረምን ይከላከላል፤ እንዲሁም ሀረጉ ትንሽ እሾህ የመሰለውን ጸጉር ስላለው የሚጎዱ ነፍሳት ይከለከላል፤ ከዚህም በላይ የዱባ ቅጠል እርጥበት በመጠበቁ እንደ ማዳበሪያ ያገልግላል።
ሦስቱ ተክሎች ስለዚህ በጣም የሚስማሙ በመሆናቸው የበለጠ መልካም ምርት ሊያስገኙ ይቻላል። ይህ ዘዴ በሰፊ እርሻ ወይም ገነት ላይ ሲጠቀም ሚልፓ ይባላል።
የውጭ መያያዣዎች
ለማስተካከል- History of the Three Sisters: Corn, Beans and Squash Archived ማርች 11, 2008 at the Wayback Machine
- ስዕል Archived ኦገስት 12, 2008 at the Wayback Machine