ኖቪ ድቩር ክሩለፍስኪ (ፖሎንኛ፡- Nowy Dwór Królewski «አዲስ ንጉሳዊ ግቢ») በፖሎኝ የሚገኝ መንደር ነው። 190 ሰዎች ይኖሩበታል። በቀውምኖ ከተማ ዙሪያ ነው።

በ1867 ዓ.ም. በመንደሩ የተሰራው ቤተ መንግሥት

መንደሩ መጀመርያ የተመዘገበ 1390 ዓ.ም. ሲሆን በጀርመንኛ ስሙ ኖይሆፍ ይባል ነበር። እስከ 1423 ዓ.ም. ድረስ በቲውቶኒክ ወታደራዊ ስርአት ርስት ነበረ።