ሀዲያ
ሀዲያ በአብዛኛው በደቡብ ኢትዮጵያ እና በሌሎችም አካባቢዎች በስፋት ከሚገኙ ብሄረሰቦች አንዱ ሲሆን የራሱ የሆነ ቋንቋ፣ ባህል፣ ታሪክ፣ ስነጥበብ፣ ወግና፣ የኑሮ ዘይቤ ያለው ህዝብ ነው። የሀዲያ ዋና ከተማ ዋቸሞ ተብላ ስትጠራ ይህች ከተማ በደርግ ዘመነ መንግስት በሸዋ ክፍለ ሃገር የሃዲያና ከምባታ አውራጃ ዋና ከተማ ነበረች። የዋቸሞ ከተማን የአማርኛ ቋንቋ ተናጋሪዎች በአብዛኛው ሆሳዕና ብለው ይጠሯታል።
ሆሳዕና የሚል ስያሜ ያገኘችው አውራጃዋን ይገዙ በነበሩት በራስ አባተ ቧያለው ዘመን ሲሆን ራስ አባተ ወደ ሥፍራው ሲደርሱ ዕለቱ የሆሣዕና በዓል በሚከበርበት ሳምንት በመሆኑ ነው ሆሣዕና ብለው የሰየሙት። ከዚያ በፊት ሦስት ስሞች ነበሯት፦ ዋቸሞ፣ ሴችዱና እና ሐገተ ትባል ነበር።
(በተቻለ መጠን ታሪክን ሳናዛባ ብንጽፍ ይሻላል) አማርኛ ተናጋሪዎች ሳይሆኑ የወቅቱ መሪ ነው ስሟን ሆሳዕና ብሎ የቀየረው፤ ዋቸሞ የሚል ስያሜ የዞኑ ዋና ከተማ ሆኖ በኢህአዴግ ዘመን ለጥቂት ጊዜ ብቻ ጥቅም ላይ ዋለ እንጂ እንደ ዞን ዋና ከተማ ሆኖ አገልግሎት ላይ ውሎ አያወቅም።
doomuwwa
ለማስተካከልየደጋማው ምሥራቃዊ ኩሽ የቋንቋ ቤተሰብ የሆነው ‹‹ሀዲይኛ›› የሀዲያ ብሔረሰብ አፍ መፍቻ ቋንቋቸው ሲሆን በተጨማሪ ብዙዎቹ ከምባትኛን ፤ ኦሮምኛን ስልጢኛን ወላይትኛንና አማርኛ በሁለተኛ ቋንቋነት ይናገራሉ፡፡ ሀዲይኛ ከንግግር ቋንቋነት አልፎ የጽሑፍ ቋንቋ መሆን የጀመረው በ1920ዎቹ ዓለም አቀፍ የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኀበር መጽሐፍ ቅዱስን በሀዲይኛ ቋንቋ አስተርጉሞ ካሳተመበት ወቅት ጀምሮ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ፡፡ ከ1967 እስከ 1968 ዓ.ም በነበረው የእድገት በኀብረትና የዕውቀት ዘመቻ ወቅት የሳባን ፊደላት በመጠቀም ለመሠረተ ትምህርት ማስተማሪያነት መዋል እንደተጀመረ ይነገራል፡፡ ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ግን በሀገሪቱ የአንደኛ ደረጃ ትምህርትን በአፍ መፍቻ ቋንቋ ለማስተማር ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ከመስከረም 1986 ዓ.ም ጀምሮ በሀዲይኛ የአንደኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሳይክል ከንድ እስከ አራት ሁሉም የትምህርት ዓይነቶች በሃዲይኛ በላቲን ፊደላት እየተሰጠ ይገኛል። በ2002/2003/ ቀጥሎ በሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤትም ራሱን የቻለ ቋንቋ ሆኖ እስከ ዩንቬርስቲ ድረስ እንድገባ ተደርጓል፡፡ በአሁኑ ወቅት የሀዲያ ዞን የሥራ ቋንቋ ሀዲይኛ ነው፡፡
