ፓርሻታታር
ፓርሻታታር ወይም ፓርሻታር የሚታኒ ንጉሥ ነበር።
በኑዚ በተገኘ ሰነድ፣ ንጉሥ ፓርሻታ(ታ)ር ባረፈበት ዓመት እንደ ተጻፈ፣ ሻውሽታታርም እንደ ተከተለው ይላል። በብዙዎች አስተሳሰብ ይህ ፓርሻታር እና ባራታርና (ወይም ፓራታርና፣ 1480-57 ዓክልበ. ግ.) አንድ ንጉሥ ነበሩ። ሌሎች ግን የተለያዩ ነገሥታት ነበሩና ባራታርና ከፓርሻታታር ቀደመው የሚሉ ናቸው።
ከዚህ ቅርስ በቀር የፓርሻታር ስም አልተገኘም። ባራታርና እራሱ ካልሆነ፣ ከግብጽ ፈርዖን 3 ቱትሞስ ጋር የታገለው የሚታኒ ንጉሥ ሊሆን ይችላል።