ህያርባስ ወይም ያርባስ በሮማውያን አፈ ታሪክ በጥንት ዘመን የጌቱሊያ ንጉሥ ነበር። ለቀርታግና መስራች ለንግሥት ዲዶ መሬት ሰጣት።
አኒዩስ ዴ ቪቴርቦ ባሳተመው ዜና መዋዕል ዘንድ ከዚያ በፊት ሌላ ህያርባስ የሊቢያ ንጉሥ በ2162 ዓክልበ. ግድም ሆነ። በጦርነት አስፈሪ ነበር፤ በ2141 ዓክልበ. ግድም የአማዞኖች ንግሥት ሚሪና አሸነፈችው፤ መንግሥቱን ያዘች።