ግርማ ነጋሽ

ኢትዮጵያዊ ዘፋኝ

ግርማ ነጋሽ (፲፱፻፴፮ ዓ.ም.) ታዋቂ ኢትዮጵያዊ ድምፃዊ ነው።

ግርማ ነጋሽ

ግርማ ነጋሽ የተወለደው በ፲፱፻፴፮ ዓ.ም. በአዲስ አበባ ከተማ አራት ኪሎ አካባቢ ሲሆን ያደገው ከፍልውሃ በላይ ፊት በር ከሚባለው ሠፈር ነው።

ግርማ ነጋሽ ወደ ሙዚቃው ዓለም ለመግባት ዋናው ምክንያት የሆነው ሙዚቃን መውደድ ብቻ ሳይሆን ከታዋቂው ጥላሁን ገሠሠ ጋር በአደጉበት አካባቢ በሠፈር ልጅነት መገናኘትና የቅርብ ጓደኛ መሆን ነው። መጀመሪያ በፖሊስ ሠራዊት ከዚያም በብሔራዊ ቲያር በመቀጠር ስምንት ያህል ሙዚቃዎችን ተጫውቷል። ለመጀመሪያ ጊዜ በመድረክ ላይ ይዞ የቀረባቸው ዘፈኖች «የኔ ሃሣብ»ና «ምነው ተለየሽኝ» በመባል የሚታወቁትን ነው። ዜማዎቹ የሌላ ቢሆኑም ለሰሚ ጅሮ ጥሩ ሆነው እንዲደርሱ በእኩሌታ ጥረት ያደረገባቸው በመሆኑ አብዛኞቹን ይወዳቸዋል። የቤተሰብ ሙያውን ባለመውደድ እና በተለያዩ ምክንያቶች የተነሳ ሙዚቃን የወደዳትን ይህል ፈጥኖ ሊታወቅባት ችሏል።

ማጣቀሻ ለማስተካከል