ከ«ውክፔዲያ ውይይት:የአርዕስትና የስም አጻጻፍ ልምድ» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 43፦
== ስለ ሀ እና አ ==
 
በኣማርኛ የ"ሀ" እና የ"ሃ" እንዲሁም የ"አ" እና የ"ኣ" ድምጾች ኣንድ የሆኑት በስህተት ይመስላል። የ"ሀ" ድምጽ ኣሁን በስህተት ለ"ኸ" ብቻ የምንጠቀመው፣ እንዲሁም የ"አ" ድምጽ ኣሁን በስህተት ለ"ኧ" የምንጠቀመው ነው የምንል ኣለን። ተሳስተናል?
 
````
አዎን! ተሳስታችኋል።
ተሳስታችኋል ሰልም፣ በቀላሉ መልስ የሚያሰጥም ጥያቄ ነው ማለትም አይደለም። እንደነገሩ፣ አንዳንድ ጥያቄዎች በቀጣዩ መልስን ከመጋበዝ ይልቅ፣ እራሳቸው ደግመው ጥያቄ የማስነሳት ባህራይ አላቸው። “ተሳስተናል፧” ጥያቄ ከሚያጨርሩት ወገን ነውና፣ የሚከተሉትን ጥያቄዎች እንመልከት።
 
፩ኛ/ የአማርኛ ቋንቋ የበላይ ጠባቂው ማን ነው፧ ስርአትና ደንብ የማውጣት እና(ያለ ወይም ካለ ግዴታ) በጠቃሚ መልኩ፣ ልምዱ ተቀላጥፎ ልምዱን እስከ ወዲያኛው የሚያዘልቀው፣ በድጋሚ ማን ነው፧
፪ኛ/ አማርኛ ቋንቋው፣ ከጅምሩ የራሱን የፊደል ገበታ እስካልፈጠረ ወይም እሰከሌለው ድረስ፣ በተውሶ የሚጠቀምበት የግእዝ ፊደላት፣ ሙሉ ስፌት( ልክክ) ብሎለታል ወይ፧ ግእዝ ቋንቋ እራሱስ፣ የግዕዝን የፊደል ገበታውን የተዋሰስ ከሆነስ፧ የቅጅ ቅጅ ሊሆን አይችልም ወይ፧
፫ኛ/ ለመሆን ለስንት መቶ አመታት ያህል በግእዝ (በግዕዝ) ሆሄያት ተጠቅመናል፧ (?) ለአማርኛ ቋንቋ። ፊደላቱ የአማርኛን ቋንቋን እንደራሱ ማለት እንደ ቋንቋው ባህርይ አጢኖ ገበተናወም ለዚሁ ጉዳይ ታስቦና እንዲጠቅም ተደርጎ የተሰራበት ዶሴ አለ ወይ፧
 
ከላይ የተጠቀሱት ጥያቄቶች ከሞላ ጎደሉ ነው። ጥያቄዎቹም ለእናንተ ጥያቄ የመነሳት ምክንያት የሚሰተዋሉበትን ጥያቄዎች ናቸው።+
 
ችግሩ ከዋናው ከመሰረቱ ነው። ስለሆነም፣ ስህታችሁ በሀገር የመጣ ሲሆን፣ በቀላሉ ተሳስታችኋል ሊባል ይቻልም። እንዲያውም ችግሩንም እንደመጠቆም ወደ መህትሄውንም እንደመስጠት ሞክራችኋል ትክክል ባይሆንም¡ ወደ ቀናው መንገድ ግን ይመራናል። እኔም ለመጻፍ በቃሁ። ሌላውም የራሱን ይላል። ወደ ምንስማማበት ሰፈር እንደርሳለን።
 
የንግግርና የጽሁፍ አግባባቸው የተለያዩ የሚሆንበት አጋጣሚ አለ። ይህ አጋጣሚ ግን፣ ያልተስተዋለ ለውጥ ማምጣት የለበትም(ሀ፣ሃ ወይም አ፣ኣ)። ድምፅ የመመሳሰል ባህሪይ ሲኖረው ሆሄያት ግን የላቸውም፣ ምክንያቱን ድምጹን እንዲወክል ተብሎ ከጅምሩ ስለተቀረጸ ለይቶ ሊያስቀምጣቸው የግድ ይላል። ካልሆነ ግን አልተሟላም ለማለት ይቻላል። በተለይ የአማርኛ ቋንቋ እና የግእዝ ሆሄያት ትብብር የድምፅን መመሳሰልን፣ በፅሁፍ ወቅት ልዩነቱን በግልጽ የማሳየት አቅማቸው የላቀ ነው። እንዴት፧
 
