ሳህለወርቅ ዘውዴ
አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የኢትዮጵያ የመጀመርያው ሴት ፕሬዚዳንት ናቸው።[1]
የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት | |
ከጥቅምት ፲፭ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. ጀምሮ እስከ መስከረም ፳፮ ቀን ፳፻፲፯ ዓ.ም. | |
ጠቅላይ ሚኒስትር | ኣብይ ኣህመድ |
---|---|
ቀዳሚ | ሙላቱ ተሾመ |
ተከታይ | ታዬ አፅቀ ሥላሴ |
የተወለዱት | ፲፱፻፵፪ ዓ.ም. አዲስ አበባ፣ ኢትዮጵያ |
ዜግነት | ኢትዮጵያዊ |
ሀይማኖት | የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን |
ይህ መጣጥፍ የውክፔዲያ የአቀማመጥ ልምዶችን እንዲከተል መስተካከል ይፈልጋል። |
የህይወት ታሪክ እና ትምህርት
ለማስተካከልአምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ በወርሃ የካቲት ፲፱፻፵፪ በአዲስ አበባ ከተማ ነው የተወለዱት። አምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ የመጀመርያ እና የሁለተኛ ደረጃ ትምርታቸውን ያጠናቀቁት በሊሴ ገብረማርያም ትምርት ቤት ነው። አምባሳደር ሳህለወርቅ የፈረንሳዩ ሞንተፔለ ዩኒቨርሲቲ የተፈጥሮ ሳይንስ ምሩቅ ናቸው። አማርኛ፣ ፈረንሳይኛ፣ እና እንግሊዘኛ አቀላጥፈው ይናገራሉ አባታቸዉ ዘዉዴ ሰሜን ሽዋ ደራ ጉ/መስቀል ሲሆን ትዉልዳቸዉ እናታቸዉ ከጎጃም ማንኩሳ ምንም የዘርብሄር ድብልቅ ሳይሆኑ ፅድት ያሉ አማራዊት ናቸዉ ኢትዮጵያም ያማራ ነች .....
የስራ ዝርዝር
ለማስተካከልየዲፕሎማት ስራቸው
ለማስተካከልአምባሳደር ሳህለወርቅ ዘውዴ ለኢትዮጵያ እንደ ውጪ አገር አገልግሎት ሰራተኛ ብዙ አመታት አገልግለዋል። እኤአ ከ1989-1993 ተቀማጭነታቸውን ሴነጋል በማድረግ የማሊ፣ የኬፕ ቨርድ፣ የጊኒ ቢሳዎ፣ የጋምቢያና የጊኒ አምባሳደር በመሆን አገልግለዋል። እኤአ ከ1993-2002 ደግሞ በጅቡቲ አምባሳደር ሆነው የሰሩ ሲሆን በወቅቱ የምሥራቅ አፍሪካ የልማት በየነ መንግሥታት ድርጅት (ኢጋድ) ቋሚ ተወካይም ነበሩ።
ከዚያም በመቀጠል እኤአ ከ2002-2006 በፈረንሳይ አምባሳደር እንዲሁም የተባበሩት መንግሥታት የትምህርት የሳይንስና የባህል ተቋም ተወካይ ሆነው ሰርተዋል።
የተባበሩት መንግስታት ስራቸው
ለማስተካከልበተባበሩት መንግሥታት ልዩ መልዕክተኛ ውስጥ የተቀናጀው የሰላም አስከባሪ ሃይል ተወካይ በመሆን በሴንትራል አፍሪካ(BINUCA) ኃላፊ በመሆን አገልግለዋል።
በአፍሪካ ሕብረት ውስጥና በተባበሩት መንግሥታት የኢኮኖሚ ኮሚሽን ውስጥም የኢትዮጵያ ቋሚ ተወካይ ሆነው ያገለገሉት አምባሳደር ሳህለወርቅ በውጪ ጉዳይ ሚኒስቴር ውስጥም የአፍሪካ ጉዳዮች ዳይሬክተር ጄነራል ሆነው ሰርተዋል።
እኤአ በ2011 የተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ የነበሩት ባን ኪሙንም በኬኒያ የተባበሩት መንግሥታት ዳይሬክተር ጄነራል አድርገው ሾመዋቸው አገልግለዋል።
በተባበሩት መንግሥታት ዋና ፀሃፊ አንቶኒዮ ጉቴሬስ በአፍሪካ ሕብረት ልዩ ተወካይ እንዲሁም በአፍሪካ ሕብረት የተባበሩት መንግሥታት ቢሮ ኃላፊ ሆነው ተሾመዋል።
አምባሳደር ሳህለወርቅ ጥቅምት ፩፭ ቀን ፳፻፲፩ ዓ.ም. የኢትዮጵያ ፕሬዝዳንት ሆነው ተመርጡ። በፕሬዝዳንትነት ሚና ለማገልገል የመጀመርያዋ ሴት ሲሆኑ በ ኢፌዴሪ ዘመን አምስተኛ ፕሬዝዳንት ናቸው። በአሁኑ ጊዜ በአፍሪካ ውስጥ አምባሳደር ሳህለወርቅ ብቻ ናቸው ሴት የአገር መሪ። ከሳቸው በፊት አንድ ሌላ ሴት መሪ ኖርዋት ያውቃል፤ እሳቸውም ንግሥት ዘውዲቱ ናቸው።
ማጣቀሻወች
ለማስተካከል- ^ "Ethiopia gets first female president". BBC (25 October 2018).