ማሮን
የኢቫንቴስ ልጅ አፈታሪክ
ማሮን በግሪክ አፈ ታሪክ የማሮኔያ ከተማ መሥራች ነበር። በሆሜር ዘንድ በኦዲሴዎስ ዘመን (12ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ግድም) ተገኘ፤ በዲዮዶሮስ ታሪክ ግን ከዚያ በፊት በኦሲሪስ አፒስ ዘመን (21ኛው ክፍለ ዘመን ዓክልበ. ግድም) የኖረው ሲሆን የአፒስ ሻለቃ ነበር። አፒስ ሊኩርጉስ (የጥራክያ ንጉሥ) ከገደለው በኋላ ለማሮን አደራ አገሩን ከዳኑብ ወንዝ እስከ ደማስቆ ድረስ እንደ ሰጠው ደግሞ ይባላል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |