መለጠፊያ:More citations needed

መለጠፊያ:Infobox religious buildingመለጠፊያ:Contains special characters ተድባበ ማርያም (በቀዳሚ ስሟ ተድባበ ጽዮን). በደቡብ ወሎ በቀድሞው ቦረናና ሳይንት አውራጃ የምትገኘኝ በኢትዮጵያ ከሁሉም ቀድማ የተመሰረተች ታሪካዊ አድባር ናት፡፡ ተድባበ ማርያም በኦሪት ዘመን በቤተመቅደስ (ምኩራብ) አምልኮተ እግዚአብሔርና ፣መስዋዕተ ኦሪት ከተሰዋባቸው ቀደምት አድባራት መካከል አንዷና ዋናዋ ናት።}}).

የምስረታ ታሪክ

ለማስተካከል

ተድባበ ማርያም በ982 ዓመተ ዓለም (ከእየሱስ ልደት በፊት) የተመሰረተች ሲሆን መስራቹ ደግሞ የቤተልሔም ተወላጅና የአሚናዳብ ዘር የሆነው ሳቤቅ ነው። ሳቤቅ የቅዱስ ዳዊት የወንድም ልጅ ሲሆን፤ በአዛሪያስ መሪነት ከእስራኤል ወደ ኢትዮጵያ ታቦተ ጽዮንን ተከትለው ከመጡት 12,000 (አስራ ሁለት ሺህ) ነገደ እስራል መካከል አንዱ ነው። አዛሪያስ ደግሞ የተድባበ ማርያም የመጀመሪያው ፓትርያርክ ነው። በመጻህፍትም እንደተደነገገው ተድባበ ማርያም የፓትርያርክ መቀመጫ ነበረች።

በመፅሐፈ ሱባኤ ዘአማኑኤል ካልእ ገጽ 2:6 ላይ እንደተጻፈው፤ ከሳቤቅ ጋር ከኢየሩሳሌም ወደ ኢትዮጵያ አብረውት ከመጡት መካከል ሊቀ ካህን አዛርያስ፣ የዳዊት ልጅ ከአቢያጥ የተወለደው ጌዴዎን፣ የእሴይ ልጅ የሰሎሞን አጎት ኤልያብ፣ የዳዊት የልጅ ልጅ የአምኖን ልጅ ሔት፣ ኢዩኤል፣ ከነገደ ቢኒያም የተወለደው አብሔል፣ ከከነዓን የተወለደው በልዳድ፣ ከነገደ ይሁዳ የተወለደው አሴር፣ ከመሳፍንት ወገን የሆኑት ሱርባ እና ጉርባ ጥቂቶቹ ናቸው። ከሌዋዊያኑ ካህናት ጋር ወደ ኢትዮጵያ ከመጡት መሣፍንት፣ መኳንንትና፣ ወይዛዝርት መካከል 1,500 (አንድ ሺህ አመስት መቶ) የሚሆኑት በተግባረ ዕድ የሰለጠኑ የወርቅና የብር፣ የብረትና የመዳብ፣ እንዲሁም የነሐስ አንጥረኞች አዋቂዎች ጠቢባን ፀበርተ ዕፀውና ወቀርተ አዕባን ናቸው፡፡

