ፋሲል መዋኛጎንደር ከተማፋሲል ግቢ 2 ኪሎሜተር በስተ ሰሜን ምዕራብ ርቆ የሚገኝ፣ በአጼ ፋሲለደስ ዘመን ተሰረቶ የነበረው የመዋኛ ስፍራ ነው (በአንዳንዶች ዘንድ በቀዳማዊ ኢያሱ ዘመን እንደተሰራ ይጠቀሳል)። በመዋኛ ስፍራው መካከል ላይ ያለው ባለ ሁለት ፎቅ ቤት የአጼ ፋሲል መኖሪያ እንደነበር ይገመታል። በአሁኑ ዘመን፣ ለጥምቀት በዓል የሚያገለግል ሲሆን ውሃ በምድር ውስጥ በተቆፈረ ቦይ ከቀሃ ወንዝ ያገኛል። በድሮ ጊዜ በአየር በተነፋ አቅማዳ እየተንሳፈፉ ሰዎች ይዝናኑ እንደንበርና ሁልጊዜም በውሃ የተመላ እንደነበር ይነገራል። ከአጠገቡ፣ በስተምስራቅ፣ የአጼ ፋሲለደስ ፈረስ የነበረው የዞብል መቃብር ይገኛል።

ፋሲል መዋኛ
የአጼ ፋሲለደስ መኖሪያና መዋኛው በ ፋሲል መዋኛ
ፋሲል መዋኛ is located in ኢትዮጵያ
{{{alt}}}
ፋሲል መዋኛ

12°36′ ሰሜን ኬክሮስ እና 37°38′ ምሥራቅ ኬንትሮስ

-1px

1.መኖሪያ ቤት 2.ዋናው በር 3. ውሃ ከቀሃ ወንዝ የሚመጣበት መሬት የተቀበረ ቦይ 4.ፋሲል መዋኛ ድልድይ 5. የአጼ ፋሲለደስ መኖሪያ 6.ፋሲል መዋኛ ገንዳ 7. ወደገንዳው የሚያስገቡ ደረጃዎች 8.ውሃ ማፍሰሻ ቦይ 9. ሁለተኛ በር 10. የዞብል መቃብር

በ"Wikimedia Commons"
(የጋራ ፎቶዎች ምንጭ)
ስለ Category:Fasilidas' bath የሚገኛኙ
ተጨማሪ ፋይሎች አሉ።