ከ«የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን» ለውጦች መካከል ያለው ልዩነት

Content deleted Content added
No edit summary
መስመር፡ 22፦
 
በ[[1500]] ዓ.ም. ደግሞ ኢትዮጵያ ከ[[አዳል]] ጋር ስትታገል ማቴዎስ የተባለ አንድ አርሜናዊ ወደ [[ፖርቱጋል]] ተልኮ የፖርቱጋል ንጉሥ እርዳታ ለመነ። ስለዚህ በ[[1512]] ዓ.ም. የፖርቱጋል ሚሲዮን በኢትዮጵያ ደረሰ። በሚከተለው ክፍለ ዘመን ከፖርቱጋል [[ኢየሱሳውያን]] የተባሉ ሚሲዮኖች ቤተ መንግሥቱን ወደ [[ሮማ ካቶሊክ]] ሃይማኖት ለማዞር ብዙ ጣሩ። በመጨረሻ በ[[1617]] ዓ.ም. ንጉሥ [[ሱስንዮስ]] ወደ ሮማ ካቶሊክ እምነት ተቀየሩ። ዳሩ ግን የሮማ ሃይማኖት በተዋህዶ ፈንታ ይፋዊ መሆኑን ሕዝቡ በጣም አልወደደምና በ[[1625]] ሱስንዮስ ዘውዳቸውን ለልጃቸው ለ[[ፋሲለደስ]] እንዲሰጡ ተደረጉ። ፋሲለደስ ወዲያው አገሩን ወደ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን መለሱ። ከዚህ በላይ በ[[1626]] ፋሲለደስ ኢየሱሳውያን አገሩን ለቅቀው እንዲሄዱ አዘዙ። በ[[1658]] ዓ.ም. መጻሕፍታቸውን ደግሞ አስቃጠሉ።
 
== በቅርብ ጊዜ ==
{{wikify}}
ቃለ ውግዘት።
 
«ዛሬ ካለው የቤተ ክርስቲያን አመራር ጋራ ወደ ትግል ሰልፍ እንድገባ ያደረገኝ የኔ ፈቃድ፥ ዐቅምም አይደለም። በ[[1985|፲፱፻፹፭]] ዓመተ ምሕረት [[ሐምሌ ፭]] ቀን ኦፕራሲዮን ሆኜ በሰመመን ውስጥ በነበርኩበት ጊዜ በሥርዓተ ሙታን ወደ አምላኬ ፊት ቀርቤ የተሰጠኝ ትእዛዝ ነው። በዚያች ሰዓት፤ ከ[[ቅዱስ ማርቆስ]] እስከ [[ሳድሳዊ ቄርሎስ]] የነበሩ [[የእስክንድርያ ፓትርያርኮች]]ና ሊቃነ ጳጳሳት፤ ከ[[አትናቴዎስ]]፥ ከ[[ሰላማ]] እስከ ብፁዕ ወቅዱስ [[አቡነ ቴዎፍሎስ]] የነበሩ [[የኢትዮጵያ ሊቃነ ጳጳሳት]]ና ፓትርያርኮች የእሳት ነበልባል በከበበው፥ የእሳት ልሳን ያለው መጋረጃ በተንጣለለበት በዚያ አዳራሽ፥ በዚያ የግርማ ዙፋን ግራና ቀኝ ተሰልፈው ቁመው ነበር። በ[[ኤፌሶን ጉባኤ]] [[ንስጥሮስ]]ን ያወገዘው የእስክንድርያ ሊቀ ጳጳሳት ታላቁ ሊቅ ቅዱስ ቄርሎስ በመንበሩ ፊት ለፊት ቆሟል። ቀድሞ የተወገዘው [[ንስጥሮስ]] የማዕረግ ልብሱን ተገፎ በስተጀርባው ቆሟል። [[አባ ጳውሎስ]] በማዕረጋቸው እንዳሉ ተከስሰው ከንስጥሮስ ጎን ቁመዋል። በዐጸደ ነፍስ የሚገኙት የእስክንድርያና የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን አበው፤ «አባ ጳውሎስ ሺ ስድስት መቶ ዓመት የኖረ ውግዘት ጥሰው፥ በሥጋው በደሙ የማሉትን መሓላ አፍርሰው የኢትዮጵያን ቤተ ክርስቲያን የ[[ሮም]] ቅኝ ግዛት ስላደረጉ፤ ፍርድ ይሰጥልን፤» ሲሉ ለኀያሉ አምላክ አቤቱታ አቀረቡ። ከዙፋኑ የመጣው መልስ ግን፤ «እስከ ዕለተ ምጽአት ፍርድ የቤተ ክርስቲያን ነው፤» የሚል ነበረ። ይህ ሁሉ በሚከናወንበት ጊዜ የማላውቀው ኀይል ከዚህ ዓለም ነጥቆ ከቅዱስ ቄርሎስ ጎን አሰልፎኝ ከቆየ በኋላ ከዙፋኑ የመጣው ድምፅ፤ «አንተ ያየኸውን፥ የሰማኸውን ለቤተ ክርስቲያን፥ ለምእመናን ንገር፤» ሲል አዝዞ ወደ ነበርኩበት መለሰኝ። ይህ ትእዛዝ ነው እዚህ ሰልፍ ውስጥ ያስገባኝ። ኢትዮጵያዊ፥ ኦርቶዶክሳዊ የሆነ ሁሉም ስለ ቤተ ክርስቲያኑ አጥብቆ መታገል አለበት።» [[አለቃ አያሌው ታምሩ]]።
 
በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን አመራር ላይ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በተደጋጋሚ የተከሰቱትን የሃይማኖት ትምህርትና የሥርዓት መበላሸት በማስመልከት የቤተ ክርስቲያኒቱ የሊቃውንት ጉባኤ ሰብሳቢ የነበሩት አለቃ አያሌው ታምሩ ችግሩ ሥር ሳይሰድ ገና ከጅምሩ እንዲታረም ማሳሰቢያና ተማጽኖ ለቤተ ክርስቲያኒቱ ቅዱስ ሲኖዶስ ተደጋጋሚ ተማጽኖ አቅርበው ነበር። ነገር ግን ጥያቄአቸው በቅዱስ ሲኖዶስ ዘንድ በቸልታ በመታየቱ ምክንያት፤ አለቃ አያሌው ታምሩ ባላቸው ከፍተኛ ሥልጣንና ኀላፊነት፤ በቤተ ክርስቲያን ላይ ዐመጽ የሚፈጽሙትን ፓትርያርኩንና ተከታዮቻቸውን ለማውገዝ ተገደዋል። ቃለ ግዝታቸው በመጀመሪያ የወጣው [[ሰኔ ፳፯]] ቀን [[1988|፲፱፻፹፰]] ዓመተ ምሕረት በ«መብሩክ» ጋዜጣ ላይ ነበር። ይኽም እንደሚከተለው ይነበባል።
 
« መላው የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ከፓትርያርኩና ተከታዮቻቸው ቃልና እጅ ቡራኬ እንዳይቀበል አገር አቀፍ ጥሪ ቀረበ። የወጣውን ሕግ የተቀበሉ፥ ከሥራ ላይ ያዋሉ እንደ [[አርዮስ]] እሱራን ውጉዛን ይሁኑ። አለቃ አያሌው ታምሩ ከእንግዲህ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ተከታይ የሆነ ምእመን በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቃልና እጅ፥ በሲኖዶሱ ዋና ጸሐፊ በ[[አቡነ ገሪማ]]ና በተባባሪዎቻቸው ቃልና እጅ ቡራኬ እንዳይቀበል በአብ፥ በወልድ፥ በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን፥ በጴጥሮስ፥ በጳውሎስ፥ በማርቆስ፥ በቄርሎስ፥ በባስልዮስ፥ በቴዎፍሎስ፥ በተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ቃልና በራሳቸው ማውገዛቸውን አስታወቁ። አለቃ አያሌው ታምሩ ይህን ያስታወቁት የግንቦቱ ሲኖዶሳዊ ጉባኤ አዲስ ያወጣው ሕገ ቤተ ክርስቲያን ላይ ያላቸውን አስተያየት እንዲሰጡንና ሐምሌ ፭ ወይም ፮ ቀን በሚከበረው የፓትርያርኩ በዓለ ሢመት ላይ የእሳቸው አመለካከት ምን ሊሆን እንደሚችል ለመገምገም ቃለ መጠይቅ ባደረግንላቸው ወቅት ነው። ይህንን የአለቃ አያሌውን ሙሉ ቃልና መልእክት የሚከተለው ነው።
 
