ጪን ሽኋንግ (ቻይንኛ: 秦始皇) በ267 ዓክልበ. ተወልዶ የልደቱ ስም ዪንግ ጀንግ (嬴政) ነበረ። ከ254 ዓክልበ. እስከ 229 ዓክልበ. ድረስ በቻይና መንግሥታት ጦርነት ዘመን የጪን መንግሥት ንጉሥ ነበሩ። በ229 ዓክልበ. ደግሞ ቻይናን በማዋሐድ የመላ ቻይና ንጉሠ ነገሥት ሆኑ። በ218 ዓክልበ. እስካረፉበት ዓመት ድረስ ነገሡ።

ጪን ሽኋንግ (18ኛው ክፍለ ዘመን ተሳለ።)