ወደ ኢትዮጵያ ከገቡም በኋላ 2,500 (ሁለት ሺህ አመስት መቶ) የሚሆኑት የሌዋዊያን ካህናትና ነገደ እስራል ተከዜን ተሻግረው በየጁ በኩል አድርገው ተጉዘው በጥንቱ አጠራር አምሐራ ሳይንት የሚባለው አካባቢ ላይ ሰፍረዋል። አማራ ሳይንት፣ የአሁኗ ተድባበ ማርያም ካለችበት አምባ ላይ እንደደረሱ 12 በር ባለው ታቦር  ተራራ ላይ ለእግዚብሔር ቤተ መቅደስ ሰርተው የአምልኮ ስርዓታቸውን ማከናወን ጀመሩ። ቦታዋንም በሀገሩ ስም ገሊላ ብሎ ጠራት፡፡ ፓትርያርክ አዛሪያስ ደስ አለውና ስሙን በቡራኬ አፀደቀለት፡፡ ቤተ መቅደሱን ሰርቶ ሲጨርስ ከሌዋውያኑም ከካህናቱም ከፍሎ መስዋተ ኦሪት የሚሰው ካህናትና ሌዋውያንንም ሾመ፡፡ መስፍኑ ሳቤቅ ቤተልሄማዊም በገፀ ንጉስ በወርቅ ወንበር የሚቀመጥ ነበር፡፡ በኋላም ሌዋዊያኑ ካህናት ግማሾቹ ደብር ደባብ እንበላት አሉ አዛርያስ እና የዳዊት የወንድም ልጆች ሳቤቅ ይህቺማ የኢየሩሳሌም የዳዊት መታሰቢያ ከተማ ትሆን ዘንድ ተድባበ ጽዮን እንበላት ብለው እንደሰየሟት ይነገራል፡፡ በኋላም በዘመነ ሐዲስ ክርስትና ሲስፋፋ አማሮች ተድባበ ጽዮን የሚለውን ስያሚ እንዲቀይሩ የአክሱም ነገስታት የነበሩት አብረሃ ወአጽበሃ አሰገደዷቸው፡፡ ነገስታቱም ተድባብ ጽዮንን ተድባበ ማርያም ብለው ሰየሙ፡፡ ትርጓሜውም ለእግዚአብሔር የተመረጠ ከፍተኛ ቦታ ማለት ነው፡፡

ተድባበ ማርያም የተመሰረተችበት ተራራ 12 በሮች ሲኖሩት፣ ወደ ተራራው መዝለቅ ወይም መግባት የሚቻለው ግን በሁለት የተፈጥሮ በር ብቻ ነው። እነዚህ 12 በሮችም ለነገደ እስራኤል መታሰቢያ ይሆኑ ዘንድ ሳቤቅ አገሮቹን አሻግሮ እያየ በሀገሩ ምሳሌ ሰይሟዋቸዋል፡፡ እነዚህም በሮች ገሊላ፣ደብረ ዘይት፣ ኬብሮን፣እያሪኮ፣ሎዛ፣ታቦር፤ ቦረና መግቢያ ላይ ሊባኖስ፣ ደማስቆ፣ አርሞንኤም፣ ደብር ፋራን፤ በሰሜን በኩል ደግሞ ኮሬብ ፣ቃዴስ ደብረ ፍጌህ፣ ቂሣርያ፣ ቢታኒያ፣ ጋዛ፣ ጎልጎታ፣ ፌልስጥኤም በመባል ይታወቃሉ፡፡ ሳቤቅ አማራ ሳይንትን ያስተዳድር እንደነበር ተጽፏል።ዙፋኑ፣ ዳታኑና፣ ወንበሩ የብረት ዙፋን በመባል ይታወቃል።/ያሬድ ግርማ ጎንደር ታሪክ 1999 ዓ.ም

ርዕስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም በብሉይ ኪዳን ስለመመስረቷ ምስክር የሚሆኑ አንዳንድ የኦሪት ሥረዓቶች ሲከናወኑ ይስተዋላሉ ታቦታቱ በበሚነግሱበት ወቅት በምስራቅ ያሉ ምዕመናን ነዋያተ ቅዱሳቱን ይዘው በምዕራብ ካህናት ተሰልፈው በሰሜን ያሉ ምዕመናን መጋረጃን ይዘው በደቡብ ያሉ ምዕመናን ጎራዴውንና ካሰማውን ይዘው መንቀሳቀሳቸው በኦሪት ዚሁልቁ ፪፣፫-፬ ያለውን የኦሪት ሥርዓት ያመለክታል።