«ከሁሉ አስቀድሞ እግዚአብሔር ሥራችንን ይባርክልን እላለሁ። በመቀጠልም ስሜቴን እንኳ መቆጣጠር እስከሚያቅተኝ ድረስ እየተጨነቅሁ በቃለ ጉባኤ ተባዝቶ በጽሕፈት ቤቱ በኩል ለአስፈላጊው እንዲደርስ በተደረገውና ከ[[ሚያዝያ ፳፪]] እስከ [[ግንቦት ፮]] ቀን ፲፱፻፹፰ ዓ.ም. በሥራ ላይ የነበረው የጳጳሳትና የሊቃነ ጳጳሳት ስብሰባ ሲኖዶስ ጉባኤ ቤተ ክርስቲያን «ሕገ ቤተ ክርስቲያን» ብሎ ስላስተላለፈው ሕግ ያለኝን ሐሳብና ድምፅ ለመላ የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ቤተ ክርስቲያን አባሎች በኢትዮጵያና በመላው ዓለም ለሚኖሩ ወንድሞቻችንና እኅቶቻችን ሁሉ በእግዚአብሔር ስም አስተላልፋለሁ። በእግዚአብሔር ስም አሰማለሁ።
 
፩ኛ፤ ክርስቶስ በደሙ የመሠረታት ቤተ ክርስቲያን የምትመራው ወይም አመራር የምትቀበል ከእሱ ከራሱ ከመንፈስ ቅዱስ እንጂ ከሰው አይደለም። ይህንንም ራሱ ባለቤቱ ኢየሱስ ክርስቶስ፤ «እስከ ዓለም ፍጻሜ እኔ ከእናንተ ጋር ነኝ፤» ያለውን ቃሉን ሲያስተላልፍ ለደቀ መዛሙርቱ የሰጠው ትእዛዝ፤ «ሂዱ አስተምሩ፤ በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ስም አስተምሩ፤» የሚል ነው። ይህንንም መልእክት በሚፈጽሙበት ጊዜ ግን የሚመራቸው ማን እንደ ሆነ ሲያስረዳ፤ «መንፈስ ቅዱስ ይመጣል፤ ወደ እውነት ሁሉ ይመራችሁአል፤» ብሎአቸዋል። (ማቴ፤ ም ፲፰፥ ቍ ፲፱ - ፳። ዮሐ፤ ም ፲፮፥ ቍ ፲፫።) አመራሩም ከ[[ሙሴ]]፥ ከ[[ኢያሱ]] የተለየ በውሥጣቸው ዐድሮ የሚመራቸው መሆኑን፥ ዓለም የማያውቀው እነሱ የሚያውቁት የእውነት መንፈስ መሆኑን በ[[ዮሐንስ ወንጌል]] ምዕራፍ ፲፭ ቍጥር ፲፭ - ፲፰ በተጻፈ ቃሉ ገልጾ ልኮአቸዋል። እንግዲህ እግዚአብሔር በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን እንዲጠብቁ ጳጳሳትን የሚሾም፥ ጉባኤያቸውን የሚመራም እሱ ራሱ መንፈስ ቅዱስ ነው። በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የተዋሕዶ ሃይማኖት ትምህርት ይህ ነው። ሰው ጉባኤ ቤተ ክርስቲያንን አይመራም። ግን በኋላ ዘመን ራሱን እንደ እግዚአብሔር የሚቈጥር፥ እንደ እሱ ነኝ ብሎ መሥራት የሚያምረው በቤተ እግዚአብሔር የሚኖር ትዕቢተኛ እንደሚመጣ ቅዱስ ጳውሎስ ተናግሮአል። (፪ ተሰ፤ ም ፪፥ ቍ ፬።) ይህ ካልሆነ በስተቀር በቤተ እግዚአብሔር አመራር ሰጪ እኔ ነኝ ብሎ የሚናገር ወይም እሱ ነው ተብሎ የሚነገርለት ማንም