ከ«ክሌስም ስያሜ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «'''ክሌስም ስያሜ''' በሥነ ሕይወት ማለት ማናቸውም የሕያዋን ዝርያ በይፋ በዓለም አቅፍ ሳይንቲስቶ...»
(No difference)

እትም በ20:41, 27 ማርች 2019

ክሌስም ስያሜሥነ ሕይወት ማለት ማናቸውም የሕያዋን ዝርያ በይፋ በዓለም አቅፍ ሳይንቲስቶች በኩል የሚታወቅበት ሮማይስጥ ስም ነው። «ክሌስም» መባሉ እያንዳንዱ ስያሜ ሁለት ክፍሎች ስላሉት ነው። መጀመርያው ክፍል የወገን ስም ሲሆን ሁለተኛው ደግሞ የዝርያው ስም ይሆናል። ለምሳሌ የሰው ልጅ ክሌስም ስያሜ በሮማይስጥ Homo sapiens /ሆሞ ሳፒየንዝ/ ሲሆን፣ መጀመርያው ስም /ሆሞ/ («ሰው») ወገኑ፣ ሁለተኛውም /ሳፒየንዝ/ («ጥበበኛው») ዝርያው ነው። የላም ክሌስም በሮማይስጥ Bos Taurus /ቦስ ታውሩስ/ ሲሆን፣ /ቦስ/ ወገኑ፣ /ታውሩስ/ ዝርያው ነው። ይሄ ዘዴ በስዊድን ሥነ ሕይወት መምህር ካርል ልኔየስ1745 ዓም ተጀመረ።