አጼ ይኩኖ አምላክ  በ13ኛው ክ/ዘ ቤተመንግስታቸውን በታቦር ተራራ አድርገው በብሉይ ዘመን የፍርድ መስጫ የነበረውን አደባባይ (ጉላቴ) እንዳሉት ይነገራል። በተራራው በስተቀኝ በኩል በሚገኘው በዚህ አደባባይ በ1270 አጼ ይኩኖ አምላክ  የአማርኛ ቋንቋን ብሄራዊ ቋንቋ እንዲሆን አውጀውበታል። በተጨማሪም በተጋር ተራራ ዮሐንስ ገብላዊ የቅኔ መድብል ያዘጋጁበት ብሉያተ ካህናት የተናገሩበት ጽዋተ ዜማ የተዘመረበት ቦታ ነው። የአፄ ይኩኖ አምላክ ቤተ-መንግስት ፍርስራሽ ይገኝበታል ተብሎ የሚታመነዉ በታቦር ተራራ ነው። [1] [2] [3] [4]

ህንጻ ቤተክርስቲያን

ለማስተካከል

ተድባበ ማርያም ስትመሰረት በኦሪት ዘመን በነበረው ስርዓተ አምልኮተ ስለነበር አመሰራረቷ እንደ ቤተመቅደስ (ምኩራብ፣ አድባር) ነበር። በገድለ ገላውዲዎስ ላይ እንደተመለከተው ግን፣ ለዘመናት በድንኳን ውስጥ እንደነበረች ተገልጿል። የኋላ ኋላ በዘመነ ሃዲስ የክርስትና መስፋፋትን ተከትሎ ህንጻ ቤተክርስቲያን ተሰርቶላታል። የተድባበ ማርያምን የመጀመሪያ ህንጻ ቤተ ክርስቲያን ያሰሩት አጼ ገላውድዎስ ናቸው። በስማቸውም ጽላት ተቀርጾለቸው በየአመቱ ግንቦት 2 እየተከበረ ይገኛል። ህንጻ ቤተክርስቲያኑ በየዘመናቱ በተነሱ ነገስታት ሲሰራና ሲፈርስ ኖሮ አሁን ያለውና ከነሞገሱ የሚታየው ህንጻ ዘጠነኛው ህንጻ ሲሆን የተሰራው በንጉሥ ሚካኤል ነው፡፡ የሳር ጣሪያዋ ደግሞ በ1955 ዓ.ም. በእቴጌ መነን መልካም ፍቃድና ገንዘብ ቆርቆሮ እንዲለብስ ተደርጓል፡፡

አጼ ገላውድዎስ አባታቸውን አጼ ልብነ ድንግልን ተክተው አገራችን ኢትዮጵያ ከ1533 አስከ 1551 ዓ.ም ድረስ ለ19 አመታት አስተዳድረዋል ፡፡ አጼ ገላውድዎስ በልዩ ልዩ ስፍራዎች ከግራኝ አህመድ ጋር ጦርነት አካሂደዋል፡፡ በመጨረሻም አጼ ገላውድዎስ የተድባበ ማርያምን ጽላት በመያዝ ዘምተው በ1535 ዓ.ም በበጌምድር ግዛት ግራኝን ድል አድርገው አሸንፈዋል፡፡ ጽላቷን ይዘው ከአጼ ገላውዴዎስ ጎን የተሰለፉት በወቅቱ የተድባበ ማርያም ፓትርያርክ የነበሩት አባ ዮሐንስ ናቸው። ከዚያም አጼ ገላውድዎስ ዋና ከተማቸውን ተድባበ ማርያም ካስማ ከተባለ ቦታ ላይ አደረጉ፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ተድባበ ማርያም በአካባቢው ህብረተሰብ ‹‹የግራኝ እመቤት›› እየተባለች ትጠራለች፡፡ [5] [6] [7]

ቤተክርስቲያኑ አራት በሮች (> 3 ሜትር ቁመት) እና 32 መስኮቶች (> 2 ሜትር ቁመት) በውጭ በኩል ክብ ክብ ነው። በንድፍ ፣ ቤተክርስቲያኑ በሦስት ክፍሎች በተሰበሰቡ ክበቦች ተደራጅቷል። በማዕከሉ ውስጥ ያለው አብዛኛው ክፍል ውስጠ ቅድስት (ቅድስተ ቅዱሳን) እና ዲያሜትር 24 ሜትር ያህል ነው። ታቦቱ በግልጽ ድንኳን ውስጥ (ድንኳን) ውስጥ እንደሚቀመጥ የታመነበት ይህ ነው። አሁን ባለችበት ሁኔታ ፣ ቤተክርስቲያኑ በአጠቃላይ ወደ 34 ሜትር ዲያሜትር ትለካለች። 

