ከ«ኣበራ ሞላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
መስመር፡ 210፦
ዓፄ ኃይለሥላሴ ሓውልቱን ጣልያኖች ከኣክሱም ሲወስዱትም ከመቃወማቸውም ሌላ ለብዙ ኣሥርት ዓመታት ሓውልቱ እንዲመለስ በሮም የኢትዮጵያ ኣምባሳደሮችና በየተባበሩት መንግሥታት የኢትዮጵያ ወኪሎች ጠይቀዋል። [http://articles.latimes.com/2003/nov/30/world/fg-obelisk30] የኣክሱም ሓውልት ከሮም ወደ ኣክሱም እንዲመለስ በዓፄ ኃይለሥላሴ ዘመን መንግሥት የኢትዮጵያ ምክር ቤት ጠይቆ ነበር።
 
ፕ/ር ፓንክኸርስት የኣክሱም ሓውንትሓውልት ለኢትዮጵያ እንዳልተመለስ ለኣንድ የጣልያን ጋዜጣ በ፲፱፻፹፬ ዓ.ም. የጻፉትን የኣነበቡ ብሩኖ ኢምፔሪያሊ ለኣንድ ጋዜጣ የድጋፍ ደብዳቤ ጻፉ። የተጻፈውን የኣነበቡ ቪንሴንዞ ፍራንካቪግሊያ፣ ጁይሴፔ ኢንፍራንካ እና ኣልበርቶ ሮሲ የተባሉ ምሁራን ሓውልቱ እንዲመለስ ለጣልያን መንግሥት ደብዳቤ ከጻፉ በኋላ ፕሮፌሰሩም ይኸን ድጋፍ እንደሰሙ ኢትዮጵያውያን ፊርማ እንዲያሰባስቡ ጠየቁ። በእዚህም በመተባበር ከ500 ፊርማዎች በላይ በማሰባሰብ ከተሳተፉት መካከል [[ኣሰፋ ገብረማርያም]]፣ ልጅ [[ሚካኤል ዕምሩ]]፣ [[ሺፈራው በቀለ]]፣ ክሎውድ ሰምነር፣ ደኒስ ጀራርድ፣ ፕሮፌሰር [[መስፍር ወልደማርያም]]፣ ክቡር ደጃዝማች [[ዘውዴ ገብረሥላሴ]]፣ [[ፀጋዬ ገብረመድኅን]]፣ [[ተክለጻዲቅ መኩሪያ]]፣ [[ተፈራ ደግፌ]]፣ [[ፍቅሬ ቶሎሳ]]፣ ፕሮፌሰር [[ኣቻምየለህ ደበላ]]፣ ፕሮፌሰር [[ኣሸናፊ ከበደ]]፣ [[ካሳሁን ቸኮል]]፣ ሃሪ ችሃብራና [[ራስተፈሪያን]] ነበሩበት። በዓመቱም ፕሮፌሰሩን የጨመረ ፲ ሰዎች የኣሉት የእስመላሽ ኮሚቴ ተቋቋመ። ፕ/ር ፓንክኸርስት ስለ ጉዳዩ ካነሱበትና ሌሎችም በእየጊዜው ሲጽፉ ሓውልቱን ለማስመለስ ከ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ጀምሮ የኣምስት ዓመታት የኣስተዋጽዖ ዝርዝር ውስጥ የሚከተሉት ኣሉበት። [http://www.linkethiopia.org/guide-to-ethiopia/the-pankhurst-history-library/the-question-of-the-looted-and-still-not-returned-aksum-obelisk/] [http://www.linkethiopia.org/guide-to-ethiopia/the-pankhurst-history-library/the-unfinished-history-of-the-aksum-obelisk-return-struggle-4-the-stadium-demonstration-and-the-petitioning-of-international-scholars/] የ[[ኣዲስ ኣበባ ምክር ቤት]]፣ [http://www.unesco.org/culture/laws/pdf/abstract_hailemariam.pdf] የ[[ኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ]] ተማሪዎች የጥያቄ ፊርማ፣ ፕ/ር [[እስቲቨን ሩበንሰን]]፣ ፕ/ር ደኒስ ማክ እስሚዝ፣ ኣቡነ [[ጳውሎስ ፭ተኛ]]፣ ዶ/ር [[ሳሊም ኣህመድ]] ሳሊም፣ ፕ/ር ፓስካል ጄ. ኢምፐራቶ፣ ፕ/ር ፍረደሪክ ጋምስት፣ ፕ/ር ኖርማ ኮምራዳ፣ ራጌሽዋር ሲንግ፣ ባማን ኣሊፍ፣ ዶ/ር ነቪል እስሚዝ፣ ሲይልቭያ ኤይሊንግ፣ [[ግለንዳ ጃክሰን]]፣ ኣቶ [[ገብሩ ኣሥራት]]፣ ፊታውራሪ [[ኣመዴ ለማ]]፣ ፊታውራሪ [[ኣበባየሁ ኣድማስ]]፣ ቀኛዝማች [[ቢያዝን ወንድወሰን]]፣ ሻምበል [[ምሩጽ ይፍጠር]]፣ ሻለቃ [[ዻራርቱ ቱሉ]]፣ ዶ/ር [[ፈቃዱ ገዳሙ]]፣ [[ልዑልሥላሌ ተማሙ]]፣ ኢንጂነር [[ታደለ ብጡል]]፣ [[ተስፋዬ ዘለለው[[፣ ሚስስ ዊንዞፕ ቦዝወል፣ [[ኣንጀሎ ደል ቦካ]]፣ ዶናልድ ክረሜይ፣ [[ጆን እስፔንሰር]]፣ ዴቪድ በክስተን፣ ኣልበርቶ እስባክቺ፣ [[ሰይድ ሳማታር]]፣ ቪራጅ ጉፕታ፣ ፕ/ር [[ሃጋይ አርሊች]]፣ [[ሪቻርድ ግሪንፊልድ]]፣ ፒተር ጋረትሰን፣ ዩሪ ኮቢስቻኖቭ፣ ማርያ ራይት፣ ካትሱዮሺ ፋኩይ፣ ጃክ ጎትሌ፣ ፕ/ር ኢማኑኤል ሴሚ፣ ሮጀር ሽናይደር፣ ፕ/ር ክሪስቶፈር ክላፋም፣ ፕ/ር ፍረድሪክ ሃሊደይ፣ ፖውል ብሪትዝኪ፣ [[ኣሊ ማዝሩይ]]፣ ቶማስ ፓከንሃም፣ ኮህን ለጉም፣ ኬረን ዳልተን፣ ሆዜ ጃፊ፣ ፕ/ር ዊሊያም ዲያኪን፣ ዶ/ር ኪርስተን ፒደርሰን፣ ካትርይን ባርድ፣ ዶ/ር ረይደልፍ ሞልቬር፣ ኣይቫን ኣድለር፣ [[ዊልፍረድ ተሲገር]]፣ [[ግራሃም ሃንኮክ]]፣ ሰር በርናርድ ብሬይን፣ ሉትዝ ቤከር፣ ሮደሪክ ግሪየርሰን፣ [[ሪታ ማርሌይ]]፣ ጀርሜን ግሪር፣ ሲሮ ታደኦ፣ [[ኒኮላ ደማርኮ]]፣ ፕ/ር [[ኤፍሬም ይስሃቅ]]፣ ፕ/ር [[ሥዩም ገብረእግዚኣብሔር]]፣ ፕ/ር [[ኣቻምየለህ ደበላ]]፣ ዶ/ር [[ጌታቸው ኃይሌ]]፣ ፕ/ር [[ኣሸናፊ ከበደ]]፣ ዶ/ር [[ካሳሁን ቸኮል]]፣ ዶ/ር [[ኣስፋወሰን ኣስራቴ]]፣ ልጅ [[ዘውዴ ኃይለማርያም]]፣ ኣቶ [[ሳሙኤል ፈረንጅ]]፣ ሪቻርድ ባልፍ፣ ሃሪ ካህን፣ ዶ/ር [[ካሳይ በጋሻው]]፣ [[ሪታ ፓንክኸርስት]]፣ ክቡር [[ደጃዝማች ዘውዴ ገብረሥላሴ]]፣ ኣርቲስት [[ኣፈወርቅ ተክሌ]]፣ ሎሬት [[ጸጋዬ ገብረመድኅን]]፣ ሴጉን ኦሉሶላ እና [[የኢትዮጵያ እግር ኳስ ፌደሬሽን]] ይገኙበታል። [https://richardpankhurst.wordpress.com/]
 
