ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 320፦
፲፫. “ው”ን አንጂ “ዉ”ን የሚጠቀሙ ብዙ የዓማርኛ ቃላት የሉም። በቅርቡ ግን በኣለማወቅ በ“ው” ቀለም ምትክ “ዉ”ን በግድፈት የሚጠቀሙ ፀሓፊዎች እየበዙ ነውና ቢታሰብበት ኣይከፋም። [[መዝገበ ቃላት]]ም ጠቃሚዎች ናቸው። ([[እንግሊዝኛ አማርኛ መዝገበ ቃላት 1972]])። “ው”ን በትክክል ከ40 በላይ ቃላት ውስጥ የተጠቀመ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። [http://www.dejeselam.org/2014/03/blog-post_29.html] “ው”ን በስሕተት ከ400 በላይ ቃላት ውስጥ የተጠቀመ ጽሑፍ ምሳሌ እዚህ ኣለ። [https://hornaffairs.com/am/2017/01/24/committed-leadership-corruption/] ፲፬. የግዕዙ “ሀ” ድምጽ ወደ “ኸ” የቀረበ ነው። “አ” እና “ኣ” ድምጽ ኣይጋሩም። [http://www.ethiopic.com/amharic/errors.pdf] [http://web.archive.org/web/20030315142841/] [http://web.archive.org/web/20120111013212/http://www.ethiopic.com/ethiopic_alphabet.htm] [http://dagmawibelete.blogspot.com/2013/05/ethiopic.html] ፲፭. ኣንዳንድ ፀሓፊዎች በነጠላ ሰረዝ (“፣”) ምትክ ኮማ (“,”) (Comma) በኣራት ነጥብ (“።”) ምትክ ፔርየድ (“.”) (Period) መጠቀም ስለጀመሩ ፊደሉንና ቋንቋውን እያበላሿቸው ናቸው። ፲፭. ኣንዳንድ ምሁራን ስለማያስተውሉ ሁሉንም የዓማርኛ ቃላት መክተብ በማይችሉ እየተጠቀሙ የሚያወሩትን መጻፍ ኣይችሉም። የግዕዝ ፊደል ታዋቂነት የኣለ እስፔሊንግ ስሕተት ድምጽን በማስፈር ትክክክለኛ ድምፃዊ ፊደል መሆኑ ነው። ፲፮. ማንኛውንም የግዕዝ ቀለም በሦስት መርገጫዎች መክተብ ጊዜና ጉልበት ማባከን ነው። (Typing any Ethiopic glyph with three keystrokes is a waste of time and effort.) ምክንያቱም የዶክተሩ ኣሠራር እንግሊዝኛውን ከኣጋጠመው ችግር ጭምር ለማላቀቅ እንጂ ለግዕዙ የእንግሊዝኛውን ችግር ለማስተማር ስለኣልሆነ ነው። ፲፯. ኣንድኣንድ ፀሓፊዎች የተሳሳቱ ቅርጾች ያሏቸውን ቀለሞች እየተጠቀሙ ስሕተቶችን እያስፋፉ ናቸው። ለምሳሌ ያህል የ“ኩ” እና የ“ቡ” መቀጠያዎች ኣንድ ዓይነት ኣይደሉም። ኮምፕዩተርና የእጅ ስልክ ላይ የኣሉ ፊደላት የተሳሳቱ ከሆኑ መሳሳቱ ስለማይታወቅ የተሳሳቱ ቀለሞች ተለምደው መቸገርና ማስቸገር ኣይቀርም። እነ “ቋ”፣ “ኋ”፣ “ኳ” እና “ጓ” እራሳቸውን የቻሉ መስመር ላይ የሚያርፉ ቀለሞች እንጂ እነ “ቀ”፣ “ኃ”፣ “ካ” እና “ጋ” ስር በተጋደሙ መስመሮች የሚቀርቡ ኣዳዲስ የታይፕራይተር የእውሸት ፈጠራዎች ተቀጣጥለው እንደ ኣዳዲስ ቀለሞች ማቅረብ ተገቢ ኣይደለም። የ"የ”ን እንዚራን መለየት ለኣቃታቸው ኣንድኣንድ ምሁራን የኣሌሉ ቀለሞችን መልኮች ማስተዋወቅ ኣይበጅም። [http://www.danielkibret.com/2013/11/blog-post_29.html] ስለዚህ የግዕዝን ፊደል ከመለገስ መለየቱ ቢቀድም ሳይሻል ኣይቀርም። ፲፰. መስከረምና ሰፕቴምበር ብዙ ቀናት ይጋራሉ እንጂ ኣንድ ኣይደሉም። መስከረም 1 ሰፕቴምበር 1 ወይም September 1 ኣይደለም። ፲፱. ሁለት ዓመታት ወይም ዓመቶች እንጂ ሁለት ዓመት በማለት መጻፍ ስሕተት ነው። ፳. በግዕዝ ጽሑፍ ውስጥ ኣራት ነጥብና የመሳሰሉት (በቀለማት እንጂ) በባዶ ስፍራ መቀደም የለባቸውም። ምክንያቱም ግዕዝ ከእጅ ጽሑፍና የማተሚያ ቤቶች [https://upload.wikimedia.org/wikipedia/am/e/e3/Tsehai_mesfin.pdf] ኣጠቃቀም ወደ ኮምፕዩተር ሲሻሻል መለ'የት የሚገባቸውን ዶክተሩ ስለኣቀረቡ ነው።
 