ሥርዓተ በዓላት

ለማስተካከል

በዘመነ አራት የቂጣ በዓል የአይሁድ ፋሲካ ይከበር ነበር፡፡ በዘመነ አብረሃ ወአጽብሃ ተድባበ ማርያምን አንጽው ካበቁ በኋላ ጥር 21 ቀን በአሏን ለማክበር ደንግገው ነበር፡፡ ይህም የበአል አከባበር እስከ ዐፄ ገላውዴዎስ ከቆየ በኋላ ዐፄ ገላውዴዎስ ግራኝ አህመድን ድል አድርጎ ሲመለስ ግንቦት ፩ ቀን ተድባበ ማርያም በመግባቱ የገባሁት በልደቷ እለቱ የእመቤታችን ልደቷ ነው በማለት የልደታን ጽላት አሰገብቶ የተድባበ ማርያምን በአል ግንቦት ፩ ቀን እንዲሆን አዋጅ አስነገረ፡፡ ከዚያን ዘመን ጀምሮ እስከ አሁን ድረስ ግንቦት አንድ ቀን በደማቆ ሁኔታ ይከበራል፡፡ በማግስቱ ግንቦት ሁለት የገላውዴዎስ ልደት በመሆን ተከብሮ ይውላል፡፡

ከክብረ በአሏ በተጨማሪ ከዓመት እስከ ዓመት ሰብሀተ ነግህና ሠዓታት ቅዳሴና መዓልት ሰዓታት አይቋረጥባትም፡፡ አሁን በሌላው ደብር ዓመት እስከ ዓመት ይቀድስ ነበር፣ ሰብሀተ ነግህ ይቆምበት ነበር ተብሎ ይነገርበታል እንጀ ሲሆን አይታይም ተድባበ ማርያም ግን እስከ አሁን ድረስ ቅደዳሴና ስብሐተ ነግህ ሰዓታትና መዓልት ሰዓታት ዓመት እስከ ዓመት አይቋረጥም፡፡ ዋዜማው ከጧቱ ሦስት ሰአት ተጀምሮ ከቀኑ አስር ሰአት ያልቃል ማህሌቱ ማታ ሁለት ሰአት ተጀምሮ እስከ ቅዳሴ መግቢያ ይቀጥላል በማህሌት ሰርዓቱ ላይ የሚቆመው እንደሌላ ቦታ መልክዓ ማርያም ሳይሆን የራሷ ሌቃውንት የደረሱት መልከዓ ልደታ ነው፡፡ ለአብነት ያህል ሰላም ለህንብርትኪ ዘአርያሁ ሰሌዳ ወለ ማህጸንኪ ቤቴል ማህደረ ክርስቶስ እንግዳ በእንቲአኪ ይብሉ ማርያም ሠራዊተ ንጉስ ይሁዳ ዳዊት ዘመዳ ኤያቄም ወለዳ ኤያቄም ወለዳ ዳዊት ዘመዳ፡፡ እያሉ የራሷን ድርሰት ይቆማሉ ፡፡ ይህም በሌላ ቦታ አይባልም፡፡