የለም። ሐዋርያት ራሳቸውም በመንፈስ ቅዱስ እንደ ተጠሩ በወንጌል ስብከት እንደ ተላኩ፥ የኢየሱስ ክርስቶስ ባሮች፥ አገልጋዮች፥ መልእክተኞች እንደ ሆኑ ተናገሩ እንጂ፤ እንዲሁም ቤተ ክርስቲያን የእግዚአብሔር ማኅበር እንደ ሆነች አስተማሩ እንጂ እነሱ ጌቶች፥ መሪዎች፥ አመራር ሰጪዎች እንደ ሆኑ፥ ቤተ ክርስቲያንም የእነሱ ተጠሪ እንደ ሆነች አልተናገሩም፤ አልጻፉም። የተፈጸመው አገልግሎት በጠቅላላ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እንደ ተፈጸመ፥ እንደሚፈጸም፤ የተደረገ በደል ቢኖር ደግሞ በመንፈስ ቅዱስ ላይ እንደ ተፈጸመ ጻፉ፤ ተናገሩ። ሐናንያ የተባለው ሰው የመጀመሪያዪቱን ቤተ ክርስቲያን አቋምና እርምጃ በተጠራጠረና በተፈታተነ ጊዜ ቅዱስ ጴጥሮስ፤ «መንፈስ ቅዱስን ታሳብለው ዘንድ እንዲህ በልብህ ሰይጣን ሞላን? ወይስ እንዴት ሞላ፤» ብሎ ገሠጸው እንጂ የእኔን ቃል፥ የእኔን መሪነት ተላለፍክ ብሎ አልገሠጸውም። እንዲሁም፤ «ሲጾሙና ሲጸልዩ ሳዖልንና በርናባስን እኔ ለመረጥኩላቸው ሥራ ለዩልኝ ብሎ መንፈስ ቅዱስ አዘዛቸው፤» ይላል እንጂ ሰው ለመረጠላቸው ሥራ አይልም። እንግዲህ፤ «ሰማይና ምድር የሚያልፉ ቢሆንም እንኳ ቃሌ አያልፍም፤» ያለ አምላክ የመሠረተላት፥ የሠራላት ሕግ ምን ጊዜም የማያልፍ መሆኑ ቀጥተኛ እውነት ነው። በዚህ መሠረት የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ሲኖዶስ የሚመራ በመንፈስ ቅዱስ መሆኑን፥ ቅዱስ ያሰኘውን ቅድስናውን ያገኘው፥ የሚያገኘው ከመንፈስ ቅዱስ ብቻ መሆኑን ታምናለች። ሥራዋንም በዚሁ እምነት ስታከናውን ኖራለች፤ ታከናውናለችም። ከፓትርያርኩ ጀምሮ ሊቃነ ጳጳሳት፥ ጳጳሳት፥ ኤጲስ ቆጶሳት ሁሉ፤ «ናነብር እደዊነ ዲበ ዝንቱ ኅሩይ ገብር ዘእግዚአብሔር፤» «በተመረጠ በዚህ የእግዚአብሔር አገልጋይ ላይ እጃችንን እንጭናለን፤» በሚል አነጋገር ከሦስት ቍጥር ባላነሱ ኤጲስ ቆጶሳት ድምፅና ተግባር ቤተ ክርስቲያን የምትሾማቸው ሁሉ ተጠሪነታቸው የቤተ ክርስቲያን ነው እንጂ የአንድ ሰው አይደለም። ሁሉም ይህን ያውቃሉ ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ሐዋርያውም፤ «ክርስቶስ በደሙ የዋጃትን ቤተ ክርስቲያን እንድትጠብቁ መንፈስ ቅዱስ ጳጳሳት አድርጎ የሾማችሁ እናንት ለመንጋውና ለራሳችሁ ተጠንቀቁ፤» ወይም፤ «የተሾማችሁባቸውን መንጋዎችን ሁሉና ራቻችሁን ጠብቁ፤» ብሎ የተናገረ ስለዚህ ነው። (የሐ፤ ሥራ ም ፳፥ ቍ ፳፰።)
 