አ ለሚለው ግዕዝ፣ ሰባት ተጨማሪ የድምዕ አከሎበት፣ የአን ጓድ ብቻ ሰምንት የተለያያ ድምፅ ወካይ (ሆሄ) በመስጠት። አ የሚባለው ግእዝ ይጠናቀቃል። አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ።
 
አ ኡ ኢ ኣ ኤ እ ኦ ኧ
በ ቡ ቢ ባ ቤ ብ ቦ ቧ
ሀ ሁ ሂ ሃ ሄ ህ ሆ ሇ
ረ ሩ ሪ ራ ሬ ር ሮ ሯ
 
አሁን ሰህተቱን በምሳሌ ለማስረዳት እሞክራሁ።
አበበ፡ አበበ የሚለው ንባብ እንመልከት።
አ፥ በዚህ ንባብ ውስጥ እራሱ አን የሚለውን ሆሄ ወክሎ ነው የሚሰራው። አ የሚለው ግዕዝ-ሆሄ፣ የቃሉን ትርጉም ይለውጣል። መጣ፣ ለሚለውው ንባብ፣ አ ከተጨመረበረት ትርጉምን ይቀይራል ማለት ነው። አመጣ
በ፥ በዚህ ንባብ ውስጥ እራሱን በመድገም ነው የገባው። ይህ ደግሞ ለቃሉ አንዳይነት ባህርይ ያጎናጽፈዋል። አዝግሞ የሚለወጥ ነገርን ይጠቁማል። የቃሉን ትርጉም ባናውቀውም እንኳን፣ ባህርዩን እንድናስረውል ያደርገናል።
በ፥ በዚህ ንባብ ውስጥ እራሱን የደገመው በ፣ ለቃሉ የሚሰጠው ባህርይ በምሳሌ እንመልከት። ደበበ፣ መዘዘ፣ ለዘዘ፣ በረረ…። ልብ ይበሉ በዚህ ጉዳይ ላይ የሚደገመው የመጨረሻው አንድ ሆሄ ብቻ ነው። ሁለቱም የሚደጋገሙበት ግዜ አለ። ፈተፈተ፣ ከተከተ፣ ለመለመ፣ ወዘወዘ…
አበባ፥ የሚለውን ስንመለከት ደግሞ በ፣ እረሱን ደግሞና አን፣ አስከትሎ ነው ወይስ የራሱን ራብዕ-በን፣ ተጠቅሞ ነው። አበበአ ወይስ አበባ። ብዙ የትርጉም ልዩነት ሳያመጣ የቃሉን ባህሪይ ቀየር ያደርገዋል።
ባ፥ የቃሉን ባህሪይ ሲገልጸው፣(አ ከፊታቸው ያሰለፉና ወይም ማንኛው በራብዕ ረድፍ ላይ ያለ ሆሄ) የድርጊትን መደረግንና ድርጊቱም የመቀጠል ባህርይ እንዳለው ይናገራል። ለነገሩ ባለ አንድ ፊደል ባለ ሁለት ፊደል ባለሶስት ፊደል
ቃላት የየራሳቸው የሆነውን ባህርይ ይገልጻሉ። ይህ ደግሞ አማርኛን ያልቀዋል። ገባ፣ ወጣ፣ ገዛ፣ ለዛ፣ ገበጣ፣ ሾጣጣ፣ ለማጣ… ድርጊቱ ያለና የሚቀጥል መሆኑን ያሳያል።
 
ሰለዚህ እንደ ኣ እና ሃ ያሉት ሆሄያት በተገቢ ቦታቻው ላይ ከተቀመጡ፣ ማለት በራብዕ ጎራ ላይ የባህርዩን ይጎናጸፋሉ ማለት ነው።
እና በረሀ ብለን ብንጽፍ ወይስ በረሃ ብለን ብንጽፍ የተሻለ ነው፧ ሃ፣ የመሞቅና ጉዳዩም የመቀጠሉን ነገር ስለሚያስረተውል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም።
ተሳስታችዃል የተሻለ ሳይሆን አይቀርም ብዬ የደመከምኩልህ፣ ስህተቱ ከላይ ከ ፩ እስከ ፫ የተጠቀሱት ላይ በመሆኑ ነው።
Return to the project page "የአርዕስትና የስም አጻጻፍ ልምድ".