ማናጓ (Managua) የኒካራጉዋ ዋና ከተማ ነው።

የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 1,390,500 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 1,146,000 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 12°06′ ሰሜን ኬክሮስ እና 86°18′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።

የ'ማናጓ' ስም ከናዋትል 'ማና-አኋክ' ('ውሃ አጠገብ') ተወረሰ። ከጥንት ጀምሮ ኗሪዎቹ ከተማ በሥፍራው ነበራቸው። ዘመናዊ ከተማ በ1811 ዓ.ም. ተመሠርቶ ስሙ 'ሳንቲያጎ (ቅዱስ ያዕቆብ) ዴ ማናጓ' ተባለ። በ1849 ዓ.ም. አሜሪካውያን የቆየውን ዋና ከተማ ግራናዳን ስላጠፉ ያንግዜ ማናጓ እንደ ኒካራጓ አዲስ ዋና ከተማ ተመረጠ።