፪ኛ፤ ይህ ከዚህ በላይ የጠቀስኩት ቋሚ መመሪያ ሲሆን ልዩ ልዩ መናፍቃን በቤተ ክርስቲያን ውሥጥ በተነሡበት ጊዜ ሁሉ ጉባኤ ጳጳሳት በመንፈስ ቅዱስ መሪነት እየተሰበሰበ ቤተ ክርስቲያንን ከስሕተት፥ ከኑፋቄ ሲጠብቁ ኖረዋል። በኋላ ግን ከቤተ ክርስቲያን ክብር እየሸሹ፥ ወደ ዓለማዊ ክብር እየተጠጉ፥ የእግዚአብሔርን ኀይልና ሥልጣን መከታ አድርገው መሥራት ሲገባቸው በመንግሥታዊ የፖለቲካ ኀይልና ሥልጣን መጠቀም የፈለጉ መለካውያን ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት በቤተ ክርስቲያን ላይ መከፋፈልን ስለ ፈጠሩ በምድር ላይ ዳግማዊ ክርስቶስ የሚባል መሪ አበጁ። የኢትዮጵያ ቤተ ክርስቲያን ግን በዚህ የፈተና ጊዜ በታላላቆችና በአስተዋይ ሊቃውንቶቿ አስተዋይነት፥ በመንፈስ ቅዱስ መሪነት ጸንታ ኖረች። ለሰው አልተንበረከከችም። ይህም በኢትዮጵያ አስተዳደር መንግሥት የለውጥ ጊዜ እስከ መጣበት እስከ [[1986|፲፱፻፷፮]] ዓመተ ምሕረት ድረስ ጸንቶ ኖሯል። ከዚያ ወዲህ ግን የሥጋዊው ቍስል ወደ መንፈሳዊው ተጋብቶ ይመስላል ኢትዮጵያ በቍስል ላይ ቍስል ተጨምሮባት በሥጋዊ አስተዳደር ኮሚዩኒዝም ያመጣባት በሽታ መንፈሳዊ አቋሟንም ጎድቶታል። በዚህም ምክንያት በቤተ ክርስቲያን ከደረሱት ዋና ዋና ችግሮች፤
 
*ሀ፤ የሃይማኖት ሕፀፅና የሥርዓት መበላሸት፤
*ለ፤ በቤተ ክርስቲያኒቱ ውሥጥ ውሥጥ አደግ የሆኑ መናፍቃን መፈልፈልና የኑፋቄ መጻሕፍትን ማብዛት፤
*ሐ፤ ፓትርያርኮቿ ወደ ራስ ትምክሕት፥ ወደ እብሪትና ወደ ትዕቢት በመተላለፋቸው ሲኖዶሱን የግል ግዛታቸው ማድረጋቸው፥ በገዛ ሥልጣናቸው ሲኖዶስ እያፈረሱ ሲኖዶስ መሠየማቸው፥ በመንግሥት የሥልጣን ድጋፍ ወደ ማዕረግ መውጣታቸው ዋና ዋናዎቹ ሲሆኑ፤ በዐምስተኛው ፓትርያርክ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ዘመን የታየው ደግሞ በውጭ ያዩት ዳግማዊ ክርስቶስ ተብሎ መሰየምና በፓትርያርክነት ቢመረጡ በአምላክ ፈንታ ሆኖ መንፈስ ቅዱስን መጋፋት፥ ዳኝነቱን መርገጥ ሆኗል። ይህም በቤተ ክርስቲያኒቱ ላይ የማይጠገን ስብራት፥ የማይድን ቍስል ሆኖባታል።
 
፫ኛ፤ እኔ በእነዚህ ፳፪ ና ፳፫ ዓመታት አቤቱታዬን ሳሰማ ኖሬአለሁ። ዕድል ሆነና ዛሬም እጮሃለሁ። ድምፄ ግን በውሃ ውሥጥ እንደሚናገር ሰው ተሰሚነት አላገኘም። ግን በእግዚአብሔር ላይ አሁንም ተስፋ አልቆርጥም። እንደገና እጮሃለሁ፤ እንደገና አቤት እላለሁ። የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን ምእመናን ፍርሃታቸውን ከልባቸው አውጥተው ጥለው ለቤተ ክርስቲያናቸው፥ ለሀገራቸው፥ ለሃይማኖታቸው፥ ለክብራቸው መቆም እስከ ቻሉ ድረስ አቤቱታዬን አሰማለሁ።
 
ከዚህ በላይ የዘረዘርኩት እንደ መቅድም ያህል ሲሆን ፍሬ ነገሩ የሚከተለው ነው። እንደሚታወቀው ዘንድሮ በ[[1988|፲፱፻፹፰]] የተደረጉት የቤተ ክርስቲያኒቱ ጠቅላላ ስብሰባና የሊቃነ ጳጳሳት ስብሰባ አንደኛ በጥቅምት፥ ሁለተኛ በሚያዝያና በግንቦት መገናኛ ከሚያዝያ ፳፪ እስከ ግንቦት ፮ የተደረጉ ሲሆኑ ሁለቱም ጊዜዎች ሸር የተሞላባቸው ነበሩ። ይህንንም እንደሚከተለው እገልጻለሁ።
 
