ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲናግዴ ከኦሮሞ ገበሬ አባታቸው ከአቶ ዲነግዴ ቦተራ እና የሰባት ቤት ጉራጌ ቦዞ ሰንጌ ከሆኑት እናታቸው ከእመት ኢጁ አመዲና በሺ ስምንት መቶ አርባ ሶስት እና አርባ አራት አካባቢ ፣ በአመያና ወሊሶ አካባቢ ተወለዱ፡፡ በአድዋ ዘመቻ ጊዜ በአሽከር ብዛትና በደግነት ሥራ በጣም የተመሰገኑት ሀብተ ጊዮርጊስ በ1889 ዓ.ም. ፊታውራሪ ተብለው የጦር አበጋዝነቱን ተሹመዋል፡፡

ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲናግዴ

የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዕረፍት

ለማስተካከል

ፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ዲነግዴ ዓርብ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፲፱ ዓ.ም. አርፈው፣ በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተ ክርስቲያን ተቀበሩ፡፡ በምክር አዋቂነትና በአስተዳደር ፈሊጥ የተመሰገኑ ነበሩ፡፡

ጃንሆይ አፄ ምኒልክ ታማኝ አሽከር ነበሩና ዕለተ ሞታቸው ከጃንሆይ ዕለተ ሞት ጋራ በትክክል ስለተጋጠመ፣ ሰው ሁሉ እያደነቀ ተናገረ፡፡ አፄ ምኒልክ የሞቱት ዓርብ ታኅሣሥ ፫ ቀን ፲፱፻፮ ዓ.ም. ነበር፡፡ መድፍ ተተኩሶ፣ ነጋሪት ተጐስሞ በአራዳ ጊዮርጊስ ቤተክርስቲያን ግርማዊት ንግሥት ዘውዲቱአልጋ ወራሽ ራስ ተፈሪ መኰንን በተገኙበት የፊታውራሪ ሀብተ ጊዮርጊስ ቀብራቸው ሲፈጸም፣ ባለቤታቸው ወይዘሮ አልታየ ወርቅ የባላቸውን ግምጃ ሱሪና ራስ ወርቅ ይዘው ሲያለቅሱ፣ ሌላውን ሁሉ አስለቀሱት፡፡ የአማርኛ ቅኔ አዋቂው አቶ ተሰማ እሸቴም በሰምና ወርቅ ግጥም እንዲህ አሉ፤ ‹‹ከምኒልክ ይዞ እስካሁን ድረስ፣ የአልታየ ሞት ሆነ የሀብተ ጊዮርጊስ፡፡››[1]

ዋቢ ምንጮች

ለማስተካከል
  1. ^ መርስዔ ኀዘን ወልደ ቂርቆስ፤የሐያኛው ክፍለ ዘመን መባቻ፣1999