ኢትዮ ሬይን ሜከርስ (Ethio Rain Maker) በኢትዮጵያ ውስጥ ዛፎች በመትከል ረሃብን ለመከልከል የተቋቋመ ቡድን ነው።

አንድ የዛፍ መትከል ስራ ዕቅድ በኢትዮጵያ

አሁን ወደ ምድረ በዳ መጥተው በወንድማማችነት ገነት ይሠራሉ። በድርቅ አፈር ውስጥ የሚተክሉት ዘር ታላቅ ደን ይሆናል፤ ምድሪቱ እንደገና በሙሉ እስክትሸፈን ድረስ ረጀም ዛፎች በዝተው አረንጓዴ ክንፎቻቸውን ይዘረጋሉ።


ኢትዮ ሬይን ሜከርስ ምንድነው? ለማስተካከል

ኢትዮ ሬይን ሜከርስ ሃገራችንን አረንጓዴ ለማልበስ የተቋቋመ ቡድን ነው።

ሀገራችን ኢትዮጵያ በአለም መገናኛ ብዙሃን በረሃብ ስትጠራ፣ ህዝቦችዋ በጠኔ ሲሰቃዩ ዘመናት ተቆጥረዋል። የወገኖቻችን ስቃይ፣ የሀገራችን ኋላ ቀርነት በኢትዮጲያዊነታችን እያንዳንዳችንን ይመለከተናል። ላለፉት ሰላሳ አመታት በጎ አድራጊ ድርጅቶች በአይነትም ሆነ በጥሬ ገንዘብ በቢሊዮን የሚቆጠር ዶላር እንደረዱን መረጃ አውጥተዋል። የኛ ስቃይ ግን አላበቃም። መከር ሲመጣ ሰብል ከማጨድና ምርት ከመሰብሰብ ይልቅ ለልመና እጁን የሚዘረጋ ኢትዮጲያዊ ቁጥር በሶስት እጥፍ ጨመረ። ይህ ሂደት መቆም አለበት። እንዴት?

አበው “ነገርን ከስሩ …” እንደሚሉት የሁሉም ችግር መፍትሔው ያለው ከመነሻው ላይ ነው። የኛ ረሐብ መንስዔው ምንድነው? በአጭሩ ለመግለጽ ያህል ለረሐባችን መንስዔ የዝናብ አለመኖር (ድርቅ) መሆኑን ከረሐባችን ታሪክም ሆነ ጥናቱን ካካሄዱት ምሁራን መረዳት ይቻላል። ዛሬም ቢሆን ገበሬው ዝናብ በማጣቱ ሰብሉ መበላሸቱን ከአንደበቱ እየሰማን ነው። ጦርነትን ለማቆም የጦርነት መነሻ ሃሳቦችን ማስወገድ እንጂ ጦርነትን ከጦር ሜዳ ማስቆም እንደማይቻል ሁሉ የሃገራችንንም ረሃብ ከመንስዔው እንንቀለው።

ኢትዮ ሬይን ሜከርስ፣ ኢትዮጵያ ዉስጥ ደን ማደነን (አፎረስቴሽን) ችግራችንን ከመቅረፊያ መንገዶች አንዱ እንደሆነ በማመን የተለያዩ ስልቶችን በመጠቀም ችግኞችን መትከል ጀምሯል።

1995 ዓ.ም. ከኢትዮጵያ ቅርስ ባለ አደራ ጋር በመተባበር በእንጦጦ የተፈጥሮ መናፈሻ አስር ሺህ ችግኞችን ተክሎ ሰባ ሁለት ከመቶው (7167) ፀድቋል። በ1996 ክረምት ደግሞ ሀምሳ ሺህ ችግኞችን ለመትከል አቅዶ ሀያ ከመቶው ተጠናቋል። በአሰላ፣ በመቀሌና በባህር ዳር አንድ ሺህ ዛፎችን የሚይዙ የተፈጥሮ መናፈሻዎችንን በመስራት ላይ ነን። በ1997 ለሀገራችን የሺህ አመት ስጦታ እንስጥ በሚል መነሻ ሀሳብ እያንዳንዱ ኢትዮጲያዊ አንድ ዛፍ ተክሎ የሚንከባከብበትን እቅድ አውጥተናል። ከነዚህም አንዱ አንድ ዛፍ ለአንድ ተማሪ ነው።

የሃገራችን የዘመናት ችግር በአንድ አመትና በጥቂት ሰዎች ጥረት አይፈታም። ለዚህ አላማ መሳካት የሁሉም ኢትዮጵያዊ ጥረትና እገዛ ያስፈልጋልና ሃገራችንን ከረሐብ ለመታደግ አብረን ዛፍ እንትከል። እንንከባከብም።

የውጭ መያያዣ ለማስተካከል

የኢትዮ ሬይን ሜከርስ ድረገጽ Archived ዲሴምበር 19, 2014 at the Wayback Machine (አማርኛ እና እንግሊዝኛ - Amharic & English)