ሆፕ ኩክ
ሆፕ ኩክ (እንግሊዝኛ:-Hope Cooke 1932 ዓም ተወልዳ) ከ1957 እስከ 1967 ዓም ድረስ የሲኪም መንግሥት ንግሥት ነበሩ። የአሜሪካ ተወላጅ ስትሆን በሕንድ አገር በ1951 ዓም እርሷና ባሏ ልዑል ፓልደን ጦንዱፕ ናምግያል ተዋውቀው በ1955 ዓም ተዳሩ እና ልዕልት ሆነች። በ1957 ፓልደን ዙፋናቸውን ወርሰው እርሷም የሲኪም ንግሥት ሆነች።
የሲኪም መንግሥት በተግባር የሕንድ አገር ጥገኛ ነበረ። ሆኖም በ1965-1966 ዓም ንጉሥነቱን ለማስወገድና የሕንድ ክፍላገር ለመሆን የሚል እንቅስቃሴ በሕዝቡ መካከል ተነሣ። በሚያዝያ ወር 1967 ዓም መንፈቅለ መንግሥት ተከሠተ፤ ንጉሡ ለጊዜው ታሠሩ፤ ሲኪም ክፍላገር ተብሎ ወደ ሕንድ ተጨመረ፤ ንግሥቷ ወደ አሜሪካ ተመለሰች። በ1972 ዓም ትዳራቸው በይፋ ተፈታ። ሁለት ልጆች ነበሯቸው። ከዚያ በኋላ እስካሁንም ድረስ ደራሲ ሆና አንዳንድ ጽሁፍ ጽፋለች።