ከ«ራዲዮ ስቱዲዮ 54 ኔትወርክ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት
አዲስ ገጽ ፈጠረ፦ «280px|thumbnail|የራዲዮ ስቱዲዮ 54 ኔትወርክ ምልክት '''ራዲዮ ስቱዲዮ 54 ኔትወ...» |
(No difference)
|
እትም በ18:50, 21 ጁን 2015
ራዲዮ ስቱዲዮ 54 ኔትወርክ የግል ራዲዮ ጣቢያ በሎክሪ፣ ካላብሪያ፣ ጣልያን አገር ነው። የጣቢያው ማሠራጨት ዙሪያ እስከ ፱ ደቡባዊ ክፋልገሮች ድረስ ይደርሳል፤ እነርሱም መሢና፣ ረጆ ካላብሪያ፣ ቪቦ ቫሌንቲያ፣ ካታንዛሮ፣ ኮሰንዛ፣ ክሮቶኔ፣ ለቼ፣ ፖተንዛ፣ እና ሳሌርኖ ናቸው። በጣቢያው ላይ ዘመናዊ ሙዚዋ ዘፈኖችና በየቀኑ 28 ጊዜ የዜና መረጃ ይሠጣል።
ስቱዲዮ 54 ኔትዎርክ የተመሠረተው በ6 June 1985 እ.ኤ.አ. በመሥራቾች ፔትሮ ፓሬታ፣ ፍራንቼስኮ ማሣራ፣ ኤንዞ ጋቶ፣ መሞ ሚኒቲ፣ እና ፔትሮ ሙስሜቺ ሲሆን ስሙ «ራዲዮ ዲጄ ክለብ ስቱዲዮ 54» ተብሎ ነበር። እንደ ሌሎቹ ነፃ ጣልያናዊ ራዲዮ ጣቢያዎች፣ ይህ እንደ ጨዋታ ትርዒት ጀመረ። በ1990 እ.ኤ.አ. በጣልያናዊ ሕግ ሥር ይህም የጨዋታ ትርዒት በይፋ ድርጅት ሆነ፣ በዚህም የጣቢያው ፕሮፌሽናሉ መልክ ተጨመረ።
በ1991 እ.ኤ.አ. ደግሞ ከሁሉ ካላብሪያ መጀመርያው ራዲዮ ዳታ ሲስተም የሚባል ሲስተም የሚጠቅመው ራዲዮ ጣቢያ ሆነች። ይህም ከጣልያን ሁሉ ከፊተኞቹ መካከል ነው። በ1994 እ.ኤ.አ. ማሠራጨቱ በኮምፒውተር በዲጂታል አማካኝነት እንዲሆን በቃ፤ ከበፊቱም ማሠራጨቱ ጥረትና ፍትነት አገኘ። ከ1995 እ.ኤ.አ. ጀምሮ ሌሎች የካላብሪያ ራዲዮ ጣቢያዎች በክፍያ በመግዛቱ፣ ማሰራጨቱ የሚደርስበት ርቀት ተጨመረ። በ1997 እ.ኤ.አ. እንደገና ከጣልያን ፊተኞች መካከል ሲሆን፣ የዌብካስቲንግ ችሎታ በሪል ኦዲዮ ሶፍትዌር ጀመረ።
በ1998 እ.ኤ.አ. ስሙ «ስቱዲዮ 54 ኔትወርክ» ሆነ፤ በተጨማሪ ከ2000 እ.ኤ.አ. ጀምሮ «ስታርጌት» የተባለው ተዛዋሪ ስቱዲዮ በመሥራቱ፣ ማሠራጨት ከአደባባይ ሕዝብ በቀጥታ ተቻለ።