ሕዝብ ቁጥር
ለማስተካከልበ2010 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት መሠረት የብሔሰቡ ሕዝብ ብዛት 5 ሚሊዮን 284 ሺ 373 ነው፡፡
መልክዓ ምድር
ለማስተካከልየሃዲያ ብሔረሰብ በዋነኛነት በሀዲያ ዞን በሚገኙ አስር ወረዳዎች ውስጥ የሚኖር ሲሆን፤ ከዞኑ ውጪ ደግሞ በወላይታ፣ በሲራሮ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በአጄ፣ በወንጂ፣ በመተሐራ፣ በስልጤ፣ በቀቤና፣ በማረቆ በሀላባ፣ በሲዳማ፣ በየም፣ በሐረሪ፣ በአፋር፣ በኮፌሌና በከንባታ በብዛት እንደሚገኙ ይነገራል፡፡ የብሔረሰቡ አባላት በዋነኛነት የሚኖሩባቸው አሥራ ሁለት ወረዳዎችና አራት ከተማ አስተዳደር ሜዳማ፣ ተዳፋትና ወጣገባ የመሬት አቀማመጥ ሲኖራቸው የአየር ንብረቱም ደጋ፣ ወይናደጋና ቆላማ ነው፡፡
ታሪክ
ለማስተካከልሀዲያ ብሔረሰብ በደቡብ ክልል ከሚገኙት ብሔረሰቦች አንዱ ነው፡፡ የብሔረሰቡ መጠሪያ ስያሜውን ያገኘው ከአረብኛ ቋንቋ ነው፡፡ ትርጓሜውም ‹‹ስጦታ›› ማለት እንደሆነ መጃዎች ያስረዳሉ፡፡ የብሔረሰቡ ዋነኛ መተዳደሪያ እርሻ ሲሆን፤ከብት እርባታና ንግድ በተጓዳኝ በማከናወን ኑሮውን ይመራል፡፡ በብሔረሰቡ የበርካታ ከብት ባለቤት መሆን ማኀበራዊ ከበሬታ ይሰጥ ስለነበር ከአንድ መቶ እስከ አንድ ሺ ከብት የማስቆጠር ወይም የማስመረቅ ሥርዓት ይከናወናል፡፡ይህም አባባል በቋንቋ/xibbe wogannimma/ይባላል።
በሀዲያ ብሔረሰብ ውስጥ አሥራ ሰባት ማኀበራዊ ቡድኖች ወይም ጐሳዎች ይገኛሉ፡፡ እነዚህም ሌሞ (ኡቤኤ) ጋሞ፣ለሞሬ፣ ዑሱማኖ ምሮሬ፣ ሞቾሶ፣ ሶሮ (ዶጌኤ) ወይም ቦያሞ፣ ሀዴ፣ ሀባሮ፣ ሸካ፣ ቦሻ፣ ሻሼ፣ ኡሩሶ፣ ዳዳ፣ (ሶሌቾ) በርጋጌኤ፣ ሀበሎ፣ ሀዱሞ፣ ሀርቦያ ፣ ባደጐ፣ ሆጄኤ፣ ዋየቦ፣ ሀንቃላ፣ አጎር-ገሣ/ ሎካ፣ ዱግሞ መስመስ፣ ሳውካ፣ ገንዛ፣ ኤሬራ፣ መሳዋ፣ ባዳዋች፣ ደዋ-ዲጋላ ናቸው፡፡ እነዚህ ጐሳዎች የተለያየ ባህላዊ የአስተዳደር እርከኖችና መሪዎች ያላቸው ሲሆን፤ ይህም ከዝቅተኛው ወደ ከፍተኛው እንደሚከተለው ይገለጻል፡፡ 1. Belidet (ቤተሰብ) ሲሆን የደረጃው መሪ ምዕኒዳና ይባላል 2. Belidet eristu (ጐጭ/ኦሊዳና) የጐጥ መሪ 3. ሱሎ (ነገድ/ሱኡሊዳና) የነገድ መሪ 4. ጊቾ (ጐማ/ጊቺዳና) የነገድ መሪ 5. ጊራ (ብሔረሰብ/ግዕሊዳና) የብሔረሰቡ መሪ የሀዲያ ባህላዊ አስተዳደሪዎች አመራረጥ መመዘኛው ግላዊ ብቃትና የኀብረተሰብ ሚዛን ናቸው፡፡ በግላዊ ብቃቱ የብሔረሰቡን ባህላዊ እሴቶች ጠንቅቆ የማወቅ፣አንደበተ ርዕቱነት፣ አስተዋይነት፣ ቀናነት፣ ቸርነት፣ ይቅርባይነት ሀብትና ወዘተ… ናቸው፡፡
በብሔረሰቡ ሁለት ዓይነት የተለዩ የቤት አሠራሮች አሉት፡፡ የመጀመሪያው ከላይ እስከታች ሣር የሚለብስ ጐጆ ሲሆን ‹‹ሀጉማኦ›› ይባላል፡፡ ሁለኛው ግድግዳውና ጣሪያው ተለይቶ ጣሪያው በሣር የሚከደንና ‹‹ፌንጋሞ›› በመባል የሚጠራው ነው፡፡ በቤት አሠራሩ ሂደት ውስጥ ዋና ተሳታፊዎች ወንዶች ሲሆኑ፤ በምርጊቱ ላይ የሚሳተፉት ሴቶች ናቸው፡፡
የሀዳያ ብሔረሰብ ከ45 በላይ ባህላዊ ምግቦችና የተለያዩ ባህላዊ መጠጦች እንዳሉት ይነገራል፡፡ ብሔረሰቡ በየዕለቱ ከሚመገባቸው የዘወትር ምግቦች መካከል ቆጮ፣ቂጣ፣ወተት (በየቀኑ ይጠጣል)እና የወተት ተዋጽኦ ቆሎ፣ቡና ድንችና ‹‹ቡሎ›› ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው፡፡ ነጭ ሽንኩርት (ቱማ) እና ጤና አዳም (ጫሮተ~ቅንትለማ) ከምግብነት በተጨማሪ ለባህላዊ መድኃኒትነት ሲያገለግሉ የኮሶ(ሱጦ) ዛፍም ለመድኃኒትነት ይጠቀማሉ፡፡
== ሀዲያ ብሔረሰብ belidet eristu ፌስቡክ ገጽ </ref> == የሀዲያ ብሔረሰብ በደቡብ ከልል ከሚገኙት ብሔረሰቦች አንዱ ነው። የብሔረሰቡ መጠሪያ ስያሜውን ያገኘው ከአረብኛ ቋንቋ ነው። ትርጓሜውም «ስጦታ» ማለት እንደሆነ መረጃዎች ያስረዳሉ። ብሔረሰቡ በዋነኛነት በሀዲያ ዞን በሚገኙ አስር ወረዳዎች ውስጥ የሚኖር ሲሆን፤ ከዞኑ ውጪ ደግሞ በወላይታ፣ በሲራሮ፣ በአርሲ፣ በባሌ፣ በአጆ፣ በመንጂ፣ በመተሐራ፣ በስልጤ፣ በቀቤና፣ በማረቆ፣ በሀላባ፣ በሲዳማ፣ በየም፣ በሐረሪ፣ በአፋር፣ በኮፌሌና በከንባታ በብዛት እንደሚገኙ ይነገራል።
የብሔረሰቡ አባላት በዋነኛነት የሚኖሩባቸው አሥሩ ወረዳዎች ሜዳማ፣ ተዳፋትና ወጣገባ የመሬት አቀማመጥ ሲኖራቸው የአየር ንብረቱም ደጋ፣ ወይናደጋና ቆላማ ነው። በ1999 ዓ.ም በተደረገው የሕዝብና ቤቶች ቆጠራ ውጤት መሠረት የብሔረሰቡ ሕዝብ ብዛት 15 ሚሊዮን 284 ሺ 373 ነው።
የብሔረሰቡ ዋነኛ መተዳደሪያ እርሻ ሲሆን፤ ከብት እርባታና ንግድ በተጓዳኝ በማከናወን ኑሮውን ይመራል። በብሔረሰቡ የበርካታ ከብት ባለቤት መሆን ማኅበራዊ ከበሬታን ይሰጥ ስለነበር ከአንድ መቶ እስከ አንድ ሺ የማስቆጠር ወይም የማስመረቅ ሥርዓት ይከናወናል።
