መርዓዊ ዮሐንስ

ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ

መርዓዊ ዮሐንስ ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ነው።

የህይወት ታሪክ ለማስተካከል

መርዓዊ ዮሐንስ ተወልዶ ያደገው አዲስ አበባ ውስጥ ሲሆን ወደ ሙዚቃ ዓለም የገባው የስምንት ዓመት ልጅ እያለ ነው። ወለጆቹ በትምህርቱ እንዲተጋ በማሰብ በቀድሞው አስፋወሰን ትምህርት ቤት አስገብተውት ነበር። ሆኖም መርዓዊ በዚያን ዘምን ቀደምት የነበሩትን ድምጻውያን በተለይም የጥላሁን ገሠሠን የምኒልክ ወስናቸውንና የግርማ ነጋሽን ድምጽ በሬዲዮ በሚያዳምጥበት ወቅት በስሜት አብሯቸው ይመንን ነበር።

መርዓዊ የአሥር ዓመት ልጅ እያለ በት/ቤቱ ውስጥ የወላጆች ቀን በዓል ይከበራል። በዚያን ቀን ወላጆችና በርካታ እንግዶች በተሰበሰቡበት በነበረው ቃጭል ድምጽ ልዩ ጣዕም ያለው ዜማ ያሰማል። ገና ልጅ ሳለ «አልማዜ» የምትባለውን ዘፈኑን ስለተጫወተ አድናቂዎቹ ሁሉ መርዓዊን «አልማዜ» እያሉ ይጠሩት ነበር።

የሥራዎች ዝርዝር ለማስተካከል

መርዓዊ ከተጫወታቸው ዘፈኖች መካከል በተለይ «በይ ደህና ሁኝ»፣ «እንኰይ እንኰይ»፣ «እንደምን አለሽ እህቴ»፣ «ሁሉ ጉድ አፈላ»፣ «ውቤ ከረሜላ»፣ «ተለየሽኝ»፣ «አንቺን ያዩ ሁሉ» እና «አትንኩብኝ» የተሰኙት ዜማዎቹ ታዋቂ አድርገውት ነበር።

ማጣቀሻ ለማስተካከል