ዶክተር ሙላቱ ተሾመኢትዮጵያ ፕሬዚዳንት ናቸው።

ሙላቱ ተሾመ
ተሾመ በ 2010
ተሾመ በ 2010
የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት
ከመስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም. ጀምሮ
ጠቅላይ ሚኒስትር ኃይለማሪያም ደሳለኝ
ቀዳሚ ግርማ ወልደ ጊዮርጊስ
ተከታይ ሳህለወርቅ ዘውዴ
የኢትዮጵያ አምባሳደር በቱርክ
ከሚያዝያ ፲፫ ቀን ፲፱፻፺፰ ዓ.ም. እስከ መስከረም ፳፯ ቀን ፳፻፮ ዓ.ም.
ተከታይ አያሌው ጎበዜ
የግብርና ሚኒስትር
ከጥቅምት ፯ ቀን ፲፱፻፺፬ ዓ.ም. እስከ ሰኔ ፳፬ ቀን ፲፱፻፺፭ ዓ.ም.
ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ
ቀዳሚ መንግሥቱ ሁሉካ
ተከታይ አዲሱ ለገሰ
የተወለዱት ፲፱፻፵፱ ዓ.ም.
አርጆኢትዮጵያ
የፖለቲካ ፓርቲ ኦሕዴድ
ዜግነት ኢትዮጵያዊ
ሀይማኖት የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ክርስትና

ሙላቱ ተሾመ ውርቱ በኦሮሚያ ክልል ምስራቅ ወለጋ አርጆ ወረዳ በ1949 ዓ.ም. የተወለዱ ሲሆን የመጀመሪያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምህርታቸውን በአርጆ እና በአዲስ አበባ ተከታትለዋል።

በ1974 ዓ.ም የመጀመሪያ ዲግሪያቸውን በፖለቲካ ኢኮኖሚ ፍልስፍና እንዲሁም በአለም አቀፍ ግንኙነት ከዚያም በፍልሰፍና የዶክቶሬት ድግሪያቸውን።

ዶክተር ሙላቱ ተሾመ የተለያዩ የምርምር ስራዎችን በተለያዩ መስኮች ያከናወኑ እና በመምህርነትም ያገለገሉ ሲሆን ፥ አማርኛ ፣ ኦሮምኛ ፣ እንግሊዘኛ ፣ ቻይንኛ እንዲሁም ፈረንሳይኛ ቋንቋን መናገር እና መጻፍ ይችላሉ።

ከ1993-1994 ዓ.ም የኢፌዴሪ የግብርና ሚኒስትር ፣ ከጥቅምት 1994 እስከ 1998 ዓ.ም በፌደሬሽን ምክር ቤት አፈ ጉባኤነት እንዲሁም ከ1998 ዓ.ም ጀምሮ በቱርክ የኢፌዴሪ ባለሙሉ ስልጣን አምባሳደር ሆነው አገልግለዋል።

ዶክተር ሙላቱ በትዳር ህይወታቸው የአንድ ወንድ ልጅ አባት ናቸው።

ማመዛገቢያEdit

አዲሱ ፕሬዘደንት በብሄራዊ ቤተ መንግስት አቀባበል እየተደረገላቸው