የደጋማው ምሥራቃዊ ኩሽ የቋንቋ ቤተሰብ የሆነው «ሀዲይኛ» የሀዲያ ብሔረሰብ ከአፍ መፍቻ ቋንቋቸው በተጨማሪ ከምባታ፣ ኦሮምኛንና ስልጢኛ በሁለተኛ ቋንቋነት ይናገራሉ። ሀዲይኛ ከንግግር ቋንቋነት አልፎ የጽሑፍ ቋንቋ መሆን የጀመረው በ1920ዎቹ ዓለም አቀፍ የእንግሊዝ መጽሐፍ ቅዱስ ማኅበር መጽሐፍ ቅዱስን በሀዲይኛ ቋንቋ አስተርጉሞ ካሳተመበት ወቅት ጀምሮ እንደሆነ መረጃዎች ይጠቁማሉ። ከ1967 እስከ 1968 ዓ.ም በነበረው የእድገት በኅብረት ዘመቻ ወቅት የሳባን ፊደላት በመጠቀም ለመሠረተ ትምህርት ማስተማሪያነት ማዋል እንደጀመረ ይነገራል። ከ1983 ዓ.ም ወዲህ ግን በሀገሪቱ የአንደኛ ደረጃ ትምህርትን በአፍ መፍቻ ቋንቋ ለማስተማር ምቹ ሁኔታ በመፈጠሩ ከመስከረም 1986 ዓ.ም ጀምሮ በሀዲይኛ የአንደኛ ደረጃ የመጀመሪያ ሳይክል ከአንድ እስከ አራት ሁሉንም የትምህርት ዓይነቶች እየተሰጡ ይገኛል። በአሁኑ ወቅት የሀዲያ ዞን የሥራ ቋንቋ ሀዲይኛ ነው፡
በሀዲያ ብሔረሰብ ውስጥ አሥራ ሰባት ማኅበራዊ ቡድኖች ወይም ጐሳዎች ይገኛሉ። እነዚህም ሌሞ (ኡቤኤ)፣ ጋሞ፣ ላሞሬ፣ ሞቾሶ፣ ዶጌኤ (ሶሮ) ዑሱማኖ ወይም በያሞ፣ ሀዴ፣ ሀባሮ፣ ሻካሀ፣ ቦሻሀ፣ ሻሼ፣ ኡሩሶ፣ ዳዳ፣ (ሶሌቾ) በርጋጌኤ፣ ሀበሎ፣ ሀዱባ፣ ባደጐ፣ ሆጄኤ፣ ዋየቦ፣ ሀንቃላ፣ አጎር-ገሣ/ ሎካ፣ ዱግሞ፣ መስመስ፣ ሳውካ፣ ገንዛ፣ ኤሬራ፣ መሳዋ፣ ባዳዋች፣ ደዋ-ዲጋላ ናቸው። እነዚህ ጐሳዎች የተለያየ ባህላዊ የአስተዳደር እርከኖችና መሪዎች ያላቸው ሲሆን ፤ ይህም ከዝቅተኛው ወደ ከፍተኛው እንደሚከተለው ይገለጻል።
1. ምኔ (ቤተሰብ )ሲሆን የደረጃው መሪ ምኒዳና ይባላል
2. ሞሎኒ( ጐጥ/ ኦኦሊዳና) የጐጥ መሪ
3. ሱላአ ( ነገድ/ ሱኡሊዳና) የነገድ መሪ
4. ጊዕቾ( ጐማ/ ጊዕችዳና) የነገድ መሪ
5. ግራ( ሔረሰብ/ ግዕሊዳና) የብሔረሰቡ መሪ
የሀዲያ ባህላዊ አስተዳዳሪዎች አመራረጥ መመዘኛው ግላዊ ብቃትና የኅብረተሰብ ሚዛን ናቸው።
በግላዊ ብቃቱ የብሔረሰቡን ባህላዊ እሴቶች ጠንቅቆ የማወቅ፣ አንደበተ ርዕቱነት፣ አስተዋይነት፣ ቀናነት፣ ቸርነት፣ ይቅርባይነት፣ ሀብትና ወዘተ ናቸው።
በብሔረሰቡ ሁለት ዓይነት የተለያዩ የቤት አሠራሮች አሉት። የመጀመሪያው ከላይ እስከታች ሣር የሚለብስ ጐጆ ሲሆን «ሁጉማኦ» ይባላል። ሁለተኛው ግድግዳውና ጣሪያው ተለይቶ ጣሪያው በሣር የሚከደንና «ፌንጋሞ» በመባል የሚጠራው ነው። በቤት አሠራሩ ሂደት ውስጥ ዋና ተሳታፊዎች ወንዶች ሲሆኑ፤ በምርጊቱ ላይ የሚሳተፉት ሴቶች ናቸው።
የሀዲያ ብሔረሰብ ከ45 በላይ ባህላዊ ምግቦችና የተለያዩ ባህላዊ መጠጦች እንዳሉት ይነገራል። ብሔረሰቡ በየዕለቱ ከሚመገባቸው የዘወትር ምግቦች መካከል ቆጮ፣ ቂጣ፣ ወተት እና የወተት ተዋጽኦ፣ ቆሎ፣ ቡና፣ ድንችና «ቡሎ» ለአብነት የሚጠቀሱ ናቸው። ነጭ ሽንኩርት (ቱማ) እና ጤና አዳም (ቅንትለማ) ከምግብነት በተጨማሪ ለባህላዊ መድኃኒትነት ሲያገለግሉ የኮሶ ዛፍም ለመድኃኒትነት ይጠቀማሉ።
ታዋቂ ሰዎች
ለማስተካከልFollow Us Me