ፖርት ኦፍ ስፔን
ፖርት ኦፍ ስፔን የትሪኒዳድና ቶቤጎ ዋና ከተማ ነው።
የሚኖርበት የህዝብ ቁጥር የአካባቢውን ኗሪ ሲጨምር 263,800 ሆኖ ሲገመት የራሱ የከተማው ኗሪ ቁጥር ደግሞ 45,300 ሆኖ ይገመታል። ከተማው 10°38′ ሰሜን ኬክሮስ እና 61°31′ ምዕራብ ኬንትሮስ ላይ ተቀምጦ ይገኛል።
በደሴቱ የነበሩ ኗሪዎች በሥፍራው 'ኩሙኩራፖ' የተባለ መንደር ነበራቸው። በ1530ዎቹ ስፓንያውያን እንዲሠፈሩት አንዳንድ ሙከራዎች አድርገው ስሙን 'ፕዌርቶ ዴ እስፓንያ' (የእስፓንያ ወደብ) አሉት። ነገር ግን ሠፈሩ ቋሚ አልሆነም። በ1552 ዓ.ም. የእስፓንያ ወታደሮች ምሽግ በዚያ አካባቢ ሰሩ። ከተማ እራሱ ግን በ1682 ዓ.ም. ገዳማ ሊገነባ ጀመረ። በ1749 ዓ.ም. የደሴቱ መቀመጫ ከ'ሳን ሆዜ ዴ ኦሩኛ' (የዛሬው ሰይንት ጆሴፍ) ወደዚህ ተዛወረ።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |