ሎዥባን (lojban) በ1987 እ.ኤ.አ. የተፈጠረ አንድ ሰው ሠራሽ ቋንቋ ነው። ቋንቋው የተፈጠረ በLogical Languages Group (LLG, "ትክክለኛ አሰተሳሰብ ያለው ቋንቋ ቡድን") በሚባል የዋሺንግተን ዲሲ ተቋም ነው። LLG በ1955 እ.ኤ.አ. መጀመርያ የፈጠረ ቋንቋ "ሎግላን" ተባለ። ሎዥባንም ከሎግላን 'ተሻሽሎ የወጣ ቋንቋ' ይባላል። የሎዥባን ስም የተወሰደ ከ'ሎግዢ' (ትክክለኛ አስተሳሰብ) እና 'ባንጉ' (ቋንቋ) ነው።

የሎዥባን ሎጎ

አላማቸው ስዋሰዉ በሰዎችም ሆነ በኮምፕዩተር በቀላል የሚታወቅ የ"ትክክለኛ አስተሣሠብ ቋንቋ" ለመፍጠር ነበር። ሌሎች ሰው ሰራሽ ቋንቋዎች ለምሳሌ ኤስፔራንቶ የተፈጠሩ በተለይ ከአውሮጳ ቋንቋዎች ቃላት በመልቀም ነበር። ሆኖም ሎዥባን "ባሕላዊ ገለልተኝነት" ለማሳየት ሙከራ እያደረገ ነው። ነገር ግን ሎዥባን ከአሥር በላይ የተማሩት ሰዎች ገና ስለሌለው እስካሁን ከድረገጽ በቀር ምንም የተደረጀ ሥነ ጽሑፍ የለውም።

ቃላቱ በኮምፒዩተር የተፈጠሩበት መንገድ ብዙ ተናጋሪዎች ያላቸውን 6ቱ የሰው ልጅ ቋንቋዎች በማነጻጸር ነበር። እነዚህም ቋንቋዎች ቻይነኛህንዲ/ዑርዱእንግሊዝኛእስፓንኛዐረብኛመስኮብኛ ናቸው። ለያንዳንዱ ቃል ስንት ድምጾች በጋራ ከነዚህ ቋንቋዎች ጋራ እንዳለው በኮምፒዩተሩ ተቆጠረ። ስለዚህ ከሁሉም ብዙ ተናጋሪዎች ለቻይነኛ በመኖራቸው ብዙዎች ድምጾች የተለቀሙ ከቻይነኛ ነበር።

የእያንዳንዱ ቃል ሥር በ5 ፊደል ይጻፋል። ለምሳሌ፦

  • prenu (ፕረኑ) = ሰው
  • cukta (ሹክታ) = መጽሐፍ
  • vanju (ቫንዡ) = የወይን ጠጅ

እነዚህ በኮምፒዩተር የተፈጠሩ ቃላት እንደ ሌላ ቋንቋ ባይመስሉም፣ ክፍሎቻቸው ግን ከትልቁ ቋንቋዎች መገኘታቸው ሊታይ ይቻላል። ለምሳሌ በ"ፕረኑ" (ሰው) የእንግሊዝኛ "ፐር-" (per-) ከ"ፐርሶን" (person)፣ እና የቻይንና "ረን" (人) ይታዩበታል። "ሹክታ" ደግሞ የእንግሊዝኛ "-ኡክ" ከ"ቡክ" (book)፣ የቻይንኛ "ሹ" (书)፣ እና የዐረብኛ "ኪታብ" ( كتاب ) ያዋሕዳል። "ቫንዡ" የፈረንሳይኛ "ቫን" (vin) እና የቻይንኛ "ጅዮ" (酒) ይመስላል።

የሎዥባን ስዋሰው እንደ ኮምፕዩተር ቋንቋ ይመስላል።

ምሳሌ ዐረፍተ ነገሮች ለማስተካከል

  • bramau - ብራማው: ይበልጣል።
  • mi bramau do le ka clani - ሚ ብራማው ዶ ለ ካ ሽላኒ: በቁመት ረገድ እኔ ካንተ እበልጣለሁ።
  • le cinfo cu bramau le mlatu - ለ ሺንፎ ሹ ብራማው ለ ምላቱ: አንበሣው ከድመቱ ይበልጣል።
  • mi bramaugau le cinfo le mlatu - ሚ ብራማውጋው ለ ሺንፎ ለ ምላቱ: አንበሣውን ከድመቱ እንዲበልጥ አደርጋለሁ።
 
Wikipedia