ሰለ ሓውልቱ ጉዳይ በየጊዜው በመጻፍ ከተራዱትም ውስጥ “[[ኢትዮፒያን ሪቪው]]” ([[ኤልያስ ክፍሌ]])፣ “[[ኢትዮፕያን ሬጂስተር]]” ([[ግርማ በቀለ]])፣ “[[ኢትዮፕያን ኮመንቴተር]]”፣ “[[ኣዲስ ትሪብዩን]]” እና “[[ቤዛ]]” ተጠቅሰዋል። ሓውልቱ እንዲመለስ እስከ ፲፱፻፺ ዓ.ም. እንቅስቃሴውን በመቀጠል ከተዘረዘሩት መካከል የሚከተሉት ኣሉበት። [http://www.linkethiopia.org/guide-to-ethiopia/the-pankhurst-history-library/the-unfinished-history-of-the-aksum-obelisk-return-struggle-5-the-ethiopian-parliament-and-the-people-speak-out/] [[የኣክሱም ሓውልት ኣስመላሽ ኮሚቴ]]፣ የኢትዮጵያ መንግሥትና [[ሕዝብ]]፣ ኣቶ [[ኃብተኣብ ባይሩ]]፣ ፕ/ር [[ሳሙኤል ኣሰፋ]]፣ ኣቶ [[ዳዊት ዮሓንስ]]፣ [[የኢትዮጵያ ፓርላማ]]፣ ፕ/ር [[ባሕሩ ዘውዴ]]፣ ማርኮ ቪጎኒ፣ የትግራይ ክልል ፓርላማ፣ ቶኒ ሂኬይ፣ [[ናፍታለም ኪሮስ]]፣ እስቲፈን ቤል፣ [[ኣልበርቶ ኢምፔሪያሊ]]፣ የሮም ኢትዮጵያውን፣ [[ጃራ ኃይለማርያም]]፣ ክቡር ኣቶ [[ወልደሚካኤል ጫሙ]]፣ ክቡር ኣቶ [[ሥዩም መስፍን]]፣ ፕ/ር ፍራንካቪግሊያ፣ [[በላይ ግደይ]]፣ ዶ/ር [[ተቀዳ ዓለሙ]]፣ ፕ/ር [[እንድርያስ እሸቴ]] [http://hoth.ncat.edu/~michael/AAU-Network/news/obelisk/obeliskpetition.html] [http://hoth.ncat.edu/~michael/AAU-Network/news/obelisk/obelisca.html]፣ ፕ/ር [[ኣበበ ከበደ]] [http://hoth.ncat.edu/~michael/AAU-Network/news/obelisk/] [https://www.facebook.com/abkebede/videos/vb.1575923807/10210965986177057/?type=2&theater] ፣ ክቡር ኣቶ [[ተሾመ ቶጋ]]፣ ጆርጅዮ ክሮቺ፣ የታዋቂ ኢትዮጵያውያን ፊርማ፣ ፲፬ሺህ ፊርማ የፈረሙ የኣክሱም ሕዝቦችና ብዙ ሺህ ፊርማ ያለው በዓለም ላይ ያሉ ኢትዮጵያውያና ሌሎች የጥያቄ ፊርማ (ፔቲሽን)፣ የጥቂት ኣፍሪቃ ኣገሮች ኣምባሳደሮች ደብዳቤዎችና ሌሎችንም ጠቅሷል። ስለ ፊርማውም በማሰማት የ[[ቢቢሲ]] ሬድዮና ቴሌቪዥን፣ የ[[ካናዳ]] ሬድዮ፣ የ[[እንንግሊዝ]]፣ የጣልያንና ኣንዳንድ የዓለም ጋዜጣዎች ትኩረት በመስጠት ረድተዋል። ኣንድ ቪድዮም ተሠርቶ ነበር። ለእዚህ ጉዳይ ከተረባረቡት መካከልም [[ብርሃኑ ተሰማ]]፣ [[ልዑልስገድ ተማሞ]]፣ [[ቢያዝን ወንድወሰን]]፣ [[ኣበባየሁ ኣዳማ]]፣ [[ኣፍሮሜት]] (AFROMET)፣ [[ኣሉላ ፓንክኸርስት]]፣ ታጋስ ኪንግ፣ ቶኒ ሂኪ፣ ሬናቶ ኢምፔሪያሊ፣ ጌይል ዋርደን እና [[ኣንድሩ ሎውረንስ]] ነበሩ። እዚህ የቀረበው በስም የተጠቀሱትን ብቻ ስለሆነ ወደፊት ማሟላትና ስለ እየኣንድኣንዳቸውም በስማቸው መጻፍ ይቻላል። ከእዚህ ሁሉ ድካም በኋላ ጣልያኖች ሓውልቱን እንደሚመልሱ ቃል ገብተው በ፲፱፻፺ ዓ.