መላእክት የኛን ጸሎት ስለሚያመላልሱ ስለኛ ያውቃሉ

ለማስተካከል

ከላይ እንዳየነው , "ባንድ ሀጥያተኛ መዳን " የተነሳ በሰማይ ደስታ እንዳለ ተመልክተናል ::

ሉቃስ በወንጌሉ , በዚህ ሳይወሰን , በመላእክት ፊት ደስታ እንዳለ ጠቁሞናል (ሉቅ 15:10) እላችኋለሁ፥ እንዲሁ ንስሐ በሚገባ በአንድ ኃጢአተኛ በእግዚአብሔር መላእክት ፊት ደስታ ይሆናል። ይህ ምንባብ እንግዲህ በምንም በማያሻማ መልኩ ስለኛ መዳን "መላእክት እንደሚጨነቁ አስረድቶን አልፏል ::

ከመጨነቅ አልፈውም , የኛን ጸሎት ወደ እግዚአብሔር ዙፋን እንደሚያደርሱ እና ስለዚህም ስለኛ እውቀት እንዳላቸው በዮሐንስ ራእይ ተመዝግቦ ይገኛል :- (ራእይ 8:3-4)

3 ሌላም መልአክ መጣና የወርቅ ጥና ይዞ በመሰዊያው አጠገብ ቆመ፤ በዙፋኑም ፊት ባለው በወርቅ መሰዊያ ላይ ለቅዱሳን ሁሉ ጸሎት እንዲጨምረው ብዙ ዕጣን ተሰጠው። 4 የዕጣኑም ጢስ ከቅዱሳን ጸሎት ጋር ከመልአኩ እጅ በእግዚአብሔር ፊት ወጣ። እዚህ ላይ እንደምናየው የቅዱሳን ጸሎት ከመላእክት እጅ ሲያርግ ሲሆን , ይህ ከሆነ ዘንድ እንዴት መላእክት የኛን ጸሎት አያውቁም ማለት እንችላለን ??

በዚህ ትይዩ , አይደለም መላእክት , ሀያ አራቱ ቀሳውስት እንኳን የኛን ጸሎት እንደሚያውቁና እንደሚያሳርጉ መ /ቅዱስ መዝግቧል ሀያ አራቱ ሽማግሌዎች በበጉ ፊት ወደቁ፥ እያንዳንዳቸውም በገናንና የቅዱሳን ጸሎት የሆነ ዕጣን የሞላበትን የወርቅ ዕቃ ያዙ። (ራእይ 5:Cool ይህ እሚያሳየው ወደ እግዚአብሔር የሚያርገውን የኛን ጸሎት እንድሚያውቁ ነው ::

ድጋሚ የተጠየቀ ጥያቄ :- ጻድቃን ሰማእታት ስለምድር ስለሚሆነው ያውቃሉን

ለማስተካከል

ከላይ እንዳየነው ቅዱስ ጳውሎስ ሲመሰክር : ሰማይ ያለው እውቀት መሬት ካለው እጅግ የገዘፈ መሆኑን አስረድቷል :: ለዚህ የጳውሎስ ምስክርነት ደጋፊ የመ /ቅዱስ ክፍል አለን ?

መልሱ አወ ነው :: በሉቃስ 16 ተመዝግቦ የሚገኘውን አላዛር ስለተባለ ድሀ , ሰለ አንድ ባለጠጋ ጎረቤቱና ስለአብርሀም , የክርስቶስ እየሱስ ምስክርነት እንከታተል :- 23 [ባለጠጋው ] በሲኦልም በሥቃይ ሳለ አሻቅቦ አብርሃምን በሩቅ አየ አልዓዛርንም በእቅፉ። 24 እርሱም እየጮኸ። አብርሃም አባት ሆይ፥ ማረኝ፥ በዚህ ነበልባል እሣቀያለሁና የጣቱን ጫፍ በውኃ ነክሮ መላሴን እንዲያበርድልኝ አልዓዛርን ስደድልኝ አለ።

25 አብርሃም ግን። ልጄ ሆይ፥ አንተ በሕይወትህ ሳለህ መልካም እንደ ተቀበልህ አስብ አልዓዛርም እንዲሁ ክፉ፤ አሁን ግን እርሱ በዚህ ይጽናናል አንተም ትሣቀያለህ።

ጥያቄ : አብርሀም እንዴት የባለጠጋውን የምድር ላይ ህይወት ሊያውቅ ቻለ :: ጥሩ ነገረስ ገጥሞት እንደ ነበር እንዴት አወቀ ?

