ፍፁም ጠቅላይ
ፍፁም ጠቅላይ የሥልጣናዊነት መንግስት ዓይነት ሲሆን፣ በዚህ ግዛት ሥር ተቃውሞ ሙሉ በሙሉ የሚከለከል ሲሆን በማህበረሰባዊ እና የግልሰሰቦች ህይዎት ላይ ሙሉ ቁጥጥር ለማድረግ የሚጥር ሥርዓት ነው። ይህ ሥርዓት የሥልጣናዊ ዓይነት አገዛዝ የመጨረሻ ጽንፍ ተደርጎ የሚዎሰድ ነው።
የሥርዓቱ ደራሲ እሚባለው ፋሽስቱ ቤኔቶ ሙሶሎኒ ስለ ሥርዓቱ ሲናገር «ሁሉም ነገር በመንግስት ስር ሆኖ፣ ምንም ከውጩ የሌለ፣ ደገሞም ምንም/ማንም እማይቃዎመው መንግስት » በማለት ይገልጸዋል። ፍጽምናዊ ስርዓቶች፣ በአንድ መሪ፣ መፈናፈኛ የሌለው ሁሉን አቀፍ ፕሮፓጋንዳ፣ ፖለቲካዊ ጭቆና፣ የመሪ ኣምልኮ፣ ኢኮኖሚያዊ ቁጥጥር፣ ሰፊ የስለላ መረብ፣ የመናገር መብት መከልከል፣ እና መንግስታዊ ሽብር ይገለጻል።
ጅምር! ይህ አጭር ጽሑፍ መሠረት ወይም መዋቅር ነው። አሁን ሊያስፋፉት ይችላሉ! |