ም. ይመለሳል ተብሎ (ኢትዮጵያም ፕሮፌሰር ፓንክኸርስት የኣሉበት [[የኣክሱም ሓውልት ኣስመላሽ ኮሚቴ]] በ፲፱፻፹፭ ዓ.ም. ተቋቁሞም ስለነበረ (በ1988 ዓ.ም. ከጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት በተጻፈ ደብዳቤ ለማስታወቂያና ባህል ሚኒስቴር ሐውልቱን ለማስመለስ የሚረዳ ብሔራዊ ኣስተባባሪ ኣካል እንዲቋቋም በተጠየቀው መሠረት፣ ሓውልት ኣስመላሽ ብሔራዊ ኮሚቴም ተቋቁሞ ነበር።) [http://www.elginism.com/similar-cases/axum-obelisk-re-erection-discussed-with-unesco/20050728/178/] ) የጣልያን [[ፕሬዚደንት]] ኢትዮጵያን ሲጎበኙ ይቅርታ ከጠየቁም በኋላ የመመለሱ ጉዳዩ በወሬ ቀረ። [http://ethiopiaonline.net/obelisk/tribune/11-07-97.html] [http://ethiopiaonline.net/obelisk/] [http://ethiopiaonline.net/obelisk/nationalcommittee/191200.html] [http://lubbockonline.com/stories/122698/LA0527.shtml] [http://zoomata.com/archive/italians-protest-return-of-axum-obelisk/#comments] [http://lists.peacelink.it/africa/msg02263.htm] ይህ የኢትዮጵያና የጣልያን ጠቅላይ ሚኒስትሮች ስለ ሓውልቱ መመለስ ከተፈራረሙና [[ቴምብር]] ሁሉ ከተሠራ በኋላ ነበር። በመጨረሻም በዶ/ር [[ኣበበ ከበደ]] የኣዲስ ኣበባ ዩኒቨርሲቲ የቀድሞ ተማሪዎች ኔትወርክ [http://hoth.ncat.edu/~michael/AAU-Network/news/obelisk/] [http://hoth.ncat.edu/~michael/AAU-Network/] በኩል ለጣልያን ጠቅላይ ሚኒስቴር በእንግሊዝኛና ጣልያንኛ የተጻፈው የልመና ደብዳቤ (14 June 2001) መልስ ሳያገኝ ቆይቶ በዓመቱ ግድም ሓውልቱን መብረቅ መታው። ሓውልቱን መብረቅ ሳይመታው ከስድስት ወራት ቀደም ብሎ የኢትዮጵያው ጠቅላይ ሚኒስርት ለጣልያኑ ኣቻቸው በነበሩት ውለታዎች መሠረት ሓውልቱ እንዲመለስ ደብዳቤ ጽፈው መልስ እንኳን ተነፈጋቸው።