(ሉቃ 16)27 እርሱም። እንኪያስ፥ አባት ሆይ፥ ወደ አባቴ ቤት እንድትሰደው እለምንሃለሁ፤ አምስት ወንድሞች አሉኝና፤ 28 እነርሱ ደግሞ ወደዚህ ሥቃይ ስፍራ እንዳይመጡ ይመስክርላቸው አለ። 29 አብርሃም ግን። ሙሴና ነቢያት አሉአቸው፤ እነርሱን ይስሙ አለው። 30 እርሱም። አይደለም፥ አብርሃም አባት ሆይ፥ ነገር ግን ከሙታን አንዱ ቢሄድላቸው ንስሐ ይገባሉ አለ። 31 ሙሴንና ነቢያትንም የማይሰሙ ከሆነ፥ ከሙታንም እንኳ አንድ ቢነሣ አያምኑም አለው።

ጻድቃን ሰማእታት ምድር ላይ ስለሚሆነው አያውቁም ከተባለ : እንዴት አባታችን አብርሀም ስለ ሙሴና ስለነቢያት ሊያውቅ ቻለ ? ሙሴና ነቢያት ከመወለዳቸው በፊት , አብርሀም በስጋ ሞት ከምድር ከተለየ ዘመናት አላስቆጠረምን ?? ስለዚህስ እንዴት አያውቅም በሚል እልህ እንቀጥላለን :: ቃሉ እንደሚያስረዳን , አብርሀም ያውቃል , ሙሴ ያውቃል , ቅዱስ ሰማእታት ያውቃሉ ::

የጌታችን ኢየሱስ ክርስቶስ ንግግር ሙሉ በሙሉ ምሳሌያዊ ነው። አብርሃም የእግዚአብሔር ምሳሌ፣ ሙሴና ነቢያትም የጌታን ቃል ለህዝብ የሚያስተምሩ አገልጋዮች ወይም የብሉይ ኪዳን መጽሐፍት እንደ ምሳሌ ሆነው መጠቀሳቸውን ልብ ማለት ይገባል። እንዲያውም መጽሐፍ ቅዱስ በግልጽ "ሙታን አንዳች አያውቁም" ይላል። (መክብብ. 9፡5)

ጻድቃን ነፍሳት ምስክርነት

ለማስተካከል

9 አምስተኛውንም ማኅተም በፈታ ጊዜ፥ ስለ እግዚአብሔር ቃልና ስለ ጠበቁት ምስክር የታረዱትን የሰዎች ነፍሳት ከመሠዊያ በታች አየሁ። 10 በታላቅ ድምፅም እየጮኹ። ቅዱስና እውነተኛ ጌታ ሆይ፥ እስከ መቼ ድረስ አትፈርድም ደማችንንስ በምድር በሚኖሩት ላይ እስከ መቼ አትበቀልም ? አሉ። 11 ለእያንዳንዳቸውም ነጭ ልብስ ተሰጣቸው፥ እንደ እነርሱም ደግሞ ይገደሉ ዘንድ ያላቸው የባሪያዎች ባልንጀራዎቻቸውና የወንድሞቻቸው ቍጥር እስኪፈጸም ድረስ፥ ገና ጥቂት ዘመን እንዲያርፉ ተባለላቸው። (ራእይ 6: 9-11)

ሰማእታተ , በስጋ ከሞቱ በሗላ , ጌታ ደማቸውን እንዳልተበቀለ እንደሚያውቁ ከላይ የተጠቀሰው የራእይ ክፍል ያስረዳናል :: በምድር የሚካሄደውን ካላወቁ ይህን ጉዳይ እንዴት ሊያውቁ ቻሉ ?

የነቢዩ ኤልያስ ደብዳቤ

ለማስተካከል

ንጉስ እዮራም , እንዴት ወንድሞቹን እንደገደለና የአይሁድን ዜጎች በሽርሙጥና -ባርነት እንደሸጠ የሚያትት ታሪክ በዜና መዋእል ካልእ ተመዝግቦ ይገኛል :: በዚሁ መጽሀፍ ከብዙ ዘመን በፊት , ከመሬት የተነጠቀው ነቢዩ ኤልያስ ለንጉሱ የጻፈውን ደብዳቤ እንዲህ ሲል ያስነብበናል :

12፤ ከነቢዩም ከኤልያስ እንዲህ የሚል ጽሕፈት መጣባት። የአባትህ የዳዊት አምላክ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል። በአባትህ በኢዮሣፍጥ መንገድ በይሁዳም ንጉሥ በአሳ መንገድ አልሄድህምና፥ 13፤ በእስራኤል ነገሥታት መንገድ ግን ሄደሃልና፥ የአክዓብም ቤት እንዳደረገ ይሁዳንና በኢየሩሳሌም የሚኖሩትን እንዲያመነዝሩ አድርገሃልና፥ ከአንተም የሚሻሉትን የአባትህን ቤት ወንድሞችህን ገድለሃልና፥ 14፤ እነሆ፥ እግዚአብሔር ሕዝብህንና ልጆችህን ሚስቶችህንም ያለህንም ሁሉ በታላቅ መቅሠፍት ይቀሥፋል። 15፤ አንተም ከደዌው ጽናት የተነሣ አንጀትህ በየዕለቱ እስኪወጣ ድረስ በክፉ የአንጀት ደዌ ትታመማለህ። (2ዜና 21:12-15)


እንዴት ነብዩ ኤልያስ በምድር ላይ ስለሚሆነው ሊያውቅ ቻለ ? ደብዳቤውንስ እንዴት ለንጉሱ ሊልክ ቻለ ?


የመላእክት ሰለኛ ጣልቃ መግባት

ካሁን በፊት እንደተዘረዘረው , መላእክት ካንዴም ሁለት ጊዜ , እንዲሁም ከዚያ በላይ ለሰው ልጆች ሲማልዱ አይተናል :: የጻድቃንንም ጸሎት ሲያሳርጉ , እንዲሁ ::

ጥያቄ :: ከላይ ከተዘረዘሩት ማስረጃወች ውጭ , መ /ቅዱስ ስለ መላእክት ምልጃ ተጨማሪ የመዘገበው ንባብ አለን ??

12፤ የእግዚአብሔርም መልአክ መልሶ። አቤቱ፥ የሠራዊት ጌታ ሆይ፥ እነዚህ ሰባ ዓመት የተቈጣሃቸውን ኢየሩሳሌምንና የይሁዳን ከተሞች የማትምራቸው እስከ መቼ ነው ? አለ። (ዘካ 1:12) እንግዲህ መላእኩ ሳይጠየቅ እንዲህ ሲል ከማለደ , ቢጠየቅማ የቱን ያክል ሊሆን ነው ?

በሌላኛው የትንቢተ ዘካርያስ መጽሀፍ ክፍል የእግዚአብሔር መላእክ በሰይጣን ተከሶ በእግዚአብሔር ፊት ለቀረበው ለሊቀ ካህኑ እያሱ እንዲ የሚል ማማለድ /ማጽናናት ሲያቀርብ እናያለን 3፤ ኢያሱም እድፋም ልብስ ለብሶ በመልአኩ ፊት ቆሞ ነበር። እርሱም [መልአኩ ] መልሶ በፊቱ የቆሙትን። እድፋሙን ልብስ ከእርሱ ላይ አውልቁ አላቸው። እርሱንም። እነሆ፥ አበሳህን [ሀጥያትክን ] ከአንተ አርቄአለሁ፥ ጥሩ ልብስም አለብስሃለሁ አለው። ሌላኛው ምሳሌ በኦሪት ዘፍጥረት ተመዝግቦ የሚገኘው ሲሆን , ይህ ክፍል እንዴት የእግዚአብሔር መላእክ , ያእቆብን ከጥፋት እንደታደገው ያስርዳና , ያእቆብ እራሱ ኤፍሬምንና ምናሴን ሲባርክ የተናገራቸውን ምርቃቶች እንዲህ ሲል ይመዘግባል 16፤ ከክፉ ነገር ሁሉ ያዳነኝ መልአክ፥ እርሱ እነዚህን ብላቴኖች ይባርክ፤ ስሜም የአባቶቼ የአብርሃምና የይስሐቅም ስም በእነርሱ ይጠራ፤ በምድርም መካከል ይብዙ። {ዘፍጥ 48:16)

ይህን ደጋፊ ክፍል በእብራውያን 1:14 ላይ በጥያቄ መልክ ተመዝግቦ ይገኛል :: መላእክት ሁሉ መዳንን የሚወርሱትን ለማገልገል የሚላኩ አገልጋይ መናፍስት አይደሉምን :: ይህ ክፍል በማያሻማ መልኩ መላእክት በምድር ላይ ስራ እንዳላቸው አስምሮበት አልፏል ::

በቀጣዩ ክፍል የጻድቃንን ታላቅነት , አገልግሎት , የእውቀታቸውን ስፋት , በእግዚአብሔር ዘንድ ያላቸውን ክብር /ሞገስ እናያለን :: ቀጥለንም በምልጃ ላይ የተነሱ ተቃውሞወች እና መልሶቸውን እናያለን :: ከዚያም በሰፊው በክርስቶስ ማማለድ እና በጻ /ሰማእታት , በመላእክት ማማለድ ያለውን ልዩነት አይተን , ለማሳረጊያ የምልጃን መንፈሳዊ ትርጉም አይተን እንዘጋለን :: እስከዛው ህያው እግዚአብሔር ለሁላችንም መባረክን ይስጠን :: _________________