ሀ፤ በቤተ ክርስቲያን የደረሱት ልዩ ልዩ ችግሮች ሁሉ በሲኖዶስ ተመክሮባቸው እንዲወገዱና እርምጃቸውም እንዲገታ በ፲፱፻፹፯ ጥቅምትና ኅዳር ወር ለሲኖዶሱ ማመልከቻ ስጽፍ መልእክቴ በጌታዬ በአምላኬ ትእዛዝ የተደረገ መሆኑን ገለጨ በአፈጻጸሙ ቸልተኛነት እንዳይታይበት ሲኖዶሱን በሾመ በመንፈስ ቅዱስ ዳኝነት ተማጽኜ አቤቱታዬ የእኔ ብቻ ሳይሆን በዐጸደ ሥጋና በዐጸደ ነፍስ ያሉ የኦርቶዶክሳውያን አበውና ምእመናን አቤቱታ መሆኑን ገልጬ ነበር ያቀረብኩት። ነገር ግን የሲኖዶሱ ዋና ጸሓፊ አባ ገሪማና ፓትሪያርኩ ሐሳባቸው እስከ አሁን በቤተ ክርስቲያን የኖረውን የመንፈስ ቅዱስን መሪነት ሽረው የራሳቸውን ጣዖታዊ መሪነት ለመተካት ኖሮ በጥቅምት ወር ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት በተደረገው አጠቃላይ ጉባኤ ላይ ያቀረብኩትን አቤቱታ ጭምር ሳይቀበሉ ከመቅረታቸውም በላይ የመንፈስ ቅዱስን ዳኝነት፥ የሲኖዶሱን ሥልጣን ለግል አድመኞቻቸው ኮሚቴ አሳልፈው በመስጠትና በሱ ውሳኔ ተደግፈው የኑፋቄ መጽሐፍ ማውጣታቸውና መበተናቸው አንሶ ኦርቶዶክሳዊውን የሊቃውንት ጉባኤ አፍርሰዋል።
 
