ከ«መቅደላ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
Robot-assisted disambiguation: እንግሊዝ - Changed link(s) to ዩናይትድ ኪንግደም
መስመር፡ 27፦
በንጉሠ ነገሥቱ የፖለቲካ ሥልጣን መባቻ ለሰባት ወራት የተካሄደው የ[[ወሎ]] ዘመቻ የተጠናቀቀውም በመቅደላ መያዝ ነበር፡፡ [[ዓፄ ቴዎድሮስ]] ከ[[ጎንደር]] በኋላ የሥልጣን ማእከላቸውን ለጊዜው ወደ [[ደብረ ታቦር]] ከዚያም ወደመቅደላ በማዞር ለተቀረው ግዛት ዓርዓያ ሊሆን የሚችል የአስተዳደር ሥርዓት ለማቆም ጥረት የጀመሩት በዚሁ ሥፍራ ነበር፡፡ በርካታና የተለያዩ የጦር መሣሪያዎች፣ ብዛት ያላቸው ገድሎች፣ መጻሕፍትና ድርሳናት እንዲሁም የንጉሠ ነገሥቱ የግል የክብር ዕቃዎች በሥርዓት ተሰድረው ይቀመጡ የነበረው በመቅደላ ግምጃ ቤት ነበር።
 
በዘመኑ ፲፭ መድፎች፣ ፯ ሞርታሮች፣ ፲፩ ሺ ፷፫ የተለያዩ ጠመንጃዎች፣ ፰፻፸፭ ሽጉጦችና ፬፻፹፩ ሳንጃዎች፣ ፭፻፶፭ የመድፍና የሞርታር አረሮች እንዲሁም ፹፫ ሺ ፭፻፷፫ የተለያዩ ጥይቶች በመቅደላው ግምጃ ቤት እንደነበሩ መረጃዎች ይገልፃሉ፡፡ በአሁኑ ጊዜ ግን ለታሪክ መዘክርነት በቦታው ከሚገኙት ቅርሶች አንዱ ‘ሴባስቶፖል’ የተባለው የንጉሠ ነገሥቱ ትልቅ መድፍ እና [[ዓፄ ቴዎድሮስ]] ጊዜያዊ ቤተ መንግሥት ፍርስራሽና የመቃብር ቦታዎች ናቸው፡፡ መጽሐፍቱ፣ ድርሳናቱ፣ የወርቅና ብር ዋንጫዎች፣ አክሊሎችና ሌሎች የንጉሠ ነገሥቱ የግል ሀብቶች የነበሩ ቅርሶች ሁሉ ከመቅደላው ጦርነትና ከ[[ዓፄ ቴዎድሮስ]] እረፍት በኋላ በደላንታ ሜዳ ለጨረታ ተሰጥተው በ ናፒዬር የተመራው የ[[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]] ሠራዊት ተቀራምቷቸዋል፡፡ በአሁኑ ጊዜም ከንጉሠ ነገሥቱ አናት ላይ የተሸለተውን ሹሩባ ፀጉር ጨምሮ ሌሎች ቅርሶች በ[[ዩናይትድ ኪንግደም|እንግሊዝ]] አገር የተለያዩ የሥነ-ቅርስ መዘክሮች ውስጥ ተቀምጠው ይገኛሉ።
 
ከዓርዓያዊ የአስተዳደር ማዕከልነትና ግምጃ ቤትነት ባሻገር የንጉሠ ነገሥቱ ወህኒ ቤትም የሚገኘው በመቅደላ ነበር፡፡ በእጅ ተይዘው በሞት ያልተቀጡ ጠንካራ የሥልጣን ተቀናቃኞች፣ ምርኮኞችና አማጽያን ከመቅደላ ነዋሪዎች ጥቂቶቹ ነበሩ። ከእነዚህም አንዱ የኋላው ንጉሠ ነገሥት የያኔው [[ደጃዝማች]] [[ዳግማዊ ምኒልክ|ምኒሊክ]] ናቸው። ምኒልክ ለ አሥራ አንድ ዓመታት የመቅደላ እስረኛ ነበሩ። አጼ ቴዎድሮስ ከእንግሊዝ መንግሥት ጋር በነበራቸው ጠብ እልህ ውስጥ ገብተው በጎንደር ይኖሩ የነበሩ የውጭ ዜጎችን ሰብስበው ያጎሩት በመቅደላው ወህኒ ቤት ነበር፡፡ በመጨረሻም የመቅደላ አምባ የአጼ ቴዎድሮስ ሥልጣን መደላደል ምልክት የመሆኑን ያህል የፍጻሜያቸውም ተምሳሌት ሆኗል።