ሊቀ ካህኑ ሁል ጊዜ የአይሁድ ዘሮች እንደሆኑ ከታመነ ከካህናት ክፍል ጎሳዎች ይመረጣሉ። በተጨማሪም ፣ ዲያቆኖች ፣ ዕድሜያቸው ከ 9 ዓመት በታች ብቻ ፣ አገልግሎት እንዲሰጡ ይፈቀድላቸዋል። በቤተክርስቲያኑ ውስጥ ጥቅም ላይ የዋሉት አብዛኛዎቹ ቅርሶች እና መገልገያዎች ዕጣን ማቃጠያ (ማጣሪያ በሰንሰለት) ጨምሮ ከንፁህ ወርቅ የተሠሩ ናቸው። ወደ ቅድስተ ቅዱሳን በሚገቡበት ጊዜ ረዳቶች በአደጋ ጊዜ የሊቀ ካህናቱን አካል በደህና ከውስጣዊው ቅድስት ውስጥ እንዲወጡ ለማድረግ ከሊቀ ካህኑ ጋር ታስሯል። የኢ / ኦ / ተ / ቤ / ክ 3 ኛ ፓትርያርክ አቡነ ታክላ ሃይማኖት ወደ ቅድስተ ቅዱሳን ለመግባት ሞክረው በገመድ ተጎትተው ቢወጡም ከአንድ ዓመት በኋላ በ 1988 ዓ.ም. 

በዓመታዊ በዓላት ወቅት በታቦቱ ፊት የመጥፎ አደጋን ተከትሎ መሬቱን ስለወረረ ወረርሽኝ አንድ ታሪክ ይነገራል። በኋላ የአገሩ ሰዎችም በእብጠት እና በበሽታ ተሠቃዩ። ከዚያን ጊዜ ጀምሮ ታቦቱ ከድንኳኑ ውጭ ተሸክሞ ወይም በጉባኤ ወቅት ለሕዝቡ ታይቷል። 

የቅርስ ክምችት

ለማስተካከል

ተድባበ ማርያም እድሜ ጠገብና አያሌ ታሪክ ያስተናገደች እጅግ ጥንታዊ መካነ ቅርስ ናት፡፡ የሚታዩና፣ የማይታዩ፤ ብሎም የተሰወሩና፣ ያልተነገሩ አያሌ ድንቅ የኢትዮጵያ ታሪኮችና ቅርሶችን ጠብቃ ዘመን ያሻገረች ህያው ሙዚየም ናት፡፡ ነገሥታት ዘውዳቸውን አውልቀው የሰጧት፣ ካባቸውን የደረቡላት፣ ደስታቸውን በድንቅ ስጦታዎቻቸው የገለጹላት ስፍራ ናት፡፡ አፄ ገላውደወስ፣ አፄ ዘርአያእቆብ፣ አፄ በዕደማርያም፣ አፄ እስክንድርና፣ ንጉስ ሚካኤልና ሌሎች ነገስታትም ልብሰ መንግስታቸውን፣ እንቁ፣ አልማዝ፣ ወርቅ፣ ብርና፣ ሌሎች የከበሩ ማእድናትንም ለቤተክርስትያኗ አበርክተዋል። ተድባበ ማርያም እጅግ ብዙ ውድ ሀብቶች አሏት ፣ አንዳንዶቹም ከድሮው መጽሐፍ ቅዱስ (ኦሪት) ጀምሮ ናቸው። ክምችቶቹ አሁን በአብያተ ክርስቲያናት ግቢ ውስጥ ባለው ሙዚየም ውስጥ ይታያሉ።

እጅግ ልዩ ከሆኑት ቅርሶች መካከልም የበግ ምስልና የተቁለመለመ የበግ ቀንድ ያለበት መስቀል በዚያ ይገኛል፡፡ የዚህ መስቀል ብርሀን የሚያስገርምና ዓይንን የሚያንፀባርቅ ሲሆን ከምን አይነት ማእድን እንደተሰራ አይታወቅም፡፡ ከጥንታዊያን ነገስታትም መካከል ዐፄ ካሌብ ወደ ደቡብ አረቢያ የናግራንን ክርስቲያኖች ለመርዳት ሲዘምቱ ፓትርያርክ ዘሙሴ እሱም የኦየሩሳሌምን ገዳም ያቀናና በመጨረሻም በአባ ጴንጠሌዎን ገዳም ገብቶ ያረፈ አባት ጋር ዘምተው ድል አድርገው ሲመለሱ ይዘው የሄዱትን ጋሻ በስዕለት ለተድባባ ማርያም አስገብተውት በቦታው ይገኛል፡፡ እንዲሁም የእብራይጥ ሲኖዶስና የአረማይክ ቅዳሴ እግዚእ በቦታው ላይ ይገኛል፡፡ በዚህ ገዳም ከ1000 ያላነሱ የብራና ጥንታዊያን መጸህፍት ይገኛሉ እነዚህም መጻህፍት ክፊሎቹ በጥንታዊት የአክሱም ዘመን መንግስት የተጻፈ ሲሆኑ ሌሎቹ ደግም በመካከለኛ ዘመን የተጻፉ ናቸው፡፡

