ስናን ወረዳ በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት ምስራቅ ጎጃም ዞን ከሚገኙ 17 ወረዳዎች መካከል አንዷ ናት። የወረዳዋ ዋና ከተማ ረቡዕ ገበያ ሲሆን ወረዳዋን ቢቡኝ ወረዳ (በሰሜን)፣ደባይ ጠላትግን (በሰሜን ምስራቅ)፣ አዋበል (በምስራቅ)፣አነደድ (በደቡብ ምስራቅ)፣ ጎዛምን (በደቡብ ምዕራብ) እና ማቻከል (በምስራቅ) 6 ወረዳዎች ያዋስኗታል። ወረዳዋ የበርካታ የመስዕብ ስፍራዎች መገኛ ስትሆን ከእነዚህም መካከል የጮቄ ሰንሰለታማ ተራራዎች(Mount Ras birhan)፣ በአብርኃ ወአፅብሐ ዘመነ መንግስት እንደተሰሩ የሚነገርላቸው ሦስቱ አብያተክርስትያናት (ደብረዘይት ማርያም ቤተክርስቲያን ፣ ስናን ማሪያም ቤተክርስቲያን እና ደበደቦ ማርያም ቤተክርስቲያን)፣ የዚላን ዘርዓ ብሩክ ተአምረኛ ጠበል፣የቀይ ቀበሮ ብርቅዬ እንስሳ፣ በወረዳው በተለያዩ ሰፍራዎች የሚገኙ አስገራሚ ዋሻዎች፣ የአባይ ወንዝ ገባር ወንዞች መነሻ እና የጮቄ አስደናቂ መልክአ ምድር ተጠቃሽ ናቸው። በአካባቢው ብዙ አዝርዕት፣ፍራፍሬና አትክልት የሚገኙ ቢሆንም በድንች፣ በአፕልና በቀርቀሃ ምርት ትታወቃለች።[1]

  1. ^ East gojjam zone map Different books related to the area Observation