፳፩. የግዕዝ ፊደል የኦሮምኛው ፊደል ውስጥ ያለውን የግዕዙን “ዸ” እና ሰባት እንዚራን ቀለሞቹን ያጠቃልላል። ስለዚህ እንደ “በዻዻ” የኣሉትን ቃላት በ“በዳዳ” ወይም “ዻራርቱ"ን በ“ደራርቱ” መክተብ ግድፈት ነው። የኦሮምኛው ፊደል የዶክተሩ ሞዴት፣ ኢትዮወርድ፣ ግዕዝኤዲትና ሌሎች ፕሮግራሞች ውስጥ ቀርበው የሚፈልጓቸው ተጠቅመውባቸዋል። ፳፪. ሁሉንም ቀለማት የሌሉት ወይም የማይከትቡ ዓማርኛ እየተባሉ ሲቀርቡ ኣለተቃውሞ መቀበል ነውር ነው። ምክንያቱም ይህ ለፊደሉና ለሰዋሰው የኣለመጨነቅን ስለሚያሳይ የፀሓፊዎችን ችሎታ ማነስ ስለሚያጋልጥ ነው። ፳፫. ዓማርኛ “መጠጥ” እና “መጠጥ ኣደረገ” የሚለውን በማጥበቅ መለየት ኣይችልም የሚሉ ኣሉ። [http://www.ethiomedia.com/1012pieces/oromiffa_in_geez_part_two.pdf] [https://www.youtube.com/watch?v=spzKJUn-KWY] “መጠጥ” እና “መጠጥ ኣደረገ” ሁለት ትርጕሞች ያሏቸው ቃላት እንጂ በማጥበቅ የሚለዩ ኣይደሉም። ፳፬. በኮምፕዩተር ሁለት ነጥብ “፡” የግዕዝ የባዶ ስፍራን ምልክት ነጥብ በሌለው የባዶ ስፍራ የእንግሊዝኛው ኣጠቃቀም ጋር ደርበው ዓማርኛውን የሚያቀርቡ ኣሉ። ከሁለቱ ዘዴዎች ኣንዱን መምረጥ እንጂ ሁለቱንም መውደድ ኣያዋጣም። ዶክተሩ ሁለት ነጥቦችን ኣለመጠቀም ይመርጣሉ እንጂ ኣማራጮች በማቅረብ የተጠቃሚዎችን ምርጫዎች በመገደብ ኣያምኑም። ሁለት ነጥቦችን መጠቀም ከኣስፈለገ በቃላት መካከል ማስገባት እንጂ ነጥቦችን በባዶ ስፍራዎች መክበብ ኣያስፈልግም። ምክንያቱም ይህ በእጅ ጽሑፍ ዘመን የኣልነበረውን ሁለት ነጥቦች ብቻቸውን ተነጥለው ወደ ኣዲስ መስመር መዞርን በኮምፕዩተር ሊያስከትሉ ስለሚችሉ ነው።
 
፳፭. ኣንዳንድ ሰዎች ዓማርኛ የእራሱ ፊደል የለውም ይላሉ። ዓማርኛ የእራሱ ፊደል (Amharic Alphabet) የኣለው ቋንቋ ነው። [https://en.wikipedia.org/wiki/Ge%27ez_script] የግዕዝም ቋንቋ የእራሱ ፊደል ኣለው። የግዕዝ ቋንቋ ፊደላት የዓማርኛው ውስጥ ሲኖሩ ሁሉም የዓማርኛ ፊደላት የግዕዙ ቋንቋ ፊደላት ውስጥ የሉም። ግዕዝ (Ge'ez) ወይም Ethiopic የተለያዩ ቋንቋዎች የሚጠቀሙበት የፊደሉም ስም ሲሆን ለተለያዩ ቋንቋዎች ተጨማሪ ቀለሞች ተጨምረዋል። ፳፮. የኣማርኛ የታይፕራይተር ፊደል የግዕዝ ፊደል ኣይደለም። የእውሸት (Fake) ወይም የፈጠራ የዓማርኛ ፊደል እንጂ የዓማርኛም ፊደል ኣይደለም። መጽሓፍትም ሲታተሙ የነበሩት በግዕዝ ፊደል በማተሚያ ቤቶች ትክክለኛ ቀለሞች ነበር። መጽሓፍት በብራናም ይሁን ሕዝቡ በእጁ ሲጽፍ የነበረው በግዕዝ ፊደል እንጂ በኣማርኛ ታይፕራይተር ፊደል ኣልነበረም። ኣሁንም ቢሆን በድሮው ዓይነት ወይም ዶክተሩ ኮምፕዩተራይዝ በኣደረጉት መነሻው ይህ ፊደል በሆነው የዩኒኮድ የግዕዝ ፊደል ዓይነት ነው። [http://unicode.org/charts/PDF/U1200.pdf] የታይፕራይተርንና የማተሚያውን ፊደላት የማይለዩና ሁለቱ ኣንድ የሚመስሏቸው ኣሉ። ፳፰. በወልጋዳ፣ የተሳሳቱና ከሲታ ቀለማት ተጽፈው የሚቀርቡ ጽሑፎችና መጻሕፍት እየበዙ ነው። የፊደል መልክ ከኣላማረ ለማንበብም ኣያጓጓም። ጥሩ የግዕዝ ፊደል ብርሃንና ሰላም ማተሚያ ቤት “ነጋሪት ጋዜጣ”ን ሲያትምበት የነበረው ፊደል ነው። ብዙ መጻሕፍትም ታትመውበታል። [https://am.wikipedia.org/wiki/%E1%88%98%E1%8B%B0%E1%89%A5:%E1%8B%A8%E1%8A%A2%E1%89%B5%E1%8B%AE%E1%8C%B5%E1%8B%AB_%E1%8C%B8%E1%88%93%E1%8D%8A%E1%8B%8E%E1%89%BD]