ተድባበ ማርያም ለትውልድ ካቆየቻቸው ቅርሶች መካከልም የሚታዩትና የሚዳሰሱት በጥቂቱ ከዚህ በታች ተዘርዝረዋል፡፡

1. የበግ ምስልና እንደ ኮኮብ የሚያበራ የተቁለመለመ የበግ ቀንድ ያለበት መስቀል

2. ዐፄ ካሌብ ወደ ደቡብ አረቢያ የናግራንን (የመን) ክርስቲያኖች ለመርዳት ይዘውት የዘመቱት ጋሻ

3. የእብራይጥ ሲኖዶስና

4. የአረማይክ ቅዳሴ እግዚእ (ገበታ ቅዳሴ)

5. በአረማክ ቋንቋ የተጻፉ የስሌዳ መጻህፍት

6. 4. በአረበኛና በግእዝ የተጻፉ መጻህፍት

7. ወንጌል ዘወርቅ እየተባለ የሚጠራ ትልቅ የወርቅ ጉብጉብታ ያለበት ቅዱስ ወንጌል

8. የመጀመሪያው ኢትዮጵያዊ ጳጳስ የቀደሰበት የእጅ መስቀል

9. የመጥመቀ መለኮት ቅዱስ ዮሐንስ መስቀል

10. የዕጨጌ ዮሐንስ በትረ ሆሳዕና እና የእጅ መስቀል

11. የአቡነ አኖሪዎስ የእጅ መስቀል

12. የአቡነ ቄርሎስ የእጅ መስቀል

13. ስእርተ ሀና (የማርያም እናት፣ ቅድስት ሀና ጸጉር)፣ የተቀመጠበት የሽክላ ገንቦ ጥንታዊና በስነ-ጥበባዊ ይዘቱ የሚያስገርም ነው

