ጥቅማዊነት
(ከጠቃሚያዊነት የተዛወረ)
ጥቅማዊነት (እንግሊዝኛ፦ Utilitarianism /ዩቲሊቴሪየኒዝም/) በፍልስፍና ስለ ድርጊት ትክክለኛነት የሚሰፍን ግብረ-ገባዊ ኅልዮ ነው። ከሁሉ የሚሻለው ድርጊት ለአብዛኛዎቹ ደስታ ወይም ጥቅም የሚያመጣው ያው ነው የሚለው ፍልስፍና ነው።
ጽንሰ ሃሣቡ በግሪኩ ፈላስፋ በኤጲቁሮስ ጽሑፍ ይገኛል። መርኁ ከጥንት ጀምሮ ቢታወቅም፣ በቅርቡ ዘመን ስለ ጥቅማዊነት በተለይ የጻፉት ፈላስፎች እንግሊዞች ጄርሚ ቤንታም እና ጆን ስቱዋርት ሚል ነበሩ። ቤንታም እንደ ጻፈው የተሻለው ሥራ ለብዛቱ በጎ የሚሆነው ነው። በሱ ፍልስፍና አስተያየት ሰዎች ሁሉ ለ'2 ጌቶች' እነርሱም ለደስታና ለሀዘን ሲገዙ ይኖራሉ። ስለዚህ ለሰዎች በጎ የሆነ ሥራ ማለት ደስታን ማምጣትና ማብዛት እንደ ሆነ ገመተ። አንዱ ድርጊት ለጥቂቶች ደስ ቢያስን፣ ሁለተኛውም ለብዙዎች ደስ ቢያሰኝ፣ ሁለተኛው ይመረጣል ማለት ነው። ወይም እንደገና አንዱ ድርጊት ለ10 ሰዎች፣ ሁለተኛውም ለ5 ሰዎች ብቻ ደስታ ወይም ጥቅም ካመጣ፣ መጀመርያው የበለጠው ግብረገብ ነው ብሎአል። የቤንታም ደቀ መዝሙር ጆን ስቱዋርት ሚል 'ዩቲሊቴሪያኒዝም' በሚል መጽሐፍ ለፍልስፍናው ስሙን አወረሰ። [1] Archived ሜይ 6, 2010 at the Wayback Machine