አስፈላጊ ጥሬ ዕቃዎች

ለማስተካከል

ግማሽ ኪሎ ግራም ተቀቅሎ በደንብ የተጠነፈፈ ፓስታ

2 የሾርባ ማንኪያ ዘይት

2 መካከለኛ ጭልፋ (200 ግራም) ቺዝ

4 የሾርባ ማንኪያ (100 ግራም) የገበታ ቅቤ

5 መካከለኛ ጭልፋ ቢሻሜል ሶስ

5 መካከለኛ ጭልፋ ቦሎኔዝ ሶስ

3 እንቁላል

አዘገጃጀት

ለማስተካከል

1. ፓስታውን ትልቅ ብረት ድስት ውስጥ በማድረግ ቦሎኔዝ ሶስና ሦስት ጭልፋ ቢሻሜል ሶስ መጨመር፤

2. በጭልፋ አገላብጦ በደንብ ማቀላቀልና እንቁላሉን መትቶ በመጨመር ማዋሃድ፤

3. የዳቦ መጋገሪያ ትሪ ዘይት ቀብቶ የተዘጋጀውን ውሁድ እንደ ዳቦ መጠፍጠፍ፤

4. የተረፈውን ቦሎኔዝ ሶስና ቢሻሜል ሶስ በላዩ ላይ በመቀባት መሸፈንና ቺዝ ላዩ ላይ መነስነስ፤

5. የገበታ ቅቤውን በማንኪያ ቆራርጦ ላዩ ላይ እያራራቁ ማድረግ፤

6. ዳቦ መጋገሪያ (ፉርኖ ቤት) ውስጥ ከቶ ማብሰል፣ ወይም በትልቅ ብረት ድስት በመጠፍጠፍ በላይና በታች ከሰል አድርጐ መሥራት፤

7. ወርቃማ ቀለም ሲያመጣ ማውጣት፤

8. ቀዝቀዝ ሲል እንደ ዳቦ በደንብ አስተካክሎ ስምንት ቦታ ቆርጦ ማቅረብ፡፡