ማካቬሊ በ 1469, ፍሎረንስ ከተማ , ጣልያን ሲወለድ , በ 1527 ሊያርፍ በቅቷል :: ከማካቬሊ በፊት በዙ ርዮቶች ቢኖሩም , የሱን ርዮት አብዮታዊ የሚያረገው ፖለቲካን ከሥነ ምግባር ነጻ ማውጣቱ ነበር :: ሥነ ምግባር (morals) በጅ የማይዳሰስ , በስንዝር የማይለካ ነው :: ሥነ ምግባር የሌለው ፖለቲካ እንግዲህ ሳይንሳዊ ፖለቲካ ሊባል ይችላል ምክንያቱም ውጤቱ ተጨባጭ ነውና ::ከማካቬሊ ታዋቂ መጽሀፎች ውስጥ , "the prince" ከፍተኝውን ቦታ ይይዛል :: ይህ መጽሀፍ ከያዛቸው ዋና ዋና ነጥቦች መካከል :-- 1) መሪዎች ለመፈራት ና ለመወደድ መሞከር አለባቸው ብሎ ይመክራል :: ከሁለቱ አንዱን የግድ መምረጥ ካለባቸው ግን : መፈራትን መምረጥ ይሻላል ብሏል :: 2) መሪዎች ምንጊዜም ደካማ ተቃዋሚን መታገስ አለባቸው ምክንያቱም ግርግር በተነሳ ቁጥር ይህን ደካማ ቡድን በቀላሉ በመደምሰስ , ለቀሪው ህዝብ የማያሻማ ማስጠንቀቂያ መስጠት ይቻላልና :: 3)ሁለት ጎራወች ሲጣሉ , መሪዎች , ምንጊዜም ጠንካራውን ወግን መደገፍ እንዳለባቸው መክሯል :: ለዚህ ምክንያቱ : ከጥሉ በሁአላ ድሉ የጠንካራው ስለሚሆን , የደካማው ጥላቻ ምንም ለውጥ አያመጣም :: ሁለቱንም አለመደገፍ ግን , የደካማውን ጥላች ሲያተርፍ , የጠንካራውን የድል -አጥቢያ ጡንቻ በራስ ላይ ይጋብዛል :: ይህ ደግሞ ሁለት እጥፍ ኪሳራን ያመጣል ብሏል ::

ከማካቬሊ ጥቅሶች

ለማስተካከል

1. አንድ መሪ የገባውን ቃል ለማጠፍ ምንጊዜም በቂ ምክንያት አለው።

2. ጠቢብ መሪ፣ ከራሱ ጥቅም ጋር ሚቃረንን ነገር ሁሉ እርግፍ አድርጎ መተው ይገባዋል።

3. ከሁሉም በፊት ፣ ትጥቅ ታጠቅ።

4. ሌላውን ሰው ስትጠቅም ቀስ በቀስ ይሁን ምክንያቱም ጣሙን ለብዙ ጊዜ ማጣጣም ይችላሉ እና ። በዚህ ትይዩ ፣ ስትጎዳ ግን በአፋጣኝ ይሁን ።

5. ሀብት ፈጣሪወች በጥሩ እድል እና በእንቅፋት መካከል ያለውን ልዩነት የማይገነዘቡ ናቸው። ቢገነዘቡም እንኳ ፣ እንቅፋቱን ወደ ጥሩ እድል መቀየር የሚችሉ ናቸው ።

6. ጥላቻ (መጠላት)፦ በመጥፎ ስራ ብቻ ሳይሆን የሚመጣው ፣ በጥሩ ስራም ጭምር ነው።

7. ሌላ ሰው እንዲታዘዘው የሚፈልግ ፣ እንዴት ማዘዝ እንዳለበት ማወቅ አለበት ።

8. ሌላን መጉዳት ከተፈለገ ፣ ጉዳቱ ከመጠን ያለፈ መሆን አለበት ምክንያቱም በዚህ መንገድ በቀሉን ሲፈሩ መኖር አያስፈልግም።

9. አታላይን ማታለል ድርብ -እጥፍ ደስታ ነው ።

10. ማዕረግ ሳይሆን ሰውየውን የሚያስከብረው ሰውየው ነው ማዕረግን የሚያስከብረው ።