1 አሹር-ኒራሪአሦር ነገሥታት ዝርዝር ዘንድ 26 ዓመታት (ከ1524 እስከ 1499 ዓክልበ. ገደማ) የአሦር ንጉሥ ነበረ።

ቀዳሚው 3 ሻምሺ-አዳድ ወንድሙ ነበር። ። በአሹር (አሦር) ከተማ አንዳንድ አረመኔ ቤተ መቅደስ እንዳሳደሰ ይታወቃል። ወደ ተለመዱት ማዕረጎች «የአሦር ገዥና የአሦር እንደራሴ» አዳዲስ ማዕረጎቹን «የአሦር አሳዳሽና የአሦር ገንቢ» ጨመረ።

ሆኖም ከዚህ ዘመን ብዙ ሌላ መረጃ የለም። ተከታዩ ልጁ 3 ፑዙር-አሹር ነበር።

ቀዳሚው
3 ሻምሺ-አዳድ
የአሦር ንጉሥ
1524-1499 ዓክልበ. ግድም
ተከታይ
3 ፑዙር-አሹር