14. ሄሮድስ የጨፈጨፋቸው ህጻናት ዓጽም በክፊል

15. የቅዱስ ጊዩርጊስ አወራ ጣት

16. 13. በአጠቃላይ የ28 ሰማእታት ዓጽም ይገኛል

17. የዐፄ ገላውዴዎስን ጨምሮ የስድስት ነገስታትና የአራት እጨጌዎች ዓጽም ይገኛል

18. የአጼ ዳዊት ዙፋን

19. የቅዱስ የሬድ ድጓ እና ጊዩርጊስ ወልደ አሚድ፣ ገድለ አዳም

20. ከ1000 የሚበልጡ ጥንታዊ የብራና መጻህፍት

21. ሉቃስ እንዳሳላት የሚነገርላት የቅድስት ድንግል ማርያም ስዕለ አድህኖ

22. በርካታ ጥንታዊ የእጅና የመጾር መስቀል

23. 20.ልዩ ልዩ ንዋየ ቅድሳት

24. የነገስታት ዘውዶች፣ወንበርና አልባሳት

25. ባለ 3 ተከፍች የገበታ ስእልና ጥንታዊና ስነ ጥበባዊ ቅርሶች ይገኛሉ

ስነ-ፅሁፍና ኪነ-ጥበብ

ለማስተካከል

ርእስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርያም የሐዲስ ኪዳን የስርዓት መነሻ የቅኔ ምንጭ የደጔ ምልክት ነቅ ደጔ ከጠፋ በኋላ የድጔን ምልክት በመፍጠር ለትወልድ ያሰተላልፉ አዛዢ ጌራንና አዛዢ ዘራጉኤልን ያፈራች ዙሪያዋን በታላቅ ገዳማት እና አድባራት የተከበበች የአማርኛ ቋንቋ መገኛ እንደሆነች የሚነገርላት የጎንደር የጎጃምና የሽዋ እንዲሁም የወሎ መገናኛ ማእከል የሆነች ለስነ ልሳን ተመራማሪዎች ትልቅ የቅርስ ስፍራ የሆነችው ርእስ አድባራት ወገዳማት ተድባበ ማርይም የታቦር ተራራ የቅኔ መገኛ ሰማንያ ጋሻ መሬት የሸፈነ የደንቆር ብሔራዊ ፓርክ ክልል የሚገኝባት ስትሆን ለኢትዮጵያ ታላቅ የታሪክ ማህደር ናት፡፡

ለበርካታ ጊዜያት በተፈጠሩ ክስተቶችና ወረራዎች አያሌ የቤተክርስትያን ንዋያተ ቅድሳት፣ ቅርሶች፣ መጸህፍትና፣ ሌሎችም ተቃጥለዋል፣ ወድመዋልም። በነዚህም ወረራዎች በርካታ ገዳማትና አድባራት ሲቃጠሉና ሲመዘበሩ ተድባበ ማርያም ግን ምንም አይነት ቃጠሎና የቅርስ ዝርፊያ አልደረሰባትም፡፡

ለዐዋቂዎች ጥበብን እንናግራቸዋለን ነገር ግን የዚህን ዓለም ጥበብ ወይም ያልፉ ዘንድ ያላቸውን የዚህን ዓለም ሹመች ጥበብ አይደለም፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር አስቀድሞ ከዘመናት በፊት ለክብራችን የወሰነውን ተሰውሮም የነበረውን የእግዚአብሔርን ጥበብ በምስጢር እንናገራለን፡፡


ማጣቀሻዎች

ለማስተካከል

 

  • የንጉስ ጉላውዴዎስ ዜና መዋዕል ፣ ሰለሞን ገብረየስ። https://books.google.com.et/books?id=PQmfwwEACAAJ
  • ጎጃም ውስጥ ጉዞዎች-ቅዱስ ሉቃስ ኢኮንስ እና ብራንክሌዎን እንደገና ተገኙ። JSTOR 41965874 እ.ኤ.አ.
  • የወሎ ጠቅላይ ግዛት ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ታሪክ በኢትዮጵያ - 1769–1916። ምስጋናው ታደሰ መላኩ
  • የኢትዮጵያ ታሪክ - ጥራዝ II (Routledge Revivals) - ኑቢያ እና አቢሲኒያ ፣ ኢኤ ዎሊስ ቡጌ (ገጽ 346 ፤ 351 ፤ 350 ፤ 353)።
  1. ^ Solomon Gebreyes (2019). Chronicle of King Gälawdewos. ISBN 9789042936645. https://books.google.com/books?id=PQmfwwEACAAJ. 
  2. ^ Jean Doresse (1967). Ethiopia: Ancient cities and temples. https://books.google.com/books?id=q049MQAACAAJ. 
  3. ^ "A HISTORY OF MEDIEVAL CHRISTIANITY IN SOUTHERN WOLLO". Archived from the original on 2021-05-05. https://web.archive.org/web/20210505113910/https://wollo.org/monasteries-of-south-wollo በ2021-09-24 የተቃኘ. 
  4. ^ E.A. Wallis Budge (2015). A History of Ethiopia: Volume II (Routledge Revivals): Nubia and Abyssinia. ISBN 9781138791695. 
  5. ^ The Nordic Africa Institute, Bernhard Lindahl. "Local history of Ethiopia : Ta Guba kebele - Teru wereda". https://nai.uu.se/download/18.39fca04516faedec8b249046/1580830940842/ORTTA.pdf. 
  6. ^ The Nordic Africa Institute, Bernhard Lindahl. "Local history of Ethiopia : Ta Taru - Tedo Ber". https://nai.uu.se/download/18.39fca04516faedec8b248e2f/1580829014075/ORTTA05.pdf. 
  7. ^ STEPHEN WRIGH. "Book and Manuscript Collections in Ethiopia". https://www.jstor.org/stable/41965704.