ለ፤ ይህ በዚህ እንዳለ ሲኖዶሱ ተሰብስቦ ጉዳዩን እንዲያይ በግል ማመልከቻ፤ በነጻ ፕሬሱ በኩልም ተቃውሞዬን በማሰማት ላይ እያለሁ ሚያዚያ ፲፰ ቀን ፲፱፻፹፰ ዓመተ ምሕረት የቅሬታ አስወጋጅና የሰላም ኮሚቴ በሚሉት የግል ኮሚቴያቸው ድጋፍ እኔን ካባረሩ በኋላ ከሚያዚያ ፳፪ እስከ ግንቦት ፮ ባደረጉት በአፈና የሲኖዶስ ስብሰባ ሕግ አስወጥተው በመንፈስ ቅዱስ ፈንታ ራሳቸው ፓትሪያርኩ ሲኖዶሱ ወንጌልን ለሚሰብክበት፥ ቀኖና ቤተ ክርስቲያን ለሚያስተምርበት ጉዞ አመራር ሰጪ (ጣዖት) ወደ መሆን አድገዋል። በቤተ ክርስቲያን ስም ተሰይመው እግዚአብሔርንና ቤተ ክርስቲያንን ሊያገለግሉ የተሾሙ ኤጲስ ቆጶሳት፥ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት የሲኖዶሱ ዋና ጸሓፊ ሳይቀር ለቤተ ክርስቲያን ተጠሪ መሆናቸው ቀርቶ ለፓትሪያርኩ ተጠሪዎች እንዲሆኑ ሲያደርጉ በዚያ [[ሚያዚያ ፴]] ቀን ተፈርሞ ጸድቋል በተባለውና በጽሕፈት ቤቱ አማካኝነት ለሚመለከተው ሁሉ እንዲተላለፍ የቃለ ጉባኤ ትእዛዝ በተሰጠበት ሕግ፤ ቤተ ክርስቲያን እስከ አሁን ስትሠራባቸው የኖሩት ሕጎችና ደንቦች ሁሉ በዚህ ሕግ ተሻሽለው ከስፍራቸው ሲወገዱ፥ አባ ጳውሎስ በመንፈስ ቅዱስ ፈንታ የቤተ ክርስቲያኒቱን የአመራር ሰጪነት ቦታ ሲይዙ በቤተ ክርስቲያን ላይ የአምልኮ ጣዖት ዐዋጅ ታውጆባታል። ፓትሪያርኩ በሾማቸው በእግዚአብሔርና በቤተ ክርስቲያን ላይ በፈጸሙት ተግባር ታላቅ በደል ፈጽመዋል። ከሳቸው ጋር ቃላቸውን ለማጽደቅ፥ ምኞታቸውን ለሟሟላት በሕጉ ላይ ፈርመዋል ተብሎ ስማቸው የተመዘገበላቸው ፴፬ቱ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳትም እንደ ተባለው አድርገውት ከሆነ ለተፈጸመው በደል ተባባሪዎች ናቸው። ይህም እጅግ የሚያሳዝን ነው። የሚገርመው ደግሞ በዚሁ ሕግ በአንቀጽ ፲፬፤ «ፓትሪያርኩ የተዋሕዶ ሃይማኖትን የሚያፋልስ፥ ሕግጋተ ቤተ ክርስቲያንን የማይጠብቅ፥ ማዕረጉን የሚያጎድፍ ሆኖ መገኘቱ በተጨባጭ ማስረጃ ሲረጋገጥ በምልአተ ጉባኤ ያለአንዳች የሐሳብ ልዩነት በቅዱስ ሲኖዶስ ከተጠና በኋላ በቅዱስ ሲኖዶስ ውሳኔ መሠረት ከማዕረጉ ይወርዳል፤» የሚል ቃል አስፍሮ ሲኖዶሱን በአፈና ልዩ ሥልጣን ተጠቅመውና እንደ ሌለ አድርገው ካሳዩ በኋላ፤ «የኑፋቄ መጻሕፍት በማሳተም የተዋሕዶ ሃይማኖትን አፋልሰዋል፤ ሕገ ቤተ ክርስቲያንን ሳይጠብቁ ቤተ ክርስቲያን ከምታወግዛቸው ጋር የጸሎተ ቅዳሴና የማዕድ ተሳትፎ አድርገዋል፤ ቤተ ክርስቲያኒቱ ከምታወግዘው ፓፓ ቡራኬ ተቀብለዋል፤» እያልን እየተቃወምን ለተቃውሟችንም ተጨባጭ ማስረጃ እያቀረብን፤ እሳቸውም ይህንን ሳይቃወሙ ይህ እንዳይቀጥል በሥልጣናቸው ተጠቅመው ኦርቶዶክሳዊውን የሊቃውንት ጉባኤ ሲያፈርሱ ጉዳዩን አይቶ ውሳኔ በመስጠት ፈንታ እንደገና በሕግ፥ በመንፈስ ቅዱስ ስፍራ ተተክተው ለሲኖዶሱ ሥልጣንና ተግባር አመራር ሰጪ ይሆናሉ፤ የሲኖዶሱ አባሎች ሁሉ ለፓትሪያርኩ ተጠሪ ይሆናሉ፤ ሲል የወጣው አዋጅ አፈጻጸም ነው። ይህ ሕገ ቤተ ክርስቲያን ተብሎ የታወጀው ሕግ፤ «እስመ ሜጥዋ ለዐመፃ ላዕሌከ፤» «ዐመፅን ወደ አንተ መለሷት፤» ተብሎ እንደ ተጻፈ ቤተ ክርስቲያንን መካነ ጣዖት፥ ምእመናንን መምለኪያነ ጣዖት የሚያሰኝ ስለ ሆነ ምእመናን ሁሉ በሙሉ ድምፅ እንድትቃወሙት በእግዚአብሔርና በቤተ ክርስቲያን ስም እጠይቃለሁ።
 
