ጥርስ (ማሽን)
(ከጥርስ(ማሽን) የተዛወረ)
ጥርስ ተሽከርካሪ ማሽኝ ሲሆን እላዩ ላይ በተቀረጹ ጥርሶች የሌላን አካል ጥርስ በመንከስ ጠምዛዥ ጉልበትን ከአንድ አካል ወደ ሌላ የሚያስተላልፍ ነው። ሁለት ወይም ከዚያ በላይ ጥርሶች ተባብረው ሲሰሩ አስተላላፊ(ትራንስሚሽን) ይሰኛሉ። ጥርሶች የአንድን ሃይል ምንጭ አቅጣጫ፣ መጠንና ፍጥነት ቀይረው ማስተላለፍ ይችላሉ። ስለሆነም ለመኪና ማርሽነት ግልጋሎት ይሰጣሉ። በጥርስ ቁጥሮች ልክ ትክክለኛ የፍጥነት ውድር መቀመር ስለሚቻል ጥርሶች ለሰዓት ስራ ያገለግላሉ።
የተለያዩ የጥርስ አይነቶች
ለማስተካከል-
ውስጣዊ ጥርስ
-
ስፐር ጥርስ
-
ሄሊካ ጥርስ
-
ድርብ ሄሊካ ጥርስ
-
ቤቬል ጥርስ
-
ህይፖይድ ጥርስ
-
አክሊል ጥርስ
-
ትል ጥርስ
-
ኢ-ክብ ጥርስ
-
ራክና ፒኞን ጥርስ
-
መሬትና ፀሐይ ጥርስ
-
ሃርሞኒክ ጥርስ
-
ቆጥ ጥርስ