ሎክ ዱክ
ሎክ ዱክ በቬትናም አፈ ታሪክ በአሁኑ ስሜን ቬትናም የዙሪያው መጀመርያ መንግሥት «ሢኽ ቊ» መሥራች ነበር። ያንዲ ሚንግ የሎክ ዱክ አባት ተባለ፣ ሎክ ዱክም ከቻይና ወደ ደቡብ ፈልሶ የአገሩ መጀመርያ ንጉሥ «ኪኝ ዲውንጝ ቪውንጝ» ሆነ። ይህም ምናልባት 2387 ዓክልበ. ያህል ይመስላል። በቬትናም ልማዳዊ አቆጣጠር ግን ይህ መንግሥት ከ2887 እስከ 2802 ዓክልበ. ድረስ ቆየ።
ከዚህ መንግሥት በኋላ (2301 ዓክልበ.?) ልጁ ላክ ሎንግ ኳን ንጉሥ ሆኖ የአገሩ ስም ከ«ሢኽ ቊ» ወደ ቫን ላንግ ተቀየረ።