ሐ፤ ከአሁን ጀምሮ ማለት ይህ ቃል በነጻው ፕሬስ ከተላለፈበት ጊዜ ጀምሮ በብፁዕ ወቅዱስ አቡነ ጳውሎስ ቃልና እጅ፥ በሲኖዶሱ ዋና ጸሓፊ በአቡነ ገሪማ ቃልና እጅ፥ ይህን አሁን የተጻፈውን ሕግ የቤተ ክርስቲያን ሕግ ብለው አጽድቀው በተባባሪነት አሳልፈዋል የተባሉ ጳጳሳትና ሊቃነ ጳጳሳት ሁሉ እውነት ሆኖ ከተገኘ የበደሉ ተባባሪዎች ናቸውና በነሱ ቃልና እጅ ቡራኬ እንዳትቀበሉ፥ እንዳትናዘዙ፤ ስማቸውን በጸሎተ ቅዳሴ የሚጠሩ አለቆች፥ ቀሳውስት፥ ካህናት ካሉም የአምልኮተ ጣዖት አራማጅ ናቸውና ተጠንቅቁባቸው፤ ምክር ስጧቸው፤ እንቢ ካሉም ተለዩዋቸው። እንዲሁም ሐምሌ ፭ ወይም ፮ ቀን ይከበራል ተብሎ ሽርጉድ የሚባልለት በዓለ ሢመት የአሮን የወርቅ ጥጃ መታሰቢያ ሆኖ በቤተ ክርስቲያን ሊከበር የማይገባው ስለ ሆነ በዓሉ ከመድረሱ በፊት የሲኖዶሱ አባላት በአስቸካይ ተሰብስበው ሕጉን ካልሻሩና በጣዖትነት የተሰየሙትን አቡነ ጳውሎስን ከሥልጣናቸው ካላነሡ ምእመናን ይህንን በዓል እንዳታከብሩ ለቤተ ክርስቲያን ደሙን ባፈሰሰ አምላክ ስም፥ ቤተ ክርስቲያንን በሚመራና በሚጠብቅ በመንፈስ ቅዱስ ስም ጥያቄዬን አስተላልፋለሁ። ምናልባት የሕጉን ጽሑፍ አንብቦ መረዳት የተሳነው፥ ግን በልዩ ልዩ ደጋፊዎቻቸው ተጭበርብሮ በቸልታ የሚመለከተው፤ ከዚያም ዐልፎ በሥልጣናቸው እየተመኩ ለቤተ ክርስቲያን ጥያቄ ጆሯችንን አንሰጥም ብለው ይህን በደል ያደረሱትን ፓትርያርክ አቡነ ጳውሎስን፥ በሦስት የሹመት ስም የሚንቀባረሩትን አባ ገሪማን፥ ለነሱ ድጋፍ የሚሰጡትንም ሁሉ፤ ጌታዬ አምላኬ፤ «በምድር ያሰራችሁት በሰማይ የታሰረ ይሆናል፤» ሲል በሰጠው ቃል በአብ በወልድ በመንፈስ ቅዱስ ሥልጣን፤ በጴጥሮስ፥ በጳውሎስ፥ በማርቆስ፥ በቄርሎስ፥ በባስልዮስ፥ በቴዎፍሎስ፥ በተክለ ሃይማኖት ዘደብረ ሊባኖስ ቃል፤ ኃጥእ ደካማም በምሆን በእኔም በቀሲስ ወልደ ጊዮርጊስ ቃል አውግዤአለሁ። ይህን ሕግ የተቀበሉና ከሥራ ላይ ያዋሉ ሁሉ እንደ አርዮስ፥ እንደ መቅዶንዮስ፥ እንደ ንስጥሮስ፥ እንደ ፍላብያኖስ፥ እንደ [[ኬልቄዶን ጉባኤ]]ና ተከታዮቹ እሱራን፥ ውጉዛን ይሁኑ። በማይፈታው በእግዚአብሔር ሥልጣን አስሬአለሁ።
 
ለአብ ለወልድ ለመንፈስ ቅዱስ ምስጋና ይሁን አሜን።
 
ማስጠንቀቂያ፤ አምላኬ ሂድ ተናገር ያለኝን ትእዛዝ ለእናንተ አድርሻለሁ። ሩጫዬንም ጨርሻለሁ። ከእንግዲህ ተጠያቂነቱ የእናንተ የምእመናንና ታሪክ ተጠያቂ ያደረገው የመንግሥት ነው። ለዚህም ምስክሬ ራሱ እግዚአብሔር፥ ቅዱሳን መላእክት፥ ሰማይና ምድር ናቸው።
 
አለቃ አያሌው ታምሩ ዘዲማ ጊዮርጊስ።» »
 
